Friday, January 27, 2012

አባ ፋኑኤል በዳላስ ቴክሳስ


ሥርዓት አልበኛው ጳጳስ አባ ፋኑኤል

በትላንትናው እለት አባ ፋኑኤል ወደ ዳላስ ቴክሳስ ጉዞ አድርገው ከካሊፎርኒያ እና የምዕራቡ አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ካህናት ኃይለሥላሴ እና  ለስብሰባው ከተገኙት የደብር ተወካዮች ጋር ንግግር ለማድረግ ትላንት አመሻሹ ላይ ዳላስ ቴክሳስ ገብተው አድረዋል። በደብረ ምሥራቅ አቡነ ተክለሃይማኖት ወአረጋዊ ቤተክርስቲያን የሚደረገው ይህ ከአቡኑ ጋር የሚደረገው ስብሰባ ምንም አይነት ውጤት እንደማያመጣ እና በደጋሚ የአቋም ለውጥ ካመጡ በሚል ቀቢጸ ተስፋ እንጂ ምንም የተለየ ነገር እንደማይጠብዙ የስብሰባው ተሳታፊዎች ከቦታው ገልጸውልናል፥ በተለይ በቦታው የተገኙት የደብር ሃላፊዎች እና የሰበካ ጉባኤ አባላት አቡኑ ሀሳባቸው እንደ ሁልጊዜው ከሆነ በምንም መልኩ አብረዋቸው እንደማይሠሩ ከወዲሁ ሲነጋገሩበት የቆየ ቢሆንም አንድ ቁርጥ ውሳኔ ከአቡነ ፋኑኤል እንደሚጠብቁና ውጤት ሊያመጣ የሚችል ንግግር ካልሆነ ግን ስብሰባውን ጥለው ወደየመጡበት ሀገር እንደሚወጡ አስቀድመው አሳውቀዋል። ለዚህ ስብሰባ መጠራት ትልቅ አስተዋፅኦ ያደረጉት የዴንቨር ደብረ ሰላም መድኃኒዓለም አስተዳዳሪ የሆኑት ሊቀ ካህናት ኃይለሥላሴ እንደሆኑ እና በባለፈው በ፴ኛው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ወቅትም በብጹዕ አቡነ ኤውስጣቲዎስ እና በብጹዕ አቡነ አብርሃም ላይ ከሊቀ መምሕራን ቀሲስ አማረ ካሣዬ ጋር በመሆን በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ አቤቱታ አቅርበው ለአባ ፋኑኤል ወደ አሜሪካን መምጣት አይነተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው ይታወሳል።

 በስብሰባው ላይ ብዙ ያልተገኙ አድባራት ተወካዮች ያልተገኙ ቢሆንም፥ የተገኙት ግን አባ ፋኑኤል በተለያየ ጊዜ የሚያደርሱትን የሥርዓተ ቤተክርስቲያን መጣስ እና የቀኖና ማፍረስ ሥራዎችን በመቃወም ነበር ስብሰባው የተጀመረው፤ ተሰብሳቢዎቹም የተለያየ የምስል እና የድምጽ መቅረጫዎችን እንዳይጠቀሙ ሊቀ ካህናት አጥብቀው ሲያሰሙ ስለነበር በተከታዮቹ ቀናት በተሰብሳቢዎቹ ካህናት እና የሰበካ ጉባኤ ተጠሪዎች ችግር ሳይገጥማቸው እንደማይቀር ይገመታል።
የስብሰባው ሙሉ ሪፓርት እንደደረሰን እናቀርባለን ተጠባበቁን። 
ቸር ወሬ ያሰማን

የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

2 comments:

  1. የስብሰባው ሙሉ ሪፓርት እንደደረሰን እናቀርባለን ተጠባበቁን ብላችሁ ነበር ነገር ግን እስከአሁን ምንም ያቀረባችሁት ዘገባ የለም:: ምነው?

    ReplyDelete
  2. ሰላም አንባቢ፣
    ሙሉው ሪፓርት ደርሶናል፣ በቅርቡ ይጠብቁን ስለ አስተያየቶት ለልብ እናመሰግናለን
    የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

    ReplyDelete