Saturday, February 16, 2013

የፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ ሁለተኛ ዙር መግለጫ ሰጠ


አርእስተ ዜና፡-
  • የጸሎተ ምሕላው ሱባኤ ምርጫው እስኪጠናቀቅ ይቀጥላል
  • ኮሚቴው የለያቸውን ዕጩዎች የካቲት 14 ቀን ለቅ/ሲኖዶስ ያቀርባል
  • ከአንድ ሺሕ የካህናትና ምእመናን ጥቆማዎች በላይ እንደተሰበሰበ ተገምቷል
  • ጥቆማ ለኮሚቴው በግብአትነት ብቻ የሚያገለግል ነው
  • የጠቋሚ ብዛት ለዕጩነት መመረጥን አያመለክትም፤ አንድ አባት በአንድ ሺሕም ተጠቆመ በአንድ ሰው ያው ጥቆማ ነው፤ ዕጩው የሚለየው በፓትርያሪክ መመዘኛ መስፈርት በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ውሳኔ ነው፡፡
  • ምርጫው ዓለማዊ ሳይኾን እግዚአብሔርንና የእግዚአብሔርን ሕዝብ ለማገልገል የሚካሄድ የቤተ ክርስቲያን ምርጫ በመኾኑ ከምንም ዐይነት ተጽዕኖ የጸዳ ነው ተብሏል
  • ሰባክያነ ወንጌል በዐውደ ምሕረት ካህናትንና ምእመናን ለዕጩ ጥቆማ እንዲቀሰቅሱ በመደረጉ፣ ሚዲያውም በማገዙ በዚህም መሠረት የነቃ ተሳትፎ በመታየቱ ጥቆማው ለአዲስ አበባ ብቻ ነው የተሰጠው የሚለው የተጋነነ ነው
  • ዕጩዎች በሕዝብ ጥያቄና አስተያየት የሚተቹበት የ15 ቀን ጊዜ እንዲታጠፍ የተደረገው ምርጫውና ሢመቱ በጾም ውስጥ እንዳይካሄድ፣ ጊዜውም ተራዝሞ ቤተ ክርስቲያኒቱ ያለአባት ለተጨማሪ ጊዜ እንዳትቆይ አስመራጭ ኮሚቴው አዘጋጅቶ ለቋሚ ቅ/ሲኖዶስ ባቀረበውና ቋሚ ቅ/ሲኖዶስ በምልአተ ጉባኤው በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ባጸደቀው ልዩ ፕሮፖዛል መሠረት ነው፡፡
  • ትክክለኛው የመራጮች ቁጥር ከ800 በላይ ሊደርስ ይችላል፤ ኮሚቴው በቃለ ጉባኤ ወስኖ በቀጣይ ያስታውቃል፡፡
  • የስድስተኛው ፓትርያሪክ መራጮች ቁጥር ከዚህ ቀደሙ የላቀ እንደኾነ መገለጹ በሦስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ ከተሳተፈው 1133 መራጭ አንጻር ጥያቄ ተነሥቶበታል
  • ‹‹ወደ ምርጫው የተገባው ዕርቀ ሰላሙ ተዘግቶ አይደለም፤ እርሱ እንደቀጠለ ነው፡፡››
  • የጋዜጠኞችና የሚዲያ ተቋሞቻቸው በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የሚያሳድሩት ተጽዕኖ ሊገታ እንደሚገባው ዐቃቤ መንበሩ አሳስበዋል –‹‹ጋዜጠኞች በሞያቸው ሞጋቾች ቢኾኑም ጠበቃም እንዲኾኑ ያስፈልጋል፡፡›› /ዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪክ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል/
የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
Source: http://haratewahido.wordpress.com/

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment