Friday, March 9, 2012

ጥንታዊው ገዳመ ዋልድባ ለመታደግ የአቤቶታ ሰላማዊ ሰልፍ ማርች 26, 2012 ይደረጋል

ጥንታዊው ገዳመ ዋልድባ ለመታደግ የአቤቶታ ሰላማዊ ሰልፍ ማርች 26, 2012 ይደረጋል

 READ IN PDF
አጽራረ ቤተ ክርስቲያን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለማዳከም በተጠና እቅድ ይንቀሳቀሳሉ:: ከእቅዶቻቸውም መካከል ለቤተ ክርስቲያኒቱ የትምህርት እና የጸሎት ማዕከል በመሆን እያገለገሉ የሚገኙት ታላላቅ ገዳማትን የሚጠፉበት ሁኔታ ማመቻቸት ነው:: ከእነዚህ ታላላቅ የቤተ ክርስቲያኒቷ የአስተምህሮ ማዕከላት መካከል አንዱ ገዳመ ዋልድባ ነው:: እነዚህን የትምህርት ማዕከላት ገዳማት ለማጥፋት በተለያየ ግዜ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን ሞክረው ነበረ:: ነገረ ግን በቀደሙት አባቶቻችን ፍጹም ተጋድሎ ለዚህኛው ትውልድ አስተላልፈው አልፈዋል::

ከጥንታውያን ታላላቅ ገዳምት ውስጥ የምትመደበው የዋልድባ ገዳም ህልውና አስገጊ ደረጃ ላይ መሆኑን የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል:: አሁን በእኛ ዘመን መንግስ ልማት ተገን በድረግ የአጽራረ ቤተ ክርስቲያን እቅድ እውን እያደረገላቸው ይገኛል:: ዋልድባ  ለብዙ ዘመናት በአባቶቻችን ተጋድሎ ተከብሮ  እኛ በአደራ እንደተረከብነው ሁሉ ለሚቀጥለው ትውልድ እስከነ ሙሉ ይዘቱ በአደራ የማስተላለፍ ግዴታ አለብን::

ገዳሞቻችን የማፍረስ የአጽራረ ቤተ ክርስቲያን እቅድ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በታላላቅ ገዳማት አካባቢ የሚደረጉ ተግባራት ገዳማቱን ያማከለ ጥናት ሳይጠና መከናወን የለበትም:: መንግስት የገዳማቱ አስተዳደር ሳያማክል ያጠናው ጥናት ተገቢ አይደለም:: በገዳማቱ አካባቢ የሚደረጉ ልማቶች ለገዳማቱ ህልውና አስጊ እንዳይሆን መንግስት መከላከል አለበት::

አሁን በዋልድባ ገዳም እየተደረገ ያለው የልማት እንቅስቃሴ ለገዳሙ ህልውና አስጊ መሆኑን የገዳማቱ አባቶች የአቤቶታ ጥሪ ማስተላለፋቸው በመገናኛ ብዙኃን ተገልጾልናል:: መንግስት የአባቶች አቤቶታ ችላ በማለት እንቅስቃሴውን ቀጥሎበታል::

ይህንን የገዳማቱ አባቶች አቤቶታ የሰሙ ቅናተ ቤተ ክርስቲያን ያደረባቸው/የበላቸው ወንድሞች የአቤቶታ ሰላማዊ ሰልፍ በተለያዩ የዓለማችን ከተሞች ለማድረግ እቅድ ይዘዋል:: የመጀመርያው ሰላማዊ ሰልፍ የአሜሪካ መንግስት መቀመጫ በሆነችው በዋሽንግተን ዲሲ March 26, 2012 ወይም
መጋቢት 17፣2004 ከጠዋቱ 3 ሰዓት፤ በዚህ ሀገር አቆጣጠር 9am ይደረጋል::  በአቤቶታ ሰልፉ ላይ ሁሉንም የቤተ ክርስቲያን አማኝ ምንም ዓይነት የፖለቲካ ልዩነት ሳይገታቸው በአንድነት ድምጻቸውን እንዲያሰሙ አዘጋጆቹ የአደራ ጥሪ አስተላልፈዋል::

የታላላቅ ገዳማት ህልውና መጠበቅ ለቤተ ክርስቲያናችን ህልውና መጠበቅ ስለሆነ በተለያየ ዘርፍ የተከፋፈሉት የቤተ ክርስቲያኒቷ ልጆች በዚህ እንዲተባበሩ አሐቲ ተዋሕዶ ጥሪዋን ታስተላልፋለች::

እግዚአብሔር አሐቲ ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን!!!
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

1 comment:

  1. ግንኮ መንግስት የልማት እንቅስቃሴው በምንም ሁኔታ ክገዳሙ ጋር ንክኪ እንደማይኖረው መግለጫ ሰጥቷል....::

    ReplyDelete