Tuesday, November 18, 2025

ቅዱስነታቸውን በተመለከተ የሚሰማው ምንድነው?

"…ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ በቅዱስነታቸው ጤንነት ዙሪያ እንዲህና እንዲያ ሆነ እያተባሉ የሚወሩ ወሬዎችን በሰማሁ ጊዜ በቀጥታ ወደ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ

ወፎቼ ነው የደወልኩት። ወፎቼም እዚያና እዚህ ገብተው አገኘነው ያሉትን መረጃ እነሆ ጀባ ብያችኋለሁ። 

• የሆነው እንዲህ ነው ይላሉ ወፎቼ… 

"…የጥንታዊቷ፣ የቀኖናዊት፣ ሐዋርያዊቷና ብሔራዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስድስተኛው ፓትርያርክ የሆኑት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በገጠማቸው ድንገተኛ አደጋ ምክንያት በሕክምና ላይ እንደሚገኙ ታማኝ የመረጃ ምንጮቼ የሆኑት ወፎቼ ከአዲስ አበባ መረጃውን አድርሰውኛል። 

"…ቅዱስነታቸውን ለሕክምና ያበቃቸውም ጉዳይ የመረጃ ምንጮቼ እንደነገሩኝ ከሆነ "በማረፊያ ክፍላቸው ዎክ ሲያደርጉ የታጠፈ የመሬት ምንጣፍ ጠልፎ ስለጣላቸው በድንገት ወድቀው" እንደሆነ እና በዚህም ምክንያት ድንጋጤ ተጨምሮበት በአደጋው በአንደኛው እግራቸው ዳሌ ላይ ስብራት እንደረሰባቸውና በዚህም ምክንያት በሀኪሞች በተደረገላቸው ከፍተኛ ርብርብ ቀዶ ጥገና ተደርጎላቸው ሕክምና እየተከታተሉ መሆናቸውን ነው የመረጃ ምንጮቼ የሚገልፁት። በአደጋው ወቅት በተጨማሪ የአልጋ ጠርዝም ሆነ ሌላ አደጋውን ከፍ የሚያደርግ ተጨማሪ ምት ስላልገጠማቸውና ሙሉ ለሙሉ ከመሬቱ ላይ ብቻ በመውደቃቸው የደረሰባቸው አደጋ ቀላል ባይባልም ነገር ግን ለክፉ የማይሰጥ በመሆኑ በዚህ ሁለትና ሦስት ቀናት ውስጥ ወደ መንበረ ፓትርያርክ ማረፊያ ቤታቸው እንደሚመለሱም ነው የወፎቼ መረጃ የሚያመለክተው። 

"…አረጋዊው አባትና ስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በተለይም ባለፉት ጥቂት ዓመታት እጅግ ከባድ ፈተና የገጠማቸው ሲሆን "በሀገሪቱ በተፈጠረው የፖለቲካ ግጭት ምክንያት "በላይ እሳት፣ በታች እሳት ሲነድባቸው፣ በአላፊ አግዳሚው ሲሰደቡ፣ ሲገፉ መኖራቸውም በሁሉ ዘንድ ይታወቃል። በተለይም በዘመነ ብልፅግና በዳንኤል ክብረት የሚመራው የሚዲያ ሠራዊት አፉን ሲከፍትባቸው፣ እነ ታዬ ቦጋለ፣ እነ ስዩም ተሾመ፣ እነ ዘሪሁን ሙላት፣ ኢሳቶች፣ ጌትነት አልማውና ሌሎች ገሚሶቹ በሚዲያ፣ የቤተ ክህነቱ ሰዎች ደግሞ በመንበረ ፕትርክናቸው በጽሕፈት ቤታቸው ድረስ በመገኘት ቢሰድቧቸውና ቢያዋርዷቸውም እሳቸው ግን መንበሩን ለአውሬ፣ ትቼ የትም አልሄድም በማለት በመንበራቸው ጸንተው፣ ፈተናውን ሁሉ ተቋቁመው በሚያስደንቅ ትእግስት በቤተ ክርስቲያንም ሆነ በራሳቸው ላይ የመጣውን ፈተና በድል አሸንፈው እያሳለፉ የሚገኙ ቅዱስ ፓትርያርክ ናቸው። 

"…ቅዱስነታቸው በዘመነ ፕትርክናቸው ካሳኩአቸው ትልቁ ስኬቶች መካከል ከእርሳቸው ዘመነ ፕትርክና በፊት በዘመነ ኢህአዴግ ከሁለት ከተከፍሎ የነበረውን ሲኖዶስ ወደ አንድ በማምጣት፣ በአሜሪካ ስደተኛ ተብሎ ይጠራና በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ይመራ የነበረውን ሲኖዶስ ከነ ፓትርያርኩ ወደ ሀገር ቤት በመጡ፣ በተመለሱም ጊዜ በፍቅር ተቀብለው አብረው ቡራኬ በመስጠት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በእረፍተ ሥጋ ሲለዩም ቆመው አልቅሰው ቀብረው የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ተጠብቆ እንዲቆይ በባለጌዎች እየተሰደቡ፣ ለቡራኬ ሁላ ማይክራፎን እየተከለከሉ፣ የፓትርያርክ መንበር፣ ሀገረ ስበከታቸው የሆነችውን አዲስ አበባንም በእግታና ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ውጪ በጉልበት ተነጥቀው በዚያም ሳያኮርፉ፣ ሳይሸማቀቁም፣ ቂም ሳይዙ እርሳቸው ለእኛና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንደ ሻማ ቀልጠው አንድነታችንን አስጠብቀው ያስቀጠሉ አባት ናቸው። ለዚህም ታሪክም፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም አይረሷቸውም። ዘላለም ሲዘከሩም ይኖራሉ። 

"…ቅዱስነተቻው በፍጥነት በቶሎም ድነው ወደ ተለመደው የቀደመ አገልግሎታቸው ይመለሱ ዘንድ የሁላችን ጸሎት ነው።  •  አግዚአብሔር ይማርልን።  አሜን።🙏 

• ''ጸልዩ በእንተ ሊቅነ አባ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘሀገር ዓባይ ኢትዮጵያ'' (ሥርዓተ ቅዳሴ)

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment