Sunday, November 16, 2025

አባ!!! ምን አሉ? ልናሻግራችሁ ነው ወይስ አስክሬናችሁን ረብርበን ልንሻገርባችሁ? እስቲን ይድገሙት።

ስንት ዓመት ነው የምትቀልዱት? ከደርግም፣ ከወያኔም፣ ከኦነግም፣ ከብልጽግናም ጋር ተቃቅፎ  ተራ በተራ እየተኙ ዘመናትን 
ማስቆጠር ለክርስቶስ ምስክር ያስብላል? ባይሆን  እንኳንስ "እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ" የሚለውን ይዞ የመጋደል የአዲስ ኪዳን ፍጹምነት ለፍጥረታዊ ሰው የተሰጠውን አታመንዝር የሚለውን ኦሪታዊ ቃል ሻራችሁ አያድንም?

ለነገሩንእኮ ---
ራሱም ያልተሻገረ ግለሰብና ስብስብ ማንንም ማሻገር አይችልም!!!

ቤተ ክርስቲያንን ለማሻገር መጀመሪያንወደንክርስትና መሻገር የሚጠይቀውን የምንኩስናንተጋድሎንፍንጭ አሳዩ! 

የሌባ ዓይነንደአቅ መልሶ ልብ ያውልቅ ይላሉ እአበው እመዎቻችን።

ፈሪሃ እግዚአብሔር ቢቀር ሚሊዮኖችን የሚያፍር ህሊና ወዴት ተሰወራችሁ???

ቤተ ክርስቲያን ማለት ምን ማለት ነው?

የጥምቀት ልጆች አንድነትም አይደል?

በቀኖና ሐወርያትብጸንቶና የክህነት ውስን ጠብቆ በመቀጠልም አይደል?

ዓለምን በናቁናንክርስቶስን ለመዋሃድ በሚናፍቁ መነኮሳት አባትነትና አርአያነት አምላክን መምሰልናንመምራትም አይደል?

በጥምቀት ተወልዶ ከጎሣና ዓለም ተላቅቆ መልእክትን በመምሰል አንድ የክርስቶስ ዘር መሆንም አይደል?

የምንኩስናን ትርጉም ሳይማሩናንሳያምኑበት ነኮሳት፣ ፤ የቤተ ክርስቲያንን ትርጉም ሳይረዱ የጰጰሱ  ተጋድሎ የማይመለከታቸው ነገገሥታት ምን እያሉ ይሆን???  "መንግሥት ጋር በመግባባት?" ትርጉም ይገርማል።

ከመንግሥት ጋር መግባባት በሲኖዶስ ላይ አምጾ  ወንድ አዳሪን የቡና ቤት አምንዝራና ዳንሰኛ ሳይቀር በአብይ ትዕዛዝ ሽመልስ የገዛውን የግሪክ ጨርቅ አልብሶ ጳጳስ እንኩ ማለት ፣ ይህን የማይቀበለውን ማስግደል ነው ማሻገር?

 የጥምቀት ልጆችን በዘር ተካፍሎ ከሚያጫርሰው ፖለቲካ  ጎን ቆሙው እነርሱም የጎሣ ጳጳሳት አየሾሙ፣ አንድን የክርስቶስ አካል ብልቶች በመከፋፈል፣ እያሳረዱና እያስፈናቀሉ የተረፉትን ደግሞ  እየሸለትን  መቀጠል  መቻላችን  ማሻገር ይባላል እያላችሁ ነው

ከወለጋ እስከ አርሲ ማሳርድ ነው ማሻገር? 

 እኛ በድሎት የምንቀጥልበት ስልት ሁሉ  "ቤተ ክርስቲያን ተሻገረች" ያሰኛል?

ቤተ ክርስትያን በእናንተ ሕንፃው ነው? ከሆነም እየፈረሰ እናንእየተዘጋ ነው።

ጵጵስና ነው? ከሆነም ምንኩስና የሌለበት የፖለቲካ ኮታናንየጎሣንወኪል ሆኗል።

በዓላት ማድመቅ ነው? ከሆነም መንፈሳዊ ተልእኮውን ተገፍፎ የቱሪዝም ሸቀጥና የገጽታ ግንባታ መሣሪያ ከሆነ አርቲስቶች እየተረከቡት ነው። 

ቤተ ክርስቲያን የጥምቀት ልጆች በክርስቶስ አንድ መሆን ነው? እርሱንም በቋንቋ ሥር ተደብቃችሁ ለፖለቲካ ስትላላኩ  ወደየጎሣው በትናችሁ የዘር ጣዖት የሚያመልክ ትውልድ ፈጥራችኋል።

ቤተክርስቲያን በምድር የሰማያዊ ንጉሥ ክርስቶስ አምባሳደር ነች? ከሆነም አምባሳደርነታችሁ  ለድሎታችሁና ለሚልካችሁ ፖለቲካንሆኗል።

የቷን ቤተ ክርስትያን ከየት? ወዴት? እንዴት? እያሻገራችሁ ነው? 

ያብልጽግና ወንጌል ሃይማኖት ፓርቲ መሪውን #አብይ አህመድን አይነት ቅዠት የወረሳችሁ አይመስላችሁም?  እርሱ ነው ሰው እየፈጀ ስለ #ችግኝ፣ #ወደብ፣ #ግድብ #አስፋልት፣ #መናፈሻ እያለ ሰማይና ምድር የተፈጠረለትን ክቡር የሰው ልጅ ከቅዠቱ አሳንሶ  ነመመልከት መደበኛ ሠራዊት አስልፎ እያረደ "እያሻገርኳችሁ ነው" የሚለን።

የጨከነውን ግብረ መልስ ስሙ:-

በደብዳቤ ቀኖና መሻርን፣ ማስጨፍጨፍን፣ ሲኖዶስና ክህነትን መዳፈርን፣ ጎሠኝነትን፣ ምንኩስናን ማልከስከስን ---- መግባባት ይሉታል? ከሰይጣን የሚግባባ ራሱም ሰይጣን ነው! ሰይጣንን በስመ ስላሴ፣ የሰይጣን ሠራተኛንየሆነውን መንግሥት በሰማዕትነት ያባርሩታል እንጂ አይግባቡትም።
ከልጆቻችሁ ሳትግባቡ  ከጠላት የምትጋቡ ልትቀብሩን እንጂንልታሻግሩን ሀሳብ የላችሁም።
መነኩሴ ነኝ፣ አራዳ ነኝ አብሮ አፕሄድም። አንዱን ምረጡ። ወይ ክርስቶስን  ወይ ሰይጣንን።

ምንጭ፤ ሞዐ ተዋሕዶ

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment