=====
(EOTCMK TV ኅዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም)
ዛሬ ኅዳር 01 ቀን 2018 ዓ.ም ልዩ ቦታው ጠለታ ቅዱስ ገብርኤል በተባለ አካባቢ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ገደማ ሦስት ኦርቶዶክሳውያን በአውድማ ላይ እህል እየወቁ ባሉበት በጥይት ተደብድበው በግፍ መገደላቸው ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመላክታል ።
ከተገደሉት ምእመናን መካከል ዲ/ን ኢዮብ እጅጉ፣ ጥላሁን ቦጌ እና ሕፃን ጻድቃኔ ሠራዊቱ የተባሉ ኦርቶዶክሳውያን ይገኙበታል ።
ሥርአተ ቀብራቸው በጠለታ ቅዱስ ገብረኤል ቤተክርስቲያን ዛሬ ኅዳር 01 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ላይ ተፈጽሟል።
በተጨማሪም ከዚህ ቀደም በነበሩ የኦርቶዶክሳውያኑ አፈናና ግድያን በተመለከተ መረጃ አቀብላችኋ በሚል ምክንያት የአካባቢው ወጣት ምእመናን ወዳልታወቀ ሥፍራ ታስረው እየተወሰዱ እንደሚገኝ ምእመናኑ ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
በሥፍራው ላይ የጸጥታ ሓይል ቢኖርም ኢ-ሰብአዊ ድርጊቱ ፣ አፈናና ግድያውም ተባብሶ መቀጠሉን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።
ስለጉዳዩ ተጨማሪ መረጃ ለመጠየቅ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን መዋቅር ወደ ሆነው የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ እና የዞኑ የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ የእጅ ስልክ ላይ በተደጋጋሚ ብንደውልም ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአሁኑ ሰዓት ሴቶች እና ሕጻናት አካባቢውን ለቀው ወደ ሌላ ቦታም እየሸሹ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያመላክታል።
ከማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስቲንግ አገልግሎት የተገኘ
No comments:
Post a Comment