| ታሪክ ራሱን ይደግማል! |
ቡድን ማኅበረ ቅዱሳን አጣሪ ኾኖ አለመግባቱ ነበር።
ሕወሃት ዋልድባ ገዳምን ለስኳር ልማት ፕሮጀክት ብሎ ገዳሙን ሊያነሣው ፈልጎ ማረስ ሲጀምር ከፍተኛ ቁጣ ይቀሰቀሳል። ይኽንን የነደደ ቁጣ ለማብረድ ተብሎ ከጠቅላይ ቤተክህነት፣ ከማኅበረ ቅዱሳን ከፌደሬል ጉዳዮች የተውጣጣ ቡድን መጋቢት 25- 30 ቀን 2004 ዓ.ም. ወደ ዋልድባ ይላካል። ሙሉ ወጩው የተሸፈነው በማኅበረ ቅዱሳን በኩል ነበር።
አጣርተው የመጡት ሰዎች ሪፓርት አቀረቡ። በሚዲያ የስኳር ፕሮጀክቱ ገዳሙን እንደማይነካ አሳወቀ። ማኅበረ ቅዱሳን ለኢዲቶሪያል ክፍል በሪፓርቱ ዝርዝር ያቀረበ ሲኾን አንደኛ ስኳር ልማቱ ገዳሙን ከበጎርፍ ከመጥለቅለቅ እንደሚታደገው ኹለተኛ የሚገደበው ግድብ ለገዳሙ አሳ ምርት እንደሚጠቅመው፣ ሦስተኛ ቦታው የቱሪስት መዳረሻ ለሙኾን ያስችለዋል የሚልና የስኳር ፕሮጀክቱ ጠቃሚ መኾኑን ገለጹ።
በዚኽ ምክንያት የኢዲቶሪያል ክፍል የነበረው ዲ/ን አባይነህ ካሴ እጅግ ይቆጣል። ቱሪስት ገዳም ምን ይሠራል፣ ገዳሙ የመነኮሱት አሳ ልበሉ ነው ወይ? ብሎ ይናገራል። ሰነዱ እንዳይለቀቅ ይወስናል።
አባይነህ ከስብሰባ እንደ ወጣ ሰነዱ በማኅበረ ቅዱሳን ድረገጽ ላይ ተለጠፈ። ዲ/ን አባይነህ VOA ላይ ወጥቶ ስኳር ፕሮጀክቱ ገዳሙን እንደሚጎዳ ተናገረ። ሲናገር ዲ/ን ኢ/ር አባይነህ ካሴ ከማኅበረ ቅዱሳን ኤዲቶሪያል ቦርድ ሰብሳቢ ብሎ ነበር። ይሄ ጥርስ አስነከሰበት። በማግሥቱ ከማኅበሩ ተባረረ። ዲ/ን አባይነኽ ይኽችን ጉዳይ በፍጹም ሲናገር አልሰማሁትም። ለማኅበሩ አዝኖ ወይስ ሌላ አላውቅም። አባይነህ የተገፋው በዚኽ ነው።
እኔ ደግሞ በተመሳሳይ ወቅት ይኽችን ጉዳይ ከፌደራል ጉዳዮች ኃላፊ ከአንደበቱ ሰምቻታለሁ።
ማኅበሩም ጫጫታ ሲበዛበት የለጠፋትን ዝርዝር ጥናት አነሧት። ዛሬ አለ ዜናው። ሪፓርቱ ግን የለም። ገብታችሁ እዩት። ሙሉ ዶክመንቱ እኔ አለኝ።
በዚኽ ምክንያት ብዙ ወንድሞች እኔንም ጨምሮ ብዙ ተወያየን ብናናግራቸው “መንግሥት ማኅበሩን ሊመታ ይፈልጋል” አሉን። ያኔ ቀን ከሌሊት ሕይወታቸውን ሰጥተው ከቢሮ ወጥተው ጽ/ቤት የሚያመሹ ብዙ ቁርጠኛ ኦርቶዶክሳውያን ማኅበሩን ጠለው ወጡ።
በራሳችን ቤት የምንጠቃው የጀመረው ዛሬ አይደለም። የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማትም የኾነው እንደዚያው ነው። ሲኖዶሱ ተገደልን ብሎ መግለጫ አወጣ። የራሱ የቤተክህነቱ ስብከተ ወንጌል መምሪያ ኃላፊ ወጣና “ግድያው ሃይማኖታዊ አይደለም” ፋኖ ነው ገዳዩ ብሎ ቁጭ። ታሪክ ራሱን በተመሳሳይ ትዕይንት ደገመ። ይቀጥላል ገና።
ለምን ብሎ የማይጠይቅ ትውልድ!!
ምንጭ፡ ከፍኖተ አበው ቴሌግራም የተገኘ
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም
No comments:
Post a Comment