Monday, January 23, 2012

አባ ፋኑኤል እና የሐሰት ስርጭታቸው

ባለፈው ቅዳሜ ጥር ፲፪ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. አባ ፋኑኤል በቪኦኤ የአማርኛው ዝግጅት በአቶ አዲሱ አበበ  አማካኝነትክፍል አጭር ቃለ መጠይቅ አድርገው ነበር፣ በቃለ ምልልሱም በርካታ የሆኑ ውሸት አዘል መልዕክቶችን በአባው ተላልፈዋል ከነዚህም ቀንጠብ ቀንጠብ አድርገን ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡ በመቀጠል ጥያቄዎችን በተከታታይ እንመልከታቸው
ጥያቄ: አባታችን አሁን የመጡበት ሹመቶ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው?
መልስ፡ አዎ፣ ከዚህ በፊት መጥቼ ቅዱስ ፓትሪያሪኩንም ነግሬያቸው ነበር እኔ የመጣሁት ሀገሬን ለማገልገል ነው እና በተቻለ መጠን እዚሁ ቢያረጉኝ ብዬ ነበር ነገር ግን በቅዱ ሲኖዶስ ስለታዘዝኩኝ ትዕዛዙን አክብሬ መጥቻለሁ፣ በመቀጠም እራሴው ደብዳቤ ጽፌ ወዳገሬ እንዲመልሱኝ ያለምንም ችግር በመጣሁ በሦስት ወሬ ወዳገሬ ተመልሻለሁ ነበር ያሉት።
እርምት: እኛ እስከምናውቀው ድረስ ከዚህ በፊት በመጡበት ወቅት ትልቅ ችግር ተነስቶ እንደውም በቅዱስ ሚካኤል ደብር መቀመጥ እንደማይችሉ ተነግሯቸው፣ እንደዛ ከሆነ የቤቱ ባለቤት እራሴው ነኝ እስቲ የምታደርጉትን እናያለን ብለው ከጥቂት የቤተክርስቲያኑ አባላት ጋር አምባጓሮ ጀምረው በዛው ጊዜ የተጀመረው የፍርድ ቤት ክስ እስከ አሁን ድረስ ሕዝበ ክርስቲያኑን ለሁለት ከፍሎት ይገኛል፣ ቤተክርስቲያኑንም ላላስፈላጊ የ$200000 ብር ወጪ ተዳርጓል ለምን ይሄን ሸሸጉ?
ሌላው በዚሁ በመጡበት ጊዜ በተለምዶ እራሳቸውን ገልልተኛ ብለው የሚጠሩ አብያተ ክርስቲያናት ስብስብ ከቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለንም ብለው በዛው ጊዜ ከገለልተኞች አንድነት የወጡበት እና ባይተዋር የተደረጉበት ጊዜ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው።

ጥያቄ: እንዴት በድጋሚ ሊመለሱ ቻሉ?
መልስ: "ሕልም ሲደጋግም እውነት ነው እንደሚባለው" አሁን ለሁለተኛ ጊዜ በቅዱስ ሲኖዶስ ይሄን ሀገረ ስብከት እንዳገለግል ስላክ እውነትም እግዚአብሔር እንዳገለግለው የፈለገው እዚህ መሆን አለበት መሆን አለበት ብዬ እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ ትዕዛዝ ለማክበር ብዬ ተመልሼ መጣሁ።
እርምት: እርሳቸው እንዳሉት ሕልም ሲደጋግም የሚሉት ቅዠት ካልሆነ ሕልም እንዳልደገማቸው ብናውቅም ባለፈው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ወቅት ከዚህ አደራጅተው በቀሲስ አማረ ካሣዬ መልዕክተኝነት የተላኩትስ? እነሱም በሕልም ነው በዕውን መልሱን ለሳቸው እንተወው እና ከዚህ በፊት ወደዚህ ዋሽንግተን ዲሲ በሕገወጥ መንገድ በመጡ ጊዜያት ሁሉ ያለቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ወይም የለሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ እውቅና ሲሾሙ፣ ሲሸልሙ፣ ቤተክርስቲያን ሲባርኩ፣ እንዲሁም የተለያየ ከቀኖና ውጪ ሲሰሩ በነበረበት ጊዜ ሁሉ፣ በተለያዩ በሄዱባቸው ቦታዎች ሁሉ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እኮ እኔ ነኝ አሁን ያሉት አባት ከተነሱ ቆይተዋል በማለት ይናገሩ የነበረውስ? የቅዱስ ሲኖዶስን ትዕዛዝን አከብራለው ማለታቸው ማንን ሊያታልሉ ነው፣ "ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት" እንዳይሆንቦት እንላለን።
ጥያቄ: ለሁለተኛ ጊዜ ተሹመው ሲመጡ ምን አይነት አቀባበል ተደረገሎት?
መልስ: ለሁለተኛ ጊዜ ተመልሼ ስመጣ በርካታ የዋሽንግተን ዲሲ ካሕናት፣ አስተዳዳሪዎች፣ የቦርድ ተወካዮች፣ ምዕመናን በታላቅ አክብሮት አቀባበል አድርገውልኛል።
እርምት: በወቅቁ የተገኙ የዚህ ዝግጅት ተወካዮች እንደገለፁልን የሚካኤል ቤተክርስቲያ ቦርድ አባላት ሦስቱ፣ ከከህናት የኪዳነ ምሕረት ቨርጂኒያ፣ ቀሲስ ደረጀ ስዩም፣ ቀሲስ ይስሐቅ፣ የደብረ ምህረት ካህናት በሙሉ፣ በጣም ጥቂት የደብሩ ሰንበት ት/ቤት አባላት ብቻ ነበሩ የተገኙት ከተገኙት ጥቂት ካህናት ውስጥም ደጅ ጥናት እንደሆነ ይገመታል ለምን እንደመጡም የታወቀ ነው እንደተለመደው ክፈቱልን ለማለት እንደሆነ የታወቀ ስለሆነ የሚያስገርም አይደለም። ከሁሉ የሚገርመው ግን በታላቅ አክብሮት አቀባበል አድርገውልኛል ሲሉ መሰማቱ በጣም ያስገርማል። የሚመጡበትን ቀን ሳይቀር በቲፎዞዎቻቸው አሳስተው ሳይጠበቁ በድብቅ ገብተው ማደራቸውን የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ስለሆነ አያስገርምም።
ጥያቄ: ባለፈው አንድ የስብሰባ ጥሪ አድርገው ነበር፥ በመጥሪያውም ላይ የቤተክርስቲያናችሁ ደንብ እንደተከበረ ሆኖ፣ ቀኖና እንዳይጣስ፣ ሥርዓት እንዳይበላሽ እንመካከር ብለው ነበር ለምን? በስብሰባው ላይ ምን ያህሎች ተገኙ?
መልስ: ባለፈው ታሕሳስ ፯ ባደረግነው ስብሰባ ለ፲፯ ስቴቶች የስብሰባ ጥሪ አድርጌያለሁ፣ ብዙዎች በተለይ እሩቅ ያሉት አንዳንዶች አንድ ካህን ስላላቸው፣ ለእሁድ አገልግሎት ስለማይደረሱ እንደማይመጡ ገልጸውልናል፥ ሆኖም ግን ከአካባቢያችን ፱ የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች፣ ሁለት የቤተክርስቲያን ተወካዮች በጥቅሉ ፲፩ ቤተክርስቲያኖች ተገኝተዋል ነበር ያሉት።
ተያያዥ ጥያቄ: በስብሰባው ላይ እኮ በተለይ እራሳቸውን ገለልተኛ ከሚባሉት ሚካኤል ብቻ ነበር የተገኙት እንዴት ነው?
መልስ: አይደለም ከተገኙት መካከል የኪዳነ ምሕረት ቨርጂኒያ አስተዳዳሪ፣ የውድ ብሪጅ ኢየሱስ (በቀሲስ ወርቅነህ ኃይሌ) የተመሠረት (ያለ ኤጲስ ቆጶስ ወይም ጳጳስ የተባረከ ቤተ ክርስቲያን ሊባል አይችልም ፍትኀ ነገሥት መንፈሳዊ) የልደታ ተወካይ ብለው ከ፲፩ ውስጥ ሁለቱን ብቻ ነበር የጠቀሱት ሌሎች ተወካይ ወይም ቦርድ አልተገኙም ማለት ነው (ወይ የውሸት መዓት. . . ስብሃት ለአብ. . . እውነት እኛን መስለው ሊነጥቁ የመጡ መሆናቸውን ሊያሳየን ይችላል)
እርምት: እዚህ ላይ አቡኑ የተናገሩት በሙሉ ውሸት እንደሆነ በአጠቃላይ በቃለ ምልልሱ ላይ ጠቅሰውታል መጀመሪያ አስራ አንድ ናቸው ብለውን ነበር፣ በኃላ ደግሞ ከጠቀሱት ሦስቱ ቤተክርስቲያን ከሚባሉት ሁለቱን ብቻ ነበር የጠቀሱት፣ በአጠቃላይ የአባ ፋኑኤልን ሥራ ልንመለከት ይገባናል የበግ ለምድ ለብሰው የመጡ ነጣቂ ተኩላነታቸውን በሚገባ ያስገነዘቡን ይመስለናል።
የሆነ ሆኖ ፍርዱን ለተመልካች እና ቤተክርስቲያናችንን ልንጠብቅበት የሚገባ ጊዜ ስለሆነ ክርስቲያኖች ሁላችን ነቅተን ልንጠብቅ፣ ሕዝበ ክርስቲያኑን ከነጣቂ ተኩላዎች ልንጠብቃቸው ይገባል ባይ ነን።
በመጨረሻ ለአባ ፋኑኤል: ቤተክርስቲያን መቼም አሳድጋ፣ አስተምራ (የተማሩት ካለ ማለታችን ነው)፣ ለክብር አብቅታ በከበሬታ ወንበር ላይ አስቀምጣ ስታበቃ እንደዚህ ቤተክርስቲያንን ለመናፍቃን እና ለፕሮቴስታንቶች አሳልፎ ለመስጠት ምን አደፋፈረዎ፣ ወይስ ቤተክርስቲያኒቱስ ምስን አጎደለችብዎት? ሲሆን እዚህ ላደረሰችዎ ቤተክርስቲያን፣ ነገ ጥለው ለሚሄዱት ዓለም እንዲህ ክርስቲያኖችን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በሰጠዎት ሥልጣን ተጠቅመው ከሚያምሱት፥ ለምን ነገ ትውልድ ሊያመሰግንዎ፣ እግዚአብሔርም በምድር ያከበረዎ በሰማይም እንዲያከብርዎ ሥርዓቷን፣ ቀኖናዋን፣ ትውፊቷን ለልጅ ልጅ ለማድረስ አይፋጠኑም በእውነቱ በአሁን ሰዓት ቤተክርስቲያንን ልንታደግ የሚገባ ጊዜ መሆን ሲገባው ለምን ሰድበው ለሰዳቢ ቤተክርስቲያኒቱን ይሰጣሉ? ለምንስ ያለውን እንደነበረው ከአባቶቻችን የተቀበልነውን የሃይማኖት አንድነት ለነገው ማስተላለፍ አቃተን፣ እግዚአብሔርስ እንዴት ይለመንን እናንተ ካሕናት እኮ ናችሁ ሕዝቡን ወደ ድህነት እንድትወስዱት ሥልጣኑን ካህን፣ ጳጳስ አድርጎ የሾማችሁ ይሄ እንዴት ተረሳችሁ ምን ጥቅም ዓይንን ቢያውር ለተመረጡለት ክብር መብቃት ደግሞ ከኛ ይጠበቃል እግዚአብሔር እንዳከበረዎ፣ የተሰጠዎትን ቢቀበሉ እንመክራለን፤ ነገር ግን በራሴ ጥበብ በሚሉት ቢሄዱ እጁን መዘርጋቱ አይቀርም "የሲኦል ደጆች አይችሏትም" ነው የተባለላት።
ሲሆን አጠገብዎ የከበብዎትን የተኩላ መንጋ አስወግደው ለክብር ላበቃችዎ ቤተክርስቲያን ለሥርዓቷ፣ ለቀኖናዋ፣ ለትውፊቷ የሚጋደሉ ሕይወታቸውን የሚሰጡትን ወገኖች ሰብስበው ቢሰሩ መልካም ይመስለናል ነገር ግን በኢትዮጵያ እና በተለያዩ ሀገሮች በታወቁት መናፍቃን የፕሮቴስታንት አፈ ቀላጤዎችን ለምሳሌ እንደ
፩ኛ/ አባ ኃይለሚካኤል ቀንደኛ የፕሮቴስታንት ምልምል
፪ኛ/ ኃይለጊዮርጊስ ጥላሁን ተረፈ አርዮሳዊ በምንፍቅናው ከቤተክርስቲያን የተባረረ
ሌሎች ለጥቅም የከበቦዎት ሁሉ፣ ለቤተክርስቲያን ሳይሆን ለግል ጥቅማቸው የሚሯሯጡ፣ አሁን በስም የማንጠቅሳቸው ነገር ግን በቅርብ ዝርዝር ሥራቸውን የምንጠቁማቸው ለከርሳቸው ያደሩ ክህነታቸውን እንደ ኤሳው ለእራፊ ጨርቅ እና ለቁራሽ እንጀራ የሸጡ ከበው ልክ የወደቀ ሥጋ እንዳየ አሞራ ዙሪያ ከበው "ቅዱስ አባታችን" (ቅድስናዎን እርሶ ያውቃሉ) የሚልዎት በሙሉ እውነት ለቤተክርስቲያን መቆማቸውን በቀላሉ ማሳየት ይችላሉ። ልጥቅም የቆሙ እንደሆኑም በተደጋጋሚ በሚሰሩት እና በሚያደርጉት እራሳቸውን ያሳዩ የጥቅም ሰዎች ናቸው።

ሌላው ለአቶ አዲሱ አበበ፥ የአሜሪካን ሬዲዮ ጣቢያ አቅራቢ፣ የሠራህው በጣም ጥሩ ሥራና ጊዜውን የጠበቀ ሥራ በመሆኑ ልትመሰገን ይገባሃል። ነገር ግን ሥራህን ሙሉ ሊያደርግ የሚችለው የሚከተሉትን ሚዛናዊ በሆነ የጋዜጠኝነት ሙያ መሰረት ስታቀነባብረው ነው፤
፩ኛ/ አባ ፋኑኤል መቼም ያሉት ሁሉ ትክክል ነው ብለህ እንደማትቀበል ሁሉ ሐሰት ነው ልትልም እንደማትል እርግጠኞች ነን፤ እንደ አድማጭ ግን የምንጠቁመው እውነቱን ከሐሰቱ ሊለይ የሚችለው ልክ በአሜሪካን ሀገር (fact checker) እንደሚባሉት በእኛም ሀገር በተለይ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሊቃውንት ጉባኤ እንዳለ ስለምታውቅ የተናገሩትን በሊቃውንቱ ጉባኤ ብታረጋግጥ፣ ቤተክርስቲያኒቱ እንዲህ አይነት አሠራር የላትም ብለው ሲሉ ተቀብለን መሄድ ያለብን አይመስለንም።
፪ኛ/ በቦታው የነበሩትን አባት አቡነ አብርሃምን ማነጋገር ምናልባት ሚዛናዊ ሊያደርው ይችላል ብለን እናምናለን ስለዚህ በሚገኙበት ቦታ ብታነጋግራቸው ሥራህን ሚዛራዊ ሊያደርው ይችላል ብለን እናምናለን።


ቸር ይግጠመን ብለን ለዛሬ እንሰናበታለን

http://vimeo.com/35450932
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

No comments:

Post a Comment