Monday, November 10, 2025

ከቤቲ ወ/ሐዋርያ ፌስቡክ ገጽ የተወሰደ ........


'ዘማሪ' ቴዎድሮስ ዮሴፍ (በስም የጠቀስኩህ የፖስቱ ስክሪን ሻት እንደሚደርስህ ስለማውቅ ነው!) ምናልባት ዕውቀቱ ከሌለህ በኮ'ሚኒስታዊ
ዘማሪ ቴዎድሮስ 

ሥርዓት ዘመን በራሽያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን.....የሀገሪቱ ኦርቶዶክሳውያን ቤተ ክህነታቸው ውስጥ የነበሩ በሞታቸውና በተነፈጋቸው መብት ሲሳለቁ የነበሩ የገዛ ጳጳሳት ነን ባዮቻቸው ላይ ምን እንዳደደረጉ ገለጥ ገለጥ አርገህ ማንበብ ነው!
በዕርግጥ እኔ ''ሰው አርገኝና ሰው ይግረመው'' የሚልን ዘፈን መዝሙር ነው ብሎ ካወጣ ዘማሪ ነኝ ባይ ከዚህ የተለየ የረቀቀ ሀሳብ ብዙ አልጠብቅም..... ለዩቲዩብ ቪው ማድመቂያነት ካልሆነ በስተቀር በቀራንዮ ተሰቅሎ ወደ ሰውነት ክብር የመለሰን ዓምላክ ፊት እንዴት ይሄንን የረከሰ ወሬ የምስጋና መስዋዕት ነው ብለን ልናቀርብ እንችላለን??? ''የአጋዘን አስተሳሰብ ስላለኝ ወደ ሰውነት መልሰኝ'' ከሚል የግል ምኞት ለይቼ አላየውም!!
ለማንኛውም:-
የቤተሰብ ሙሉ አባላትን ጨምሮ ብዙ ኦርቶዶክሳውያን በሚሰቀጥጥ ሁኔታ በገ*ጀራ ሲታረዱና በጥይት ሲጨፈጨፉ፣ አንድ ነፍስ ያላወቀ የ4 አመት ህፃን ልጅ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን በመሆኑ ብቻ በጥይትና በገጀራ ሙሉ ቤተሰቡ ተጨፍጭፎ ተገ*ድሎ..እሱ በተዓምር ቢተርፍም በዚሁ ጭፍጨፋ በደረሰበት ጉዳት በህፃንነቱ ሊቦርቅበት የሚገባው

እግሩ ሲቆረጥና በዚሁ ምክንያት ከምዕመናን መቀነት በሚፈታ የሙዳየ ምፅዋት ገንዘብ የሚተዳደር ቤተ ክህነት ውስጥ ያሉ 'ጳጳሳትን' ስለምን በሞታችን ላይ ዝምታን መረጣችሁ ብሎ መውቀስ ጥፋቱና ስህተቱ ምንድን ነው?! ቢያንስ አፍህንን መዝጋት እና ድምፅ መሆን ባትችል እንኳን ይሄንን የሚጠይቁ እህትና ወንድሞችን ለመንቆር ያገኘኸው ድፍረት አጃኢብ ያሰኛል!
ቢያንስ ክርስቶሳዊ ወንድማዊነቱ ከልብህ ቢፋቅ እንኳን ኦርቶዶክሳዊ የመዝሙር አልበም አወጣሁ ስማልኝ የምትለው ህዝብኮ ነው..... በኦርቶዶክሳዊነቱ እየተጨፈጨፈ ያለው... እንዴት ጭንቅላትህ ቢደፈን ነው ከጨፍጫፊዎቻችን እኩል በሞታችን ላይ የምትሳለቀው??

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment