፩. በኦርቶዶክሳውያን ላይ የጥቃት አድራሹ አካል ከመንግሥት ጋር በመናበብ የሚሠራው ጠቅላይ ቤተ ክህነት እና ሲኖዶስ ስለሆነ
ለችግራችን ምንጭ አድርጎ በመቁጠር ድምጽ ማሰማት።
ለችግራችን ምንጭ አድርጎ በመቁጠር ድምጽ ማሰማት።
፪. የጠቅላይ ቤተ ክህነት ወይም ቋሚ ሲኖዶስ በአስቸኳይ ጉዳቱ ወደ ደረሰበት አካባቢ በመሄድ ወገኖቻችንን እንዲጎበኝና እንዲያጽናና መጠየቅ።
፫. በጉዳቱ አካላቸውን ንብረታሸውን ላጡ ወገኖቻችን አስቸኳይ እርዳታ እንዲያደርግ መጠየቅ።
፬. በጉዳቱ ሰማእትነት ለተቀበሉ ወገኖች ጠቅላይ ቤተ ክህነት ለአረርቲ ክርስቲያኖች እንዳደረገው ጸሎተ ፍትሐት እንዲያደርግ በተመሳሳይ ቀን በሁሉም አድባራት እንዲደረግ ጥያቄ ማቅረብ።
፭. ሁሉም አህጉረ ስብከቶች ለዚህ ጉዳት መግለጫ እንዲሰጡ መጠየቅ ካልሆነ ከገዳያችን ለይተን አናያቸውም።
፮. በቀጣይ ይህ ችግር እንዳይከሰት መፍትሔ የሚለውን በአስቸኳይ በዝርዝር ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ እንዲያሳውቅ።
፯. በአርሲ ሃገረ ስብከት በተደጋጋሚ ከፍተኛ ተጋድሎ ሰማእትነት የተቀበሉ የሰማእታት ልጆች ሕጻናት ቤተክህነቱ ተቀብሎ በማሳደጊያ እንዲወስዳቸውና እንዲያሳድግ መጠየቅ።
ንዋይ ካሳሁን
No comments:
Post a Comment