Friday, March 23, 2012

ሦስተኛው የVOA ቃለ ምልልስ ስለ ገዳመ ዋልድባ


የዋልድባ ገዳም እና በአካባቢው በሚደረጉ የመንግስት በእጅ አዙር ሃይማኖትን የማጥፋት ሥራ በVOA ለሦስተኛ ጊዜ የዓድርቃይ መስተዳር ኃላፊ የሆኑት አቶ ሲሳይ የተናገሩት እና በመምህር ገብረ ክርስቶስ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ ነው።
መንግስት የተለያዩ ማስተባበያዎችን ማውጣቱን ቀጥሎ ፕሮጀክቱንም በምን ቸገረኝነት እንደቀጠለ ይነገራል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በመጪው ሰኞ ለተጠራው ሕዝባዊ ትዕይንት በተለያየ የአሜሪካን ግዛቶች ይህው ትዕይንት
እንደሚደረግ ይጠበቃል። ከአካባቢው በደረሰን ምንጭ መሰረት በተለይ በዋሽንግተን ዲሲ እና በአካባቢው ባሉ የተለያዩ ቤተክርስቲያን
ባሉ ወጣቶች አስተባባሪነት ይህው ሰላማዊ ትዕይንት ለማድረግ በዝግጅት ላይ እንደሆኑ ለመረዳት ችለናል፣ በዚህም ሕዝባዊ ትዕይንት
ላይ በተለምዶ የተለያዩ ክፍፍል ያለባቸው የቤተክርስቲያን አካላት በዚህ ጉዳይ "በቤተክርስቲያን ጉዳይ፥ ዝም አንልም" በማለት በተለያዩ የቤተክርስቲያን አስተዳደሮች በበኩላቸው ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ለመረዳት ችለናል፥ በዚህ ሕዝባዊ
ትዕይንት ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አማኝ ብቻ ሳይሆን መላው የኢትዮጵያ ቅርስ እና ሃብት መውደም እና መጥፋት የሚያሳስባቸው
በሙሉ በትዕትይኑ ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ስለ ሕዝባዊት ትዕይንት ከአካባቢው የሚደርሱንን መረጃዎች እንደደረሰን ለማቅረብ እንሞክራለን
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

No comments:

Post a Comment