Thursday, November 6, 2025

የጸሎት እና የምኅላ መርኅግብር በዋሺንግተን ዲሲ ማርያም ቤተክርስቲያን ተጠርቷል


በመላው ዋሺንግተን አካባቢ ለምትገኙ ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ በነገው እለት ማለትም November 7, 2025 at 5:00 pm ጀምሮ በደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን በምሥራቅ አሩሲ አባባቢ ለተጨፈጨፉት በመንግሥት መር እሥላማዊ አክራሪዎች ደማቸው ለፈሰሱት ንፁሐን ኢትዮጵያውያን ኦርቶዶክሳውያን የጸሎተ ፍትሃት ይደረጋለ ተብሎ መረጃው ደርሶናል፤ ይሄንንም ዜና በአካባቢው ለሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ለማድረስ ለዝግጅት ክፍላችን በተላከልን መሠረት ለማዳረስ እና ለማስታወስ እንወዳለን፤ ዛሬ በኢትዮጵያ ሃገራችን በተለይ አሩሲ ላይ የደም ጎርፍ ሃገሪቷን እያጠባት ነው፤ ቤተክርነቱም ቤተምንግሥቱም ትንሽ እንሰሳ እንኳን የሞተባቸው አይመስልም በሚያሳዝን መልኩ
እነዚህ የቤተመንግሥቱም ይሁኑ የቤተክርነቱ ሰዎች ይሄው የሚጨፈጨፈው ኦርቶዶክሳዊ ነው ለቤተክህነቱ አሥራት በኩራት፣ ሙዳየ ምጽዋት በማለት ይከፍላል፤ ሲሞት ግን ፍትሃት እንኳን አያደርጉለትም በእጅጉ ይዘገንናል።
ቤተመንግሥቱም ቢሆን ይሀው የሚገደለው ሰው ነው ታክሱን የቄሳርን ለቄሳር እያለ ግብሩን እየከፈለ የሚኖረው ፤ ነገር ግን ሲጨፈጭፉት እና ሲያስጨፈጭፉት እንኳን ትንሽ ሃዘኔታ ወይም ትንሽ ሪሞርስ የላቸውም ፤ አንድ ቀን ዓለምም ሕዝምብ ይፋረዳችኋል የጊዜ ጉዳይ ነው፤





የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment