Thursday, January 26, 2012

ተሀድሶያውያን እንደ እባብ የሞተ በመምሰል አፈር ልሰው ለመነሳት እየሞከሩ ነው

 

ትዝታው እና አቶ በጋሻው

(አንድ አድርገን ጥር 16 ፤ 2004ዓ.ም)፡- እነዚህ ሰዎች በጥምቅቱ የሲኖዶስ ጉባኤ የታገዱ እና ህገወጥ የተባሉ ሰባኪያን እና ዘማሪያን መሰል የተኩላው ለምድ የለበሱ ሰዎች (አቶ በጋሻው ደሳለኝ ፤ አሸናፊ ገ/ማሪያም ፤ አሰግድ ሳህሉ ፤ ትዝታው ሳሙኤል ፤ ምርትነሽ ጥላሁን ፤ ሀብታሙ ሽብሩ ፤ እና መሰሎቻቸው) በየትኛው በር ገብተው ነው የቤተክርስትያናችን አዳራሽ የተፈቀደላቸው ? እኛ እስከምናውቀው ድረስ ከቅዱስ ሲኖዶስ የትኛውም አውደ ምህረት ላይም ሆነ የትኛውም ቤተክርስትያን ላይ የመስበክ ፍቃድ እንዳይሰጣቸው እና ቤተክርስትያንን የማይወክሉ መሆኑን ገልፆ ቅዱስ ሲኖዶስ ለመላው አዲስ አበባ ውስጥም ላሉ ፤  ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚገኙ አብያተክርስያናት በሀገረስብከታቸው አማካኝነት እንዲደርሳቸው ተደርጎ ነበር ፤ ታዲያ ይህን ጉባዬ ለዛውም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት አዳራሽ ማን ፈቀደላቸው?

ፍቃድ የተሰጠው ገቢ ማሰባሰቢያ
አዘጋጆች፡-   (አቶ በጋሻው ደሳለኝ ፤ አሸናፊ ገ/ማሪያም ፤ አሰግድ ሳህሉ ፤ ትዝታው ሳሙኤል ፤ ምርትነሽ ጥላሁን ፤ ሀብታሙ ሽብሩ ፤ እና መሰሎቻቸው)


የምናፍቃኑ ግሩፕ በጋራ ምን ሊሠሩ ይሆን?

አሁን ግን እያልን ያለነው እነዚህ በአውደ ምህረት ላይ የመስበክና የመዘመር ፍቃድ የተነፈጋቸው ሰዎች አቅጣጫቸውን ለውጠው በዚህ መልክ ብቅ ማለታቸው ገርሞንም ደንቆንም ጭምር ነው ፤ የዛሬ ሶስት ሳምንት ገደማ የተሀድሶያውያን ሁለተኛ መናህሪያ ከተማቸው ባደረጓት በሐረር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ላይ የታኦሎጎስ አንደኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የሚፈልጉትን ሀሳብ ለማስተላለፊያ ያመቻቸው ዘንድ በጠቅላይ ቤተክህነት በወረደ ቀጭን ትእዛዝ በአላቸውን ሲያከብሩ ተመልክተናል፤ የሲኖዶሱ ውሳኔ የማይከበር ከሆነ ለምን ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት በዓመት ሁለት ጊዜ መሰብሰብ አስፈለጋቸው ? 


በተሀድሶ አቀንቃኝነት ስሙ ዘወትር የሚነሳው  አስግድ ሳህሉ ሳይቀር ፤ ከመላ አባሎቻቸው ጋር የገቢ ማሰባሰቢያ በሚል ሰበብ አዳራሹን በአቡነ ጳውሎስ ፈቃጅነት ሊዘሉበት ቅድመ ሁኔታዎችን አጠናቀው ቀኑን በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ ፤ ያገሬ ሰው ‹‹በጅብ ላይ ስጋ አይጫንም››የሚል ብሂል አለው ፤ እኛም ሲጫን አይተን አናውቅም ፤ ጅብን አምኖ ስጋ ቢጫን እንኳን የተላከው ቦታ እንደማያደርስ እሙን ነው ፡፡ ምዕመኑ እነዚህም ሰዎች ይህን የመሰለ በጎ አድራጎት ስራ ለመስራት ስጋዊ ጥንካሬ መንፈሳዊ ስብእናና ብቃት የሌላቸው መሆኑን አውቆ  ሊጠነቀቅ ይገባዋል ፤  የዛሬ 2 ዓመት ገደማ ከአንድ ሚሊየን የኢትዮጵያ ብር በላይ የቅድስት ማርያም ማኅበር ብለው የቤተ ክርስትያን ብር መብላታቸውን በቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ (ዜና ቤተ ክርስትያን ) ላይ ተገልጧል ፤ ብሩን መልሱ ቢባሉም ብሩም ሊመልሱ አልቻሉም ፤ የ‹‹ቋንቋዬ ነሽ ድንግል›› ዘማሪ ለህክምና የገቢ ማሰባሰቢያ ይረዳው ዘንድ ለመሸጥ የወሰደውን ቲኬት ሂሳብ ያልመለሰው የአቶ በጋሻው ደሳለኝን ስራ አንረሳም ፤ ደግሞ እነዚህን ሰዎች የቤተክርስትያንንና ፤ የባለቤቱን ብር የቆረጠሙ ለሰውስ ብር በምን ይታመናሉ? ታዲያ ይህን ድርጊታቸውን ዘርዝሮ ያወጣው ‹‹ዜና ቤተክርስትያን›› ጋዜጣ የሚታተመው በጠቅላይ ቤተክህነቱ ሆኖ ሳለ ለመሰል አላማ ሲንቀሳቀሱ እየተመለከተ ፤ የሲኖዶሱን ውሳኔ ወደ ጎን በመተው ዋናውን አዳራሽ ፈቅዶ ዝለሉበት ማለት ምን ይሉታል ? ለዘመናት ታፍራና ተከብራ የኖረች ቤተክርስቲያን አሁን በኛ ዘመን ደረሰችና መጫወቻ አደረጓት ፤ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን ያፈራች የበጎች ቤት ዛሬ የተኩላ መዝለያ ሊያደርጓት አዳራሹን ፈቀዱላቸው፡፡

ይህ ከእገዳው በኋላ ሁለተኛ መድረካቸው ነው ፤ በፊት በወር 30 ቀን ሙሉ በውሎ አበል እየዞሩ እንዳይጨፍሩ ማድረግ መቻላችን ጥሩ ሆኖ ሳለ አሁንም ደግመው እንዳይነሱ በምግባራቸውና በእኩይ ስራቸው ምዕመኑ እንዳይረብሹ ተግተን መስራት መቻል አለብን ፤ የዛሬ አዳራሽ እና አውደ ምህረት ለአልባሌ ሰዎች ፈቃጆች ነገ ስም አጠራራቸው እስኪረሳ ድረስ ያልፋሉ ይህች በማእበል የምትናጠው ቤተክርስያናችን ግን ቃሉ እስኪፈፀም ፀንታ ትኖራለች ፡፡

እንደ እኛ እንደ እኛ ባገኙት አጋጣሚ የነበራቸውን ቦታ ለማግኝት የማይፈነቅሉት ድንጋይ ፤ የማይወጡት ተራራ ፤ የማይገቡበት ቢሮ ፤የማይከፍሉት ዋጋ አለመኖሩን አስረግጠን መናገር እንችላለን ፤ ለዚህ ሁሉ ስራቸው የጀርባ አጥንት ሁነው ስራቸውን የሚደግፉትን አቡነ ጳውሎስን እና መሰሎቻቸውን እግዚያብሔር ሀሳብ ድርጊታቸውን የሚያስታግስበት ጊዜ ሩቅ ነው ብለን አናስብም ፤ ከጥቅምት ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ አከርካሪያቸውን ተመተው የራቁት ተሀድሶያውያን እንደ እባብ የሞተ በመምሰል አፈር ልሰው ለመነሳት እየሞከሩ መሆኑን ልናጤን እና ልንገነዘብ ይገባል ፤ ለጊዜው ሊርቁልን ይችሉ ይሆናል ነገር ግን እደማይተውን ጭምር ማወቅ አለብን ፤ ዛሬ ቤተክህነት አዳራሽ እንዲሰብኩ ፍቃድ ተሰጥቷቸዋል ፤ ነገ ደግሞ አውደ ምህረት ላይ እንደማይወጡ ምንም ማረጋገጫ የለንም ፡፡ 

የወንድማችን ህመም እግዚአብሔር ፈፅሞ እዲምረው ፅኑ ምኞታችን ነው ፤ ነገር ግን ይህን አጋጣሚ በመጠቀም በመርዝ የተለወሰ ትምህርታቸውን ፤ ከፕሮቴስታንት የተቀዳ መዝሙራቸውን በቤተክርስያናችን አዳራሽ መካሄዱን ፈፅሞ እንቃወማለን ፤ 20 ብር የመርጃ ቲኬት አዘጋጅቶ በመናፍቃን ተሀድሶያውያኑ የታሸውን በቀኑ ለማስተላለፍ ያሰቡትን ትምህርታቸውን እንቃወማለን ፤ መርዳት የምትፈልጉ ሰዎች በአካል ተጎጅውን አግኝታችሁ ብትረዱት ከእግዚአብሔርም መልስ ምታገኙበት ስራ ነው ፤ ያዘጋጁትን ጉባኤ ላይ መገኝት ግን እነሱን እንደማበረታታት ስለሚቆጠር ልታስተውሉ ይገባል፡፡

እነርሱ መንገዳቸው ረዥም ስትራቴጂያቸው እንደ እስስት በየጊዜው ተቀያያሪ መሆኑን አውቀን አቡነ ጳውሎስ ቢፈቅዱላቸው እንኳን እኛ ራሳችንን እና አብያተክርስትያናችንን ከመሰል የመናፍቃንን ትምህርት ለብሰው ከመጡ እና ከሚመጡ አስመሳይ ተሀድሶያውያን ነቅተን መጠበቅ ይገባናል ፡፡ ፤ እግዚአብሔርም ወንድማችንን እንዳለ ገብሬ ከህመሙ ይምረው ዘንድ መልካም ምኞታችን ነው፡፡ 
ከአንድ አድርገን የተወሰደ።
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

3 comments:

  1. yetewahido tekorikar atmeslum
    aye maberekdusan kasetachew alshet ale?
    bewushet yesewu semi matfat hatyatnew manm ayaminachewm wushetam eyandandh rasin atsseda lelawun kemekonen ..............

    ReplyDelete
  2. egziabher leb yeste wendem bewendemu lay yeminsabet zemen yasznal betam

    ReplyDelete
  3. right you are.Go ahead God is always with us.

    ReplyDelete