Wednesday, December 5, 2012

በጀርመን የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ካህናት “ግልጽ ደብዳቤ” አወጡ


(ደጀ ሰላም ኅዳር 23/2005 ዓ.ም፤ዲሴምበር 1/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በጀርመን አገር ኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን ኃላፊ የሆኑት ሊቀ ካህናት /መርዓዊ ተበጀ “  ስለ  ነገዋ ቤተክርስቲያን ስንል ዕድሉ ዛሬባያመልጠንስ? “   ሲሉ “  ግልጽ ደብዳቤ”   አወጡ። የእናት ቤተክርስቲያን መካፋፈል የራስ ምታት፧ የሆድቁርጠት፧ የልብ ሕመም ወዘተ ሆኖ 21ዓመታት  “   እኽ እኽ››  እያሰኘ መኖሩበውስጡ ላለፈበት ትውልድ ሁሉ ግልጽ”   መሆኑን የጠቀሱት ሊቀ ካህናቱ እርሳቸውም የበኩላቸውን ሐሳብ ለመስጠት እንደፈለጉ ጠቅሰዋል። ይህንን ደብዳቤ አሁን መጻፍ የፈለጉት ጊዜው “የተመቸ” ነው በሚል ወይም በርሳቸው አገላለጽሲመች በእጅ፣ ሲፈጅ በማንካ ለማለት ሳይሆን ከዚህ አስቀድሞ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ከመሾማቸው አስቀድሞም ተመሳሳይ ሐሳብ ማቅረባቸውን ማስረጃ ጠቅሰው አብራርተዋል።

ደጀ ሰላም ይህ መሠረታዊ ጽሑፍ ለአንባብያን ቢደርስ ያለውን ጥቅም በመረዳት፣ እንዲሁም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ይህንን አስተያየት ከግምት እንደሚያስገቡት በማመን አቅርበነዋል። መልካም ንባብ።
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡



ግልጽ ደብዳቤ
ስለ  ነገዋ ቤተ ክርስቲያን ስንል ዕድሉ ዛሬ ባያመልጠንስ?
በዚህ ርእስ ለመጻፍ ስነሣሣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ደሙ ስለ መሠረታት፣ እስክ ኅልፈተ ዓለም እግዚአብሔርመንፈስ ቅዱስ ስለ ሚመራት፧ ከሁሉም በላይ ስለ ሆነች፧ ሐዋርያት ስለ ሰበሰቧት፧ ስለ አንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትንሽመናገር ፈልጌ ነው። አንዲት የሚለው አሐዳዊ ቅጽል ሦስት መቶ አሥራስምንት (318) ሊቃውንት እንደወሰኑት ዓለምአቀፋዊነቱን እንደያዘ ሆኖ ስለ እኛዋም ቤተ ክርስቲያን  “   አሐቲ» አንዲት የሚለው ቅጽል ከሀገርና ከሃይማኖት አንጻርይስማማታል። ስለዚህም ነው አንዲት እናት ቤተ ክርስቲያን የምንለው።

ለብዙዎቻችን የእናት ቤተ ክርስቲያን መካፋፈል የራስ ምታት፧ የሆድ ቁርጠት፧ የልብ ሕመም ወዘተሆኖ 21 ዓመታት  “   እኽ እኽ››  እያሰኘ መኖሩ በውስጡ ላለፈበት ትውልድ ሁሉ ግልጽይመስለኛል። ኢትዮጵያዊ ያውም ኦርቶዶክሳዊ ሆኖ፧ በሁለቱ ወገን ተከፋፍሎ  የአለ ሁሉ  “   ይህባይሆን ኑሮ» በማለት ሀሳቡን ያልገለጸና የማይገልጽ አለ ማለት አይቻልም።

“   ቀን ሲደርስ አምባ ይፈርስ» እንደሚባለው ሆነና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አርፈው፧ ብፁዕወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በሕይወተ ሥጋ በመኖራቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት እንዴት ይምምጣበሚለው ቃለ መጠይቅ ዙሪያ በመገናኛ አውታሮችም ሆነ ወይም በግል የመነጋገር ርእሰ ጉዳይ ከሆነአራተኛ ወሩን በማስቆጠር ላይ ይገኛል። በሕዝብ የመገናኛ አውታሮች በተለይም በጀርመንና በአሜሪካራዲዮ ጣቢያዎች ቃለ መጠይቅ የቀረበላችው አባቶችና ወንድሞች የሚናገሩት አስታያየት በከፊልየመለያያ ነጥብ በማንሳት ሀቁን ለመጠቆም ሲፈልጉ፥ የተወሰኑት ደግሞ ሀቁን በመተው ጊዜውን ብቻለመዋጀት የሚፈልጉ ሆኖ ተገኝቷል።

ከዚህ ላይ አንተ ከማን ወገን ሁነህ ነውእንዲህ የምትጽፍ የምትሉኝ ከሆነ፧  ችግሩ እንደተከሠተ ገናብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሳይሾሙ “ሳይቃጠል በቅጠል እንደሚባለው በአውሮፓ ደረጃ  ከጥቅምት 13-16.1984/23-26,10.1991/ በኮለኝ ከተማ ጉባኤ ቤተ ክርስቲያን ተካሂዶ ስድስት ዐበይትውሳኔዎችን ሲያስተላልፍ በሁለተኛ ተራ ቁጥር “የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ጉዳይ ኖዶሳችንብቻ ፍትሕ ርትዕ በተመላበት ሆኔታ ታይቶ በመጀመሪያ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማንያን፥ ቀጥሎም ለዓለም አብያተ ክርስቲያናት /ቤት ማኅበር እንዲገለጽ የሚል ውሳኔበጊዜው ረዳት ፓትርያርክ ለነበሩት ለብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስና ለቅዱስ ሲኖዶስ /ቤት እንዲደርስሲያደርግ “በሕመም ምክንያት የተባለውን ግን በቂ ምክንያት ነው ብሎ አልተቀበለውም። 

ሰሚ ጠፍቶ በኃያላኑ ጣልቃ ገብነት  ሹመቱ እንደተፈጸመ 1985/1992 . ላይ ስህተትሲደጋገም በሚል ርእስ በሰባት ገጽ የተጠቃለለ ከቅዱሳትና ከቀኖና መጻሕፍት ማስረጃዎችንበማጣቀስ የጻፍኩበትና በግልጽ ተቃውሞ ያሰማሁበት ስለሆነ ነው እንጂ “ሲመች በእጅ፣ ሲፈጅበማንካ እንደሚባለው አይደለም። ብዙዎች በፍርሃት ይሁን ወይም በይሉኝታ መንፈስ በተሸበቡበትዘመን   ይህ የቀኖና ድንጋጌ እስከ ተሻረ ድረስ የሚከፈለው መሥዋዕት ቀላል እንዳልሆነና አንድ እልባትሊደረግለት እንደሚገባ አበክሬ ተማኅጽኖ አቅርቤአለሁ። ጽሑፉ በጊዜው ጊዜ ብዙ የተባለለትከመሆኑም ባሻገር፧ በኢትዮጵያ የመጻፍና የመናገር ዕድል እንዳሁኑ ሳያከስም የተለያዩ የግል መጽሔቶናጋዜጦች አንዱ ካንዱ እየተቀባበሉ አውጥተውት ነበር። ሰሚ ግን አልተገኘም።

አሁን እንዲህ በአለ ጽሑፍ ላይ እንዳለፈው ስለነገረ ፓትርያርክ ምዕራፍ ከምዕራፍ፧ አንቀጽከአንቀጽ እያጣቀሱ ማስረጃ ለማቅረብ መሞከሩየአንባቢን ጊዜ መሻማት መሆኑን በመገንዘብ፧ሁሉን መዘርዘር ባያስፈልግም ፓትርያርክ እያለፓትርያርክ አይሾምም የሚለው ዐቢይ መሠረታዊአንቀጽ ግን እንዲህ ይነበባል። ይህች ሹመት(ፓትርያርክነትበአንድ ዘመን በአንድ ሀገርለሁለት ሰዎች ልትሆን አይገባም። ይህ በአንድሀገር ከተደረገ ግን አስቀድሞ ለተሾመው ትጽና።ካለ በኋላ ስለታመመ ፓትርያርክ ሲናገር ግንአእምሮውን ያጣ እንኳን ቢሆን ይድናል ብለውተስፋ የሚያደርጉ ከሆነ ይጠብቁት። ይድናልብለው ተስፋ ባያደርጉ ግን፧ የታመመበት ዘመንበጣም ጥቂት ቢሆን ከሹመት አይሻሩት። ከመዳንቢዘገይ ግን ይሻሩት። ... (ፍትሐ ነገሥት ፍትሕ መንፈሳዊ ዐቢይ  አንቀጽ 4 ንኡስ ቁጥር 70-78)

ቀኖናው በዚህ መልኩ ተቀምጦ ሳለ፣ ሀቁን ይዞ ችግሩን  በጋራ ውይይት መፍታት እስካልተቻለ ድረስመልአክ ከሰማይ እስከ ሚመጣ ድረስ መጠበቅ ያለብን አይመስለኝም። ከአኃት እብያተ ክርስቲያናትየሚበጀውን ልምድ መውሰድ፧ በጋራም ከስምምነት ላይ መድረስ  ነው። ይህ ሳይሆን ቀርቶስድስተኛውን ፓትርያርክ ለመምረጥ መዘጋጀት ለማገገም የቀረበውን ስብራት እንደገና ሰባብሮ ለመጣልከመጣደፍ የተለየ አይሆንም። ያለው ልዩነት በስምምነት ሳይፈታ፥ አጉራ ዘለሎች በሦስትኛና በአራተኛረድፍ በቆሙበት ሰዓት ሌላ ፓትርያርክ ከተሾመ እምቀዳሚቱ የሀኪ ደኃሪቱ ነውና ከቀደመው የባስይመጣል ብሎ መናገሩ ነቢይ የሚያሰኝ አይደለም።  እንግዲያውስ  ጌታ የሚለው  ኢትአብስ ዳግመ»ዳግመኛ አትበድል አይደል? የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስየፈጸመውን ጥፋት በጥሙና እንመልከተው።

1. በዘመነ ደርግ ከቀኖና ውጭ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ከመንበራቸው ሲወርዱ፥ ብሎም ለሞት አልፈው ሲሰጡ  ምንም ድምፅ አላሰማም።
2. በዘመነ ኢሕደግ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከመንበራቸው ሲወርዱ ከላይኛው ስህተትአልተማረም። እንዲያውም ስሙን ለውጦ ስህተቱን የሚያስፈጽሙለት አባቶች ሲመርጥ ኮሚቴ የሚልተራ ( የዓለምስም አውጥቶ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ስኖዶስ በ፭/5/ ሊቃነጳጳሳት ኮሚቴነት እንዲመራ ወሰነ። ብሎ መግለጫ ከሰጠ በኋላ፧ አቃቤ መንበር እንኳን ሳያስቀምጥ የሚሆነውን ሁሉ አደረገ። ቅዱስ ሲኖዶስ የራሱን ሕግ በራሱ ሲያፈርስ እጅግ ያሳዝናል።
3. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በሞተ ሥጋ ሲለዩ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ 21 ዓመታት የቆየውንከባድ ፈተና እግዚአብሔር አምላክ ሲያቀል እንደገና ወደ ፈተና ለመግባት በሩን ከፍቶ በመጠበቅ ላይይገኛል። ያው ቅዱስ ቃሉ እንደሚያዘው ለሦስተኛው ስህተት ግን ዕድል ሊሰጠው አይገባም። “   ንግራለቤተ ክርስቲያን» ነውና ማኅበረ ምእመናንና ማኅበረ ካህናት በአንድ ላይ ሁነው እግዚኦ በእንተአንድነት የሚሉበት ጊዜ አሁን ነው። የግለሰብ ጉዳይ ቢሆን ኖሮ እንደ ልማዳችን “ቢሰማህ ምከረው፣ባይሰማህ ግን መከራ ይምከረው» ብለን እናልፈው ነበር። ይህ ግን ከምንም በላይ ነው። ጉዳቱናመዳከሙ፥ በወንዝ መከፋፈሉ እንዳለ ሆኖ ቤተ ክርስቲያናችን ቀኖናዋ ተጥሶ እስከ መቼ የባዕዳንመሳለቂያና የብዕር ማሟሻ ሁና ትኖራለች።?  የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ለልጆቻቸው የሚያስተምሩትንእነርሱ ሠርተው ካላሳዩን ማነን ልንከተል እንችላለንአሁንም ኢትአብሱ ዳግመ ዳግመኛ አትበድሉእንበላቸው።  አንተስ ለምን ዳርዳር ትላለህ የሚለኝ ካለ በስደት ያሉት ፓትርያርክ በዘመነ ደርግየፈጸሙት በደል ኖሮ ከመንበረ ፐትረካናቸው የሚያሰወርድ በደል ከተገኘባቸው እንደ ብፁዕ አቡነመልከጼዴቅ  በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ይታይባቸው ባይ ነኝ።    

በዚህም ሆነ በሌላ “እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን  አንቅደም እያልን የምናሰተምር መምህራነ ወንጌል በሕመም ምክንያት ከዛሬ 21 ዓመት በፊት ከመንበረ ርክናቸው የወረዱት አባት በሕይወተ ሥጋእያሉ፣ የቁጥር ዶግማ እንዘ አሐዱ ሠለስቱ ወእንዘ ሠለስቱ አሐዱ አንድ ሲሆን ሦስት፣ ሦስት ሲሆንአንድ ነው ከሚለው ከምሥጢረ ሥላሴ ውጭ ሌላ የቁጥር ዶግማ ያለ ይመስል ነገሩ ስለ አራተኛውናስለአምስተኛው ፓትርያርኮች ቅደም ተከተል ለመግለጽ ተፈልጎ ነው አራት ተብሎ አምስት እንጂእንደገና አራት ስለማይባል ስድስተኛውን ፓትርያርክ እንመርጣለን በሚል በቁጥር ስድስት ምክንያትየተጣሰውን ቀኖና ላለመቀበል የአዲስ አበባው ቃል አቀባይ የማይሆን ምክንያት እየደረደሩልን ነው።የቅዱስ ሶኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤልና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ይህች ሹመት(ፓትርያርክነትበአንድ ዘመን በአንድ ሀገር ለሁለት ሰዎች ልትሆን አይገባም። ይህ በአንድ ሀገርከተደረገ ግን አስቀድሞ ለተሾመው ትጽና። የሚለውን በማናበብ እንዴት ከግንዛቤ ውስጥእንዳላስገቡት የሚያስተዛዝብ ነው። ምን አለእንደ አባቶቻችን “እውነትን ተናግሮ ከመሸበት ማደርየሚለውን ዘይቤ በክህነታዊ ሥራችን ብንተረጉመው።ካላይ እንደገለጽኩት እንዲህ በጠጠር ኃይለቃል የምናገረው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወርደው፥ በመንግሥት ሞተር የሚንቀሳቀሰውሲኖዶስ ገና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ከመሾሙ በፊት ስለተናገርኩት ብቻ ነው።
 

መቸም ሀቅ እንደ አሥር  ቁጥር ነቁጥ ነጠላ ሠረዝና ድርብ ሠረዝ የላትምና ሀቁን መፈለጉበእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የምትመራ ቤተ ክርስቲያን እንድትኖረን ብሎም በየቦታው አኩርፈውየተበታተኑትን  ሁሉ በአንድ ጥላ ሥር እንዲሰባሰቡ ያደርጋል። ያዘኑት ይጽናናሉ፧ የጠፉት ይገኛሉ።ባላገራ ሠይጣንም ለዘለዓለም ያፍራል።

ከዛሬ 21 ዓመት በፊት በበሽታ ምክንያት ከመንበራቸው የወረዱት አባት በሕይወተ ሥጋ እያሉ ሙሉጤነኛ ተብለው በመንበሩ የተቀመጡት አባት በሞተ ሥጋ ሲለዩ ያለሆነ ምክንያት ከማቅረብ ይልቅወይኩን ፈቃድከ እንደ ፈቃድህ ይሁን በሚለው አምላካዊ ትእዛዝ ተመርቶ መንበሩን ለባለ መንበሩማስረከብ ተገቢ ነው። በዚያውስ ላይ ማን ቀሪ አለና ነውከሀቅ የሚያሸሸን፧ ከዚህ ላይ የአገሬአስለቃሽ የሙሾ ግጥም ትዝ አለኝ
                በሉ እናንተም ሂዱ እኛም ወደዚያው ነው።
                 ወትሮም መንገዳኛ ፊትና ኋላ ነው። /ከዚህ ላይ በገጠሯ ኢትዮጵያ ያለውንቀጭን የእግር መንገድ ልብ ይሏል/
 
ወደ ተለመደው ስብከቴ ልመለስና ለማንም የማያዳላው የሞት ጽዋ ከፊታችን ተደቅኖ በሚያልፈውየማያልፈውን ፍቅር አንድነት እንዴት አናጣለን?  የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ድምፅ እናዳምጥ።ከታሪክ ተወቃሽነትም እንዳን። ለአንዲቱ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ንጹሕ ኅሊና፧ ሰፊልቡና ይኑረን። “ከመቶ ሃምሳ ዳዊት፣ አንድ የልብ ቅንነት ይሉየል አባቶች፧ ስለ  ነገዋ ቤተ ክርስቲያንስንል ዕድሉ ዛሬ አያምልጠን እያልኩ እማጸናለሁ፣ እጮህ አለሁም።       
21 ዓመት ተሞክሮ ቀላል አይደለምና አሁንም ሕዝበ ክርስቲያኑና ማኅበረ ካህናቱ ያላወቁትየተለመደው ከባድ እጅ ካለበት ሀቁ ይነገረንና እርማችን እናውጣ። በጸሎትም እንበርታ። በሰውየማይቻለው በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላልና። እግዚኦ በእንተ አንድነት እንበል።

አባቶች እንደዚህ ያለ የጋራ መከራ ሲያጋጥማቸው “የጨው ክምር ሲናድ ሞኝ ይልሳል ብልህያለቅሳል። ይላሉ። እንግዲህ እኛ ሁላችን ኦርቶዶክሳውያንና ኦርቶዶክሳውያት ምእመናትናምእመናት በተለይም መንጋውን ለመጠበቅ የተሾምን ካህናትና ሊቃነ ካህናት መነኮሳትና ቆሞሳትአበወ ምኔታትና ኤጲስቆጶሳት፣ ጳጳሳትና ሊቃነ ጳጳሳት  ከየትኛው ክፍል ነንበዛሬዋ ቤተክርስቲያናችን ውስጥ ሁነን ስለ ነገዋ ቤተ ክርስቲያን ምን ገዶን የምንል ከሆነ ለልጅ ልጅ የሚከፈል ዕዳገና አለብን።  ከዚህም እግዚአብሔር አምላክ ይሠውረን። ሴት አያቴ “ጭንቅ አቃላይዋ የምትላትየሁላችን እመቤት ቅድሰተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ታማልደን።  አሜን።

ሊቀ ካህናት / መርዓዊ ተበጀ
ጀርመን፧ ኮለኝ

ይህ ግልጽ ደብዳቤ
ለአቃቤ መንበረ ፓትርያርክ  ለብፁዕ አቡነ ናትናኤል
ለቅዱስ ሲኖዶስ /ቤት
ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ /ክህነት /ቤት
ለመንበረ ፓትርያርክ  የውጭ ጉዳይ መምሪያ
ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ላልኩአቸው አካላትና ግለሰቦች እንዲሁም ለመገናኛ ክፍሎች ሁሉ ተልኳል።

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment