የብፁዕ አቡነ ይስሐቅ አርአያነት ያለው ተግባር
=========
ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ በአርሲ ሀገረ ስብከት በኖኖ ጃዊ ቀበሌ ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ ከተገደሉት ውስጥ በእግዚአብሔር
ቸርነት ለተረፈው ሕፃን 70,000 ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ ።
![]() |
| የኖላዊው አባት ብፁዕ አቡነ ይሥሐቅ አርአያነት ያለው ሥራ |
ቸርነት ለተረፈው ሕፃን 70,000 ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ ።
(EOTCMK TV ጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም)
ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ በአርሲ ሀገረ ስብከት ጉና ወረዳ በሚገኘ ኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ከሰሙበት ጊዜ ጀምሮ እጅግ ማዘናቸውን እና ለሞቱት እረፍተ መንግሥተ ሰማያት፤ ቤተሰባቸውን ላጡ መጽናናትን እንዲሰጥ ተመኝተዋል ።
ብፁዕነታቸው የሰው ልጅ ሰው ሆኖ ከመኖር ይልቅ አውሬ እየሆነ ያስቸገረበት ዘመን ላይ መድረሳችን እጅግ የሚያሳዝን ነው ብለዋል።
እርስ በእርስ እንዋደድ ዘንድ የታዘዝነውን የአምላክ ቃል ወደ ጎን በመተው ሌሊትን ተገን በማድረግ ለተፈጸመው ድርጊት ነገ እግዚአብሔር መልስ ይሰጣል በማለት መልእክታት አስተላልፈዋል።
ከእነዚህ ከተገደሉት ምእመናን ዛሬ በወላይታ ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል ሕክምናውን እየተከታተለ የሚገኘውን ዕድሜው 4 ዓመት የሆነው ሕፃን ላይ እንዲህ አይነት ጭካኔ የተሞላበትን አረመኔያዊ ተግባር መፈጸም እጅግ አስነዋሪ ተግባር ነው ያሉት ብፁዕነታቸው ቆም ብለን ማሰብና ወደ ልቦናችን መመለስ የሚገባበት ዘመን ስለሆነ ለቤተ ክርስቲያናችን በአንድነት ዘብ የምንቆምበት ጊዜ ላይ መድረሳችንን ያሳያል በማለት አፅንኦት ሰጥተዋል ።
ይህ ሕፃን በደረሰበት አደጋ ሕክምናውን አጠናቆ እስከሚወጣ ድረስ ድጋፋቸው እንደማይቋረጥ የገለጹት ብፁዕነታቸው አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግ በሀገረ ስብከቱ ለሚገኙ ገዳማት እና አድባራት መመሪያ ሰጥተዋል።
በተጨማሪም መልእክታቸውን ያስተላለፋት የወላይታ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሰላም ቀሲስ ቦክቻ ኤንጋ ዛሬ ሰማዕትነትን በተግባር ያየንበት ዘመን ነው ያሉ ሲሆን ቤተ ክርስቲያን በሰማዕታት ደም የፀናች መሆኗን በተለይ በአንዳንድ አካባቢ የሚታየው የቤተክርስቲያን የፈተና እና የሰቆቃ ዘመን መሆኑን ገልጸው ሕፃኑ ሕክምናውን እስኪያጠናቅቅ የሀገረ ስብከቱ ክትትል እና ድጋፍ እንደማይለይ ሕዝበ ክርስቲያኑንም በማስተባበር ኮሚቴ በማዋቀር በመላው ዓለም የሚገኙ ምእመናንን የዚህ በረከት ተሳታፊ በማድረግ ዝግጅት እንደሚደረግ አሳስበዋል ፡፡
ብፀዕነታቸው በሆስፒታሉ ሕክምና ላይ ላሉ ታካሚዎች ጸሎት አድርገል፡፡ በጉብኝት መርሐ ግብሩም የሀገረ ስብከቱ የየመምሪያው ኃላፊዎች የገዳማት እና አድባራት አበምኔቶች አስተዳዳሪዎች እንዲሁ በማኅበረ ቅዱሳን የወላይታ ሶዶ ማእከል ሥራ አስፈጻሚ አባላት፣ የሀገረ ስብከቱ እጨጌ ሚዲያ እና ምእመናን ተገኝተዋል።
ዘገባው በማኅበረ ቅዱሳን የወላይታ ሶዶ ማእከል ነው።
ምንጭ Mahibere Kidusan Broadcast Service -
ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት

No comments:
Post a Comment