Wednesday, November 5, 2025

በመላው ዓለም የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ኦርቶዶክሳውያን፤ ሙስሊም፣ ፕሮቴስታንት፣ እና ካቶሊካውያን በእምነትም ያለእምነትም የምትኖሩ በሙሉ ኢትዮጵያውያን

የተወደዳችሁ የኢትዮጵያ ልጆች ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች፣ ፕሬቶስታንቶች፣ ካቶሊኮች፣ እንዲሁም እምነት ያላችሁ ወይም የሌላችሁ፤ ሁላችንንም አንድ የምታደርገን ሃገራችን ኢትዮጵያ በእጅጉ ሕመም ላይ ነች፤ ህመሟንም ሁላችንም ሳንረዳ አንቀርም እናውቀዋለን፤ እንረዳዋለን፤ ዛሬ በኢትዮጵያ የብዙ ኢትዮጵያውያን ደም በእብሪተኛው ዓብይ አሕመድ ጦር፣ በአክራሪ እስላማውያን፣ አክራሪ የሃይማኖት ሰዎች ብዙ ኢትዮጵያውያን በሚያውቁትም በማያውቁትም ክቡር ሕይወታቸው እየተቀጠፈ ይገኛል፤ ይሄንን ዜና ለማንችንም ዜና እንዳልሆነ እንረዳለን፤ ነገር ግን ማንኛውምይ የሃይማኖት ተቋም ይሄንን ግድያ እና ደም መፍሰስ በጎን ቁጭ ብለን ከመታዘብ ባሻገር ለማስቆም ወይም ለማስታገስ ጥረት ስናደርግ አንታይም፤ 

ባለፈው ሳምንት የእስምና መሪዎች አንድ መግለጫ አውጥተው ተመልክተናል፤ ነገር ግን ለበጣ በሚመስል መልኩ የእስልምና እምነት ተከታዮችም ተገድለዋል እና የእነሱንም ነፍስ ይማር በሚል ጩኸቴን ቀሙኝ በሚመስል መልኩ ሞታችንን ሲያቃልሉ ተመልክተናል ይሄ አያቀባብረንም፤ ኢትዮጵያ ለሁላችንም የምትበቃ ሃገር ሆና ሳለ አሁን በአሩሲ ያሉ ጂሃዲስት እጅግ በሚዘገንን መልኩ የክርስቲያኖችን ሕይወት ዘወትር ሲቀጥፉ እየታዩ ነው፤ ፦


 በገዛ አገራችን የመከራ ጅራፍ እየተገረፍን እንገኛለን፤ ይሄ ደግሞ አይቀጥልም ፤ በአንድም ወይም በሌላ ይሄ ከፋፋይ እና ጽንፈኛ (የብልና ስብስብ) ሥልጣን ይዘው አይቀጥሉም፤ ምክንያቱም ጽዋም ትሞላለች፤ ሕዝብ በነጻነት ሰርቶ የማይኖርበት ሃገር፣ በነጻነት የማምለክ ነጻነታችን ተነፍጎ፣ በነጻነት የምንተንፍስበት ሃገር እንድትኖረን የሁሉም አገር ወዳድ ሃይሎች ፍላጎት እንደሚሆን እገምታለሁ፤ በዚህ ደግሞ ሊቀጥል አይችልም በምንም መልኩ አሁን በያዝነው መንገድ ሄደን እንቆያለን ለማለት ያዳግታል፤ በርካታ ንጹሐን ክቡር ነፍሳቸውን ሰውተዋል፤ ከጨቅላ ሕጻናት እስከ አረጋውያን አባቶች ድረስ አንገታቸው ተቀልቷል፣ ሰውነታቸው ለአሞራ ተሰጥቷል፣ እጅ እግራቸው ተቆራርጦ ለአራዊት ተሰጥቷል፣ ተፈናቋል፣ ተሰዷል፣ በግድ ሃይማኖት እንዲቀይሩ ተደርገዋል፣ ገሚሱም በግድጅ የአክራሪ እስልምናን እንዲጋቡ እና ለተደጋጋርሚ መደፈር ተዳርገዋል፤ ይሄ ጭካኔ እና አረመኔነት አያኗኑረንም፤ 
በሃገራችን ኢትዮጵያ የምትኖሩ በተለይ ኢትዮጵያን የምትወዱ የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ ፕሮቴስታንቶች፣ ካቶሊክ እና ኦሮዶክሳውያን በሙሉ በአንድነት እነዚህን አራሙቻ ከሃገራችን ከምድረ ገጽ አስወግደን ሁላችን ተዋደን እና ተከባብረን የምንኖርባትን ኢትዮጵያን በጋር እንድንገነባ በአክብሮት እንጠይቃለን። 
አሁን እየሆነ ያለው በዚህ ከቀጠለ ሁሉም ነገር ከልክ እያለፈ ነው፤ አሁንም ጊዜ አለ አሁንም የማርያም መንገድ እንለዋለን ለመላው ሰላም ወዳድ ሃይሎች የሰላም መንገድ ሰጥተናል፤ በዚህ ከቀጠለ እና የንፁሃን ደም እየፈሰሰ በዚህ ከቀጠለ መጨረሻችን የሚያምር አይመስለንም፤ እርስ በእርሳችን ስንጫረስ ለጠላት ደስታ እንደሚሆን የሚታመን ነው፤ 
 በተለይ የእስልምና እምነት ተከታዮች መሪዎቹን ብትመክሯችው፤ ኢትዮጵያ በጋራ የምንኖባት ሃገር እንድትሆን የሁሉም ሰላም ወዳድ ሃይሎች ፍላጎት ነው፤ ስለ ሰላም ብለብ ብዙ ነገር ሆነናል፣ ብዙ ሆኖብናል ነገር ግን በዚህ ከቀጠልን በፈጣሪ ስም ይሆኑባችሁ የሚቀጥለው ነገር ጥሩ አይሆንም፤ ቀርብ ብላችሁ ብትመረምሩ ሁሉም፣ መንግሥትን የሚመሩትን ጨምሮ -- ውጭ ገብ ተላላኪዎችና የባእዳን አስተምህሮ አእምሮአቸውን ያላሸቀባቸው ጥቂቶች ናቸው።

1) ከእስልምናው ጂሃዲስቱ #የዉሃብያ መረብ
2) ከክርስትናዊ #ተረፍ-ናዚ የጀርመን ክርስትና ጽሎት ቤት ጭንጋፍ ኦነጋዊ
3) ከትግራይና ኤርትራ  በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና በምእራባውያን የስለላ ድርጅቶች ተጠፍጥፈው የተሰማሩ  የባንዳ ልጆች  #ሐውሃትና ሻዕብያ
4) ከተልያዩ ርእዮቶች #የ60ዎቹ ጭፍን ገልባጭ አርክሲስት ነኝ ባይ ድርጅቶች በሙሉ
5) የብሄር #ነጻ አውጭ ነኝ ባይ "ምሁር"
6) የሚያስቃዠው፣ ከስው በላይ ቁስ የሚበልጥበት  #የብልጽግና ወንጌል የሃይማኖት መንግሥት መሪው #አብይ አህመድና ተክታዮቹ
7) በኦሮቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የመሸገው ከላይ ከ 1 እስከ 6 የተዘረዘሩት የአገር እንግዶችና የነባርነታችን ጠላቶች እየወከሏቸው ያሰለፏቸው፣ #የጥምቀት ልጆችን በጎሣ #መከፋፈል የፈቀዱ ብቻ ሳይሆን ያመቻቹ #ጳጳሳትና #ህናት ----

እንዚህ 7ቱም ቢደመሩ የአገራችንን ነባር እሤቶችን የሚያከብሩ ነባርነትን፣ አንድነትን፣ ፍትሕን፣ ሰባዊነትን፣ እውነትን፣ ሰላምን ከሚሹት ነባሮች አንጻር ቢብዙ 5 በመቶ አይሆኑም።

95 በምቶው ሕዝብ የሚሰቃየው በተደራጁ 5 በምቶ በማይሞሉ አጥፊ መጤዎች ነው።

ዛሬ ከ7ቱ አጥፊ መጤዎች መካክለ አንዱን የጽንፈኛውን ጂሃዲስት ዉሀቢያ የማጥፋት ስልጥ በአጭሩ ጽፌላችሁአለሁ። 
የበለጠ የምታውቋቸው --- በዝርዝር አስተምሩንና 95 በምቶው ሙስሊምና ክርስቲያን ጥፋቱና ለማስቆም ይግባባ!!!  

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment