Wednesday, November 19, 2025

" ሦስት ዓመት ተከራክረን በፍርድ ቤት ያስወሰንነውን ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ወረዳው ለመክፈል ፈቃደኛ አልሆነም " - ጤና ባለሙያዎች

ውዝፉን በአንዴ ለመክፈል በጀት የለውም ወረዳው " - የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ 
የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ጥያቄ


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ሃላሌ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ያሉ 128 ጤና ባለሙያዎች በፍርድ ቤት የወሰነላቸው #ከ3_ሚሊዮን ብር በላይ የትርፍ ሰዓት ክፍያ እንዳልተፈጸመላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

ጤና ባለሙያዎቹ ምን አሉ ?

" ወላይታ ዞን ሃላሌ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለሶስት ዓመት ሙሉ ተከራክረን በፍርድ ቤት ያስወሰንነውን 17 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ወረዳው ለመክፈል ፈቃደኛ አልሆነም።

መንግስት ካሳ ጭምር ከፍሎ ወደ ስራችን መመለስ አለበት፤ ውዝፍ ገንዘባችን የቆየ እንደመሆኑ መጠን ከሦስት ዓመት በፊት ከነበረው ዶላር ምንዛሪ እና አሁን ያለውን ታሳቢ በማድረግ ይከፈለን።

ፍርድ ቤቱ የወሰነልን 3 ሚሊዮን 371 ሺሕ 424 ብር ነው 500 ሺሕ ብር ታግዶ በሆስፒታል አካውንት እንዲዛወር ታዟል። እንዲሁም ከቀሪው 2 ሚሊዮን 871 ሺሕ 424 ብር ከሰኔ 2017 ዓ/ም ጀምሮ 300 ሺሕ ብር በየወሩ ሳይተላለፍ በሆስፒታል አካውንት እንዲዛወር ፍርድ ቤቱ አዟል።

ሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ/ም ነው። ነገር ግን የተወሰነ ከፍለው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ባለማክበር ጤና ሚኒስቴር ይከፍላል፤ በሚል ለተከታታይ 4 ወራት አልከፈሉም። ጠቅላላ በፍርድ ቤት የተወሰነልን 4,151,330 ነው። የሁለት ወር ተከፍሎ 3,371,424.65 ነው ቀርቷል " ብለዋል።

ኃላፊዎች ምን አሉ ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታ ምላሽ የጠየቃቸው የሃላሌ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ማቲዎስ መንገሻ፣ " አዎ። ገንዘቡ አልተከፈላቸውም " ሲሉ አምነዋል። ተጨማሪ ማብራያ ከመስጠት ፋንታ ግን አቋርጠው ስልክ ዘግተዋል ፤ በድጋሚ ሲደወልም ስልክ አያነሱም።

ወረዳው ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ ባይሆንም ስለጉዳዩ የጠየቅናቸው የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ አቶ ፀጋዬ ኤካ፣ " የተወዘፈውን አልከፈለንም ካሉ ወረዳው 'እከፍላለሁ' የሚል ቃል ቢገባም አንዴ ለመክፈል ተቸግሮ ሊሆን ይችላል። ግን ቀስ በቀስ እየከፈለ ስለሆነ ይከፍላል " ብለዋል።

" ወረዳው መክፈል በሚችልበት አቅም እየከፈለ መጥቷል። አሁንም ቢሆን ባለሙያዎቹ የሰሩበት ህዝቡ አገልግሎት ያገኘበት ስለሆነ ይከፍላል" ያሉት ኃላፊው፣ "ባለሙያዎቹ በጊዜው ተስማምተዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ለወደፊት ግን የትርፍ ሰዓት ክፍያን በሰሩበት መጠን ያለ ውዝፍ እከፍላለሁ ብሎ እስካሁን እየከፈለ መጥቷል። ውዝፉን ግን በአንዴ ለመክፈል በጀት የለውም ወረዳ። እነርሱም ታግሰው ቀስ በቀስ የሚፍለውን እየወሰዱ በትዕግስት እንዲጠብቁ ነው በጊዜው የተስማማነው። ፍርድ ቤት ወስኗል። ወረዳውም እየከፈለ ነው። አልከፍልም አላለም እነርሱም በትዕግስት ቢጠብቁ ተሻለ ይሆናል " ብለዋል።



የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment