በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሁለት ወረዳዎች በታጣቂዎች ከተገደሉት ምዕመናን መካከል አምስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት እንደሆኑና
ከዚህ ቀደምም በጀጁ ወረዳ በታጣቂዎች የታገቱ ሰዎች እንዳልተመለሱ የዞኑ ሀገረ ስብከት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ ምሽት ገልጿል።
![]() |
| ጥቂቅ ሃገረ ስብከቶች ሃዘናቸውን እና ከአርሲ ክርስቲያኖች ጋር ቆመዋል |
ከዚህ ቀደምም በጀጁ ወረዳ በታጣቂዎች የታገቱ ሰዎች እንዳልተመለሱ የዞኑ ሀገረ ስብከት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ ምሽት ገልጿል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሀገረ ስብከት በሰጠን ቃል፣ በሰሞንኛው ጥቃት መርቲ እና ጉና ወይም አባጀማ በተሰኙት ሁለት ወረዳዎች ላይ የሟቾች ቀብር መፈጸሙን ገልጿል።
ጥቃቱ የተፈጸመው ጥቅምት 13 እኩለ ሌሊት መሆኑን ገልጾ፣ " ለምሳሌ መርቲ ወረዳ ከተቀበሩት ውስጥ ከአንድ ቤት አምስት ሰዎች ተገድለዋል። ሚስትና ሁለት ልጆችን ጨምሮ " ብሏል።
ይህን ያሉን ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዲነገር ያልፈለጉ የሀገረ ስብከቱ አመራር፣ ትክክለኛውን የሟቾች ቁጠር በተመለከተ በቀጣይ አጣርተው እንደሚገልጹ ጠቁመዋል። " አሁን በደረሰኝ መረጃ መሰረት ቁጥራቸው ከፍም ዝቅም ይላል " ብለዋል።
" ሟቾች የተቀበሩበት ቤተክርስቲያን ሎሜ ሰቃ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ነው "
ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ጥቃት ደርሶ ያውቃል ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ " ይህ አካባቢ እንኳን ትልልቅ ባለስልጣናትም የወጡበት ቦታ ነውና ከፍተኛ ጥበቃ የነበረበት፣ መቻቻል መፈቃቀር ያለበት ነበር " ሲሉም አስታውሰዋል።
" እንደሌሎቹ እንደነ ጀጁ፣ ሽርካ ስጋት ያለበት ቀጠና አልነበረም። ከዚያ በፊት ወደ ግን ስድስት ሰዎች ላይ ሙከራ ተደርጓል " ሲሉም አክለዋል።
" ከጀጁ ወረዳ ታግተው የተወሰዱ ምዕመናን አሉ። የታገቱት አልተለቀቁም ከእነርሱ ውጭ ነው ይሄ የሰሞንኛው ጥቃት የገለጽንላችሁ " ነው ያሉት።
ከጥቂቅ ቀናት በፊት በምሥራቅ አርሲ የተፈጸውምን ጭፍጨፋ ዘግናኝ ተግባር ብዙ ሃገረ ስብከቶች የሃዘን መግለጫዎችን እያወጡ ነው፤ እስከ አሁን ድረስ በደረሰን መረጃዎች የሃዘን መግለጫዎቻቸውን እና ከአርሲ ሕዝበ ክርስቲያን ጋር የአላማ አንድነታቸውን ያሳዩን የሚከተሉት ሃገረ ስብከቶች ናቸው ከነዚህም ውስጥ

No comments:
Post a Comment