Saturday, November 29, 2025

ቆመኽ አንገትኽን ተቆረጥ

የአርሲ ሰማዕታት ደም ይጮኻል 

ዛሬ ባለንበት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መከራ የቀደመ የአስተሳሰባችን ውጤት ነው። በሃገሩ ሽማግሌ አለ፣
መንግሥት አለ ብሎ ያምናል። በዚያም ሲተዳደር የኖረ ነው። በተለይ በሃይማሞት ረገድ ብዙም የከፋ ነገር አይቶ አያውቅም። በብልጽግና ዘመን መከራ አይነቱን ከመቁጠር በዝቶ መስማት ሰልችቶናል። ሰምተን እንዳልሰማን ለመኾን እንሞክራለን። 

አኹን አስተሳሰባችን ሙሉ በሙሉ ነው መቀየር ያለበት። ነጠላ ለብሶ ከበሮ የሚያሽከረክረው እንዲኽ አይቀጥልም። ልፍስፍስ ወጣት ማምረት መቆም አለበት። አራሽ ቀዳሽ ተኳሽ ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰ መኾን። የቀደመ አባቶቹን መምሰል ግድ ይላል። 
“አትግደል” ተብሏል እያለ ቆሞ አንገቱን እንደ ሸንበቆ የሚሰጥ ጅል ትውልድ አፍርተናል። ይኽ ነው እያስገደለን ያለው። 

አትንካኝ ከነካህኝ ግን አጸፋውን እንካ ማለት ተገቢ ነው። ቀሲስ ኤፍሬም ከግላቸው ምልከታ ይሁን የትኛው ተቋም አላውቅም። እንደ ሽንኩርት ሲከተፍ ቆሞ ይሙት የሚል ሕግ የለም። 

መደረጀት የአካል ብቃት እንቅስቅሴ መማር መሳሪያን መታጠቅ ራስንም አካባቢንም መጠበቅ ለነገ የሚውል አይደለላ። በስመ አብ እያልክ የምታባርረው አይደለም። ትእቢተኛ ሰው ትኅትና አያውቅም። በመጣበት ቋንቋ ማናገር ነው። 

በኦርቶዶክሳዊነት መደራጀት ተገቢ ነው። እያለቅን አትደራጁ የለም። አዎ የኢራን ክርስቲያኖች በጣም ጥሩ ተሞክሮ ነው። ወያኔ በስልት የተማረውን ኦርቶዶክስ ነጠላ እንድ ልብስ አድርጋ አራት ኪሎን ፈቅዳለት የሚያለቃቅስ ወጣት ፈጠርን። መብቱን ጥሎ መብት ጠባቂ የኾነ የተማረ ሰው።  ታጥቦ የሚበላ እንጂ ዶሮ እንኳ በአግባብ የሚያርድ አይደለም። በአጉል መንፈሳዊነት ጠቅልለን ለሃገሩ ቀርቶ ለራሱ የማይበጅ ኦርቶዶክሳዊ ፈጠርን። ብቃት የሌለን ካህናት ተሰብስበን መቅደስ እንጋፋለን። ወይ እውቀት ወይ ሞራል የለን። 

መንግሥት ገዳይ ወጣቶችን "በሬ ሸጠህ ጠመንጃ ታጠቅ ዱላ ጣልና ታጠቅ" ሲል አንተ ደግሞ ነጠላ ለብሰኽ እዬዬዬ በል።
 ዛሬ ቋንቋ ሥልጣን የሚያሰጥ መንግሥት በሚያስመሰርትበት ሃገር ብዙኅ ኾነን መንግሥት የማንኾንበት ምክንያት ምንድነው?

ለጠላት መደራጀት መዘጋጀት መሰልጠን መታጠቅ ያኔ ትንፍሽ አይልም ወዳጄ። በመግለጫና ፍትሐት በመፍታት የሚቆም ጠላት የለም። ዛፍ ስሩ ተቆርጦ አይኔርም ይደርቃል። ቤተ ክርስቲያን ከገጠር ስትቆረጥ ከተማው ይደርቃል። ዛሬ ነው ሥራ መሥራት። 
ይኽንን አጀንዳ በተለያየ ቅርጽ ማስረዳት እቀጥላለሁ። 

ንዋይ ካሳሁን


የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment