Saturday, March 17, 2012

ብጹዕ አቡነ ሺኖዳ ከዚህ ዓለም ድካም በሰላም ዓረፉ


ብጹዕ አቡነ ሺኖዳ አረፉ

በጣም አሳዛኝ ዜና!!
አንድ አድርገን መጋቢት 7 ፤ 2004ዓ.ም)ለዐሠርት ዓመታት የግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና ሁላችንንም በትጋትና በጽንዕ ያገለገሉት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ በ88 ዓመታቸው እንዳረፉ ቢቢሲ ዘገበ፡፡

ለእርሳቸው ወደ ክርስቶስ መሄድ የሚናፍቁት ቢሆንም
 ለእኛ በሕይወተ ሥጋ ላለን ግን አጽናኝን አባት ማጣት ነው፡፡

በጣም አዝነናል በዚህ ጊዜ አቡነ ሺኖዳን በማጣታችን ፤ ይህ የኮፕቶች ሀዘን ብቻ አይደለም ፤ የእኛም የእህት አብያተክርስያናት ጭምር ነው ፤ በጣም በጣም አዝነናል ፤
አምላክ ነፍሳቸውን በገነት ያሳርፍልን 
ታላቁን አባታችንን ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳንን ማጣት ምን ያህል ይከብዳል!!!....
አምላክ ሆይ እኛን ባሪያዎችህን እባክህ ያለ እረኛ አታስቀረን ፡፡
ፖፕ ሺኖዳ ሳልሳዊ


(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 8/2004 ዓ.ም፤ ማርች 17/2012)፦ ተወዳጁ የቅብጥ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፖፕ ሺኖዳ ሣልሳዊ በተወለዱ በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን የአገሪቱን ሬዲዮ የጠቀሰው ቢቢሲ ዘግቧል። ለእረፍታቸው ምክንያት የሆነው ምን እንደሆነ ያልተገለጸ ቢሆንም በዕድሜ አረጋዊ የኾኑት ቅዱስነታቸው  ለረዥም ጊዜ ሲታመሙ መቆየታቸው ይታወቃል። 
የግብጽ ኦርቶዶክስ ምእመናን  ከ80 ሚልዮን የአገሪቱ ሕዝብ 10 እጅ (10%) ብቻ ሲሆኑ በአክራሪዎች በሚደርስባቸው ተደጋጋሚ አደጋ ምክንያት ፖፕ ሺኖዳ መንግሥት የበለጠ ጥበቃ እንዲያደርግላቸው ሲማጠኑ ቆይተዋል።
ከዚህ በፊት በደጀ ሰላም ላይ ባቀረብነው አንድ ዘገባችን ፖፑ “በልቤ ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ መናገር አልችልም። ዝምታዬን እግዚአብሔር ይሰማዋል” ካሉ በኋላ ምእመናኑ ፊት ሲያነቡ ታይተዋል።  ከጻድቁ ፖፕ ከአቡነ ቄርሎስ ቀጥለው በመንበረ ማርቆስ የተሰየሙት 117ኛው ፖፕ  አቡነ  ሺኖዳ በተለይም በኢትዮጵያ ምእመናን ዘንድ በመጽሐፎቻቸው የበለጠ ታዋቂ እና ተወዳጅ ሆነዋል። ኢትዮጵያን ለመጎብኘት በመጡበትም ወቅት ሕዝቡ ከቦሌ ጀምሮ ደማቅ አቀባበል እንዳደረገላቸው ይታወሳል።
የቅዱስነታቸው በረከት አይለየን፤ ይደርብን፤ ለግብጽ ቤተ ክርስቲያንም የብፁዕ ወቅዱስ አቡነነ ሺኖዳን ዐይነት አባት ይተካላቸው፤ ይስጣቸው። አሜን
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

No comments:

Post a Comment