Thursday, December 6, 2012

የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ለብፁዕ ወቅዱስ እንዲመለሱ በደብዳቤ ፈቀዱ፤ ደብዳቤውን አጠፉ



  • የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮን ዘገባና ቃለ ምልልስ አዳምጡ::
  •  ደብዳቤዎቹን ከዚህ ላይ ያገኟቸዋል።
(ደጀ ሰላም ኅዳር 27/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 6/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርርዮስ ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊት ሪፓብሊክ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ደብዳቤ ከጻፉ በኋላ ሐሳቡን ማጠፋቸውን ገልጸዋል::በችኮላና የሚያስከትለውን “ጣጣና መዘዝ” ባለማገናዘብ በቀናነት የጻፉት ደብዳቤ መሆኑን ያብራሩት ክቡር ፕሬዚዳንቱ “መንግሥት በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ እንደማይገባ” በማስታወስ ደብዳቤያቸው መሳባቸውን አስታውቀዋል።


ከዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ አቡነ ናትናኤል ጋር መነጋገራቸውን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ በሊቀ ጳጳሱ መገሰጻቸውን አልሸሸጉም። “ይቅርታ አድርጌልኻለኹ” መባላቸውን አብራርተዋል። ስለዚህ ትህትናዎ፣ ክቡር ፕሬዚዳንት ግርማ፣ እናመሰግንዎታለን። ፕሬዚዳንት ግርማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋዶ ቤተ ክርስቲያን 4ኛ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ወደ ሃገር ቤት ተመልሰው ከሁለት የተከፈለችው ቤተ ክርስቲያን አንድ እንድትሆን የሚያሳስብ ደብዳቤ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ እና ለብፁዕ አቡነ ናትናኤል መጻፋቸው፣ ምንም እንኳን ዘግይቶ “ቢስቡትም”፣ ሐሳቡ ግን አስደስቶናል። ይበል ብለናል ክቡር ፕሬዚዳንት። እንደ መንግሥት ኃላፊነትዎም ባይሆን እንደ አንድ በሥልጣን ወንበር እንደተቀመጠ ኦርቶዶክሳዊ ሐሳብዎን መግለጥዎ ተገቢም፣ ጥሩም ነው።

ለማንኛውም የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮን ዘገባና ቃለ ምልልስ አዳምጡ።

ቸር ወሬ ያሰማን                                                                                                        


“ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን - ስለ ቤተ ክርስቲያን ሰላም ጸልዩ”።

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment