| የኦሮሙማው ክንፍ |
ይወዳሉ፣ከተሞቻችንን ይወዳሉ እኛን ግን......???"
ይኽ የናዚዝም (የጥላቻ የወንጌል ) የሚሰበከው በዘር ተቋቋመው በወልዳ ዱካ ቡኦታ ማኅበር በተዘጋጀው መርሐ ግብር ላይ ነው። በአራት ኪሎ።እኝህ ሰው "ምንም ቅልቅል ዘር የሌለባቸው ተንጹህ ኦሮሞ ጳጳስ(Organic Oromo)" ተብለው የጰጰሱት ነገር ግን አንገታቸው በአክራሪ እስልምና ስለሚቀላው ኦሮሚኛ ተናጋሪ ኦርቶዶክሶች ትንፍሽ የማይሉ በአንጻሩ ደግሞ የኦሮሞ ብሔርተኝነት ዋና አቀንቃኝ ናቸው።"ድንግል ማርያም ቤዛዊተ ዓለም አትባልም "የሚል የምንፍቅና ትምህርት አስተምረው "ኦሮሞ በመሆኔ ተዘመተብኝ" ማለታቸውም የሚታወስ ነው።እኔ የሚያዝኑኝ እኝህንና መሰሎቻቸውን "አባት" ብለው እየተከተሉ የመታረጃ ቀናቸውን የሚጠባበቁ ኦሮሞች ናቸው። እባካችሁ ዘረኝነትን እየተጸየፍን በኦርቶዶክሳዊ ኅብረታችንን እንበርታ ።በልዩ ወንጌል በልዩ ትምህርት አንወሰድ። ማንም ይሁን ማን ከምሥራቅ ይምጣ ከምዕራብ፣ከሰሜን ይምጣ ከደቡብ መለያየትን፣ዘረኝነትን የሚሰብክ እንኳንስ አባታችን ኦርቶዶክስ ሊባል አይገባውም።
<< በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ፤
እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ።
ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።
አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን>> ገላ 1:6-9
አጀንዳችንን አንቀይርም
No comments:
Post a Comment