እንደ ህልም በእዛች በተረገመች ምሽት የተደረገውን አሰቃቂ ግድያ ታስታውሰዋለች።
3 ወንድም እህቶቿን ፣እናቷን እና ሌሎች ቤተሰቦችን ጭምር ይዘው ከእነከብታቸው ስም አልባ የሞት አበጋዝ የሆኑ ታጣቂዎች
ነድቷቸው ከአንድ ጫካ ላይ ወስደው አሳረፏቸው።
| ልጇን የምትቀብር እናት እንዴት ትዘን? |
ነድቷቸው ከአንድ ጫካ ላይ ወስደው አሳረፏቸው።
ከመኖርያ ቤታቸው አርቀው ጫካ ላይ ከወሰዱ በኃላ ሁሉም እንዲንበረከኩ አደረጉ። በያዙት መሣርያ ያለርህራሄ አርከፈኩባቸው ።ከተስማው የመሣርያ ጥይት ድምጽ በኃላ ሁሉም ጸጥ አሉ።
ከጸጥታው ውስጥ ግን የሚጣጣር እና የሚያቃስት ሰው ድምጽ በትንሽ በትንሹ ይሰማል። እንደ ቤተሰቧ ይህቺ የ8 ዓመት ህጻን በትከሻዋ አከባቢ እና በጎድኗ በኩል ሁለት ጥይት በስቷት አለፈ።
በአፈሙዝ ያልሞቱትን በገጀራ ለመጨረስ ሁሉንም መከታተፍ ጀመሩ። ይህችንም ህጻን ልጅ መሃል አናቷን ሰነጠቁ። በጎድኗ እና ትከሻዋ በኩል ዘልቆ ከገባው የመሣርያ ቀለሀ በተጨማሪ ሰይፍ ለእዚህች ህጻን በአናቷ ታዘዘላት።
ይህን ድርጊት ከፈጸሙ በኃላ ታጣቂዎች ከስፍራው ሄዱ።ይህች ህጻን ግን ከትንሽ ደቂቃ በኃላ ገላዋ በደም ረስርሶ ነቃች። ባልጠነከረ የስምንት ዓመት ገላዋ ላይ የገባው ቀለሃ እና ሰይፍ ድምጽ አውጥታ አስለቀሳት።
በመሣርያ ተመተው በቆንጨራ ተጨፍጭፈው ከወደቁ አስክሬኖች መሃል የእዚህች እናት የልጇን ድምጽ ሰማች። በተኛችበት ወደ እርሷ ስባ "አታልቅሺ ድምጽሽን ከሰሙ መጥተው ይገሉሻል ዝም በይ " አለቻት።
በእዛ ድቅድቅ ጨለማ እና ጫካ ውስጥ ልጅ የእናቷን ትዕዛዝ አክብራ ከህመሟ ጋር ዝም አለች። ከትንሽ ደቂቃ በኃላ ግን ህጻኗ እናቷ ዳግም እንድታናግራት ለመሞከር ስትጥር ምንም መልስ አትሰጥም። ሞት አጅሬ ወስዳቷል።
ጥዋት ላይ ከእስክሬን መሃል ተነስታ ወደ ህክምና ተወሰደች። እናቷን እና 3 እህት ወንድሞችን በእዛችን ቀን በሞት ተነጠቀች። ይህን መርዶ የሰማው አባቷ ጻዲቁ ኢዮብ አይደለም እና " እርሱ ሰጠ እርሱ ነሣ" ብሎ አምላኩን ማመስገን አቃተው። አማረረ። ማማረር ብቻ ሳይሆን ጨርቁን ጥሎ አበደ። የልጆቹ እና የሚስቱን አስክሬን እንኳን በክብር ሳይቀርብ ጨርቁን ጥሎ አበደ። እጆቹን ለሰንሰለት ዳረገ።
የቀሩት የሟች ቤተሰቦች ተከፋፍለው የቤተሰቦቻቸውን አስክሬን ወደ ቀብር ህሊናውን የሳተውን የሟች ልጆች አባት እና የእናታቸው ባል የሆነው አባወራውን ወደ ጸበል ይዘው ሄዱ።
ይህ በእኛ ትውልድ መሃል የተፈጠረ ነፍስ ድረስ ዘልቆ የሚሰማ አሰቃቂ ታሪክ ይህ ነው ። ከጭፍጨፋው በኃላ ሁሉም የአከባቢው ኦርቶለታሪክና ለትውልድ ይቀመጥ።😭😭😭😭😭😭
Kune Demelash kassaye -Arba Minch
No comments:
Post a Comment