በትላንትናው እለት በክርስቲያኖች ደም በጨቀየችው በደም ምድሯ አርሲ ሌሎች አምስት ክርስቲያኖች ተጨፍጭፈዋል፤ የሚሰማም
መንግሥት የለም፤ የሚናገር አባትም የለም፤ የእምነቱ ተከታዮች እንኳን በትንሹ እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው በአሁን ጊዜ፤ ነገር ግን ከቤተ መንግሥቱም ሆነ ከቤተ ክህነቱ በኩል ምንም አይነት ነገር እንዳልተፈጠረ በሰላም እና በመረጋጋት ላይ ናቸው ፤ ይሄ ደግሞ ለአንድ ሃገር ሰላምዊ የሆነ የሕዝቦች የኑሮ እና የቀን ተቀን ማኅበራዊ መስተጋብር ጭምር በእጅጉ ፈታኝ የሆነ ሁኔታ ተፈጥሮ እያለ ፤ ነገር ግን መንግሥታችንም ሆነ የቤተ ክህነቱ ተጠሪዎች የዶሮ ነፍስ እንኳን የጠፋ በማይመስል መልኩ ዝምታቸውን ቀጥለዋል፤ ክርስቲያኖችስ በዚህ መጠን እየተጨፈጨፉ ዝምታን መምረጥ ነገ ክርስቲያኖች አባቶቻችን ብለው ሊነሱ ወይም አብረዋቸው ሊቆሙ የሚችሉበት ሁኔታ ይኖራል? ግብረ መልሱ በእጅጉ አስደንጋጭ እና አስፈሪ እንደሚሆን ከወዲሁ መገመት አያዳግትም፤
| ሲኖዶስ እና የንፁሐን ግድያ |

የራሳችን የሚባሉ አብቶች ቢያንስ እኳን ዘለላ እንባ ማፍሰስ ቢያቅታቸው ወጥተው ማጽናናት ማንን ገደለ? ተነስተው ግደሉ እንዲሉ አንጠብቅም ነገር ግን በጸሎታቸው በአደባባይ ወጥተው ይሄ ግድያ ወደአልተፈለገ ነገር ውስጥ እንዳይወስደን በማለት ለምን አልተናገሩም፤ የነገው ሁኔታ በእጅጉ ያሳስባል አሁን ላይ እየሆነ ያለው ፤ እርግጥ ነው እያንዳንዱ ግድያ እና ጭፍጨፋ በመንግሥት በሚሰጡ መመሪያዎች እንደሆነ ብዙ ነገሮች ግልጽ እየሆኑ ነው፤ የሕዝበ ክርስቲያኑ ምላሽ ቆይቶ ጥሩ ላይሆን እንደሚችል የተገነዘቡት አልመሰለንም፤ ይሆነ ሆኖ ነገን የምናየው ነው፤ ነገር ግን ዛሬ ላይ እያለቅን ነው ብለን እንኳን እንድንጮች ጥሪያችንን እናቀባለን።
" በአርሲ መርቲ ወረዳ የሚኖሩ 5 ኦርቶዶክሳውያን ተገድለው ፤ 3 ምዕመኖቼ ታግተው ተወስደዋል " ነው ያለችው።
" ግድያው እና እገታው የተፈጸመው በትናንትናው ዕለት ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጋዶ ቀበሌ ነው " ብላለች።
" 5 ምእመናን የእርሻ ሥራቸውን አጠናቀው ምሳቸውን እየበሉ ባሉበት ጊዜ ነው በታጠቂዎች በተከፈተባቸው የተኩስ የተገደሉት " ስትል አክላለች።
ሥርዓተ ቀብራቸው በአቦምሳ ከተማ በሚገኘው በደብረ ገነት ትንሣኤ ብርሃን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን እንደተፈጸመ ገልጻለች።
የታገቱት 3 ምእመናን እስከ አሁን የደረሰቡት እንዲሁም ያሉበት ሁኔታ አይታወቅም ብላለች።
" ይህን የምእመናኑ የግድያ እና የአፈና ተግባር ከሰሞኑ በሀገረ ስብከቱ እንደነበረው ሁሉ ተባብሶ የቀጠለ ነው " ያለችው ቤተክርስቲያኗ " በተለይም ላለፉት ሁለት ዓመታት የገጠር ቀበሌው እና በውስጡ የሚኖሩ ምእመናን ከስጋት ነጻ ሆነው ኖረው አያውቁም " ስትል አሳውቃለች።
No comments:
Post a Comment