Tuesday, December 25, 2012

ከአዲስ አበባ ቅ/ሲኖዶስን ወክሎ የመጣው ልዑክ የሰላምና አንድነት ጉባኤውን መግለጫ ተቃወመ

  •    አስታራቂ ጉባኤው ይቅርታ ካልጠየቀ በውይይቱ አንሳተፍም ብሏል፤
(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 16/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 25/2012/READ THIS IN PDF)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አባቶች መካከል የተጀመረው ዕርቀ ሰላም ከግብ እንዳይደርስ “የ6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ” ጉዳይ እንዲቀጥል አስመራጭ ኮሚቴ መቋቋሙን ተቃውሞ የሰላምና አንድነት ጉባኤው ራሱ ጠንካራ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። በተለይም አዲስ አበባ ያሉት አባቶች ጉዳዩን በጥሙና እንዲያስቡበት ያሳሰበው ጉባኤው ይህ ሁሉ ልፋት መና እንዳይቀር ተማጽኗል።
ይህንኑ ደብዳቤ በጽሙና የተቃወሙት ከአዲስ አበባ የመጡት ልዑካን ዛሬ ለደጀ ሰላም በላኩት መግለጫ “የሰላምና የአንድነትጉባኤ ያወጣው መግለጫ የተሳሳተ መሆኑን አበክሮ ገልጿል። 



የሰላምና የአንድነት ጉባኤው ታሕሣሥ12 ቀን 2ዐዐ5 . ያወጣው መግለጫ በዘለፋ የተሞላ፣ የቅዱስ ሲኖዶስን ሉዓላዊነት  
የተዳፈረ፣ሚዛናዊነትን ያልተከተለ፣ አሳሳች ትርጉም የሰጠ፣ የአደራዳሪ ወይም የአስታራቂ መርህን የጣሰ፣የተጀመረውን የሰላም ጉዞ  
የሚያደናቅፍ” ነው ብሎታል። አክሎም “ከሁ በላይ የሚያስገርመው ነገርቢኖር ሁለታችንም የጉዳዩ ባለቤቶች ከቅዱስ  
ዶስ ውሳኔ ሉዓላዊነት በመለስ የሰላሙ ጉዞ እንዳይደናቀፍ ጠብቀን በምንገኝበት በአሁኑ ጊዜ አስታርቃለሁ እያለ የሚገኝ  
አካል ሆን ብሎ የሰላሙንሂደት ለማደፍረስ ይህን ያህል የቸኮለበት” ጉዳይ ምሥጢር እንደሆነበት የልዑካኑ ቡድን ጠቅሶ በውይይቱ ወቅትም ይኸው አስታራቂ ኮሚቴ ወገንተኝነት ሲያሳይ መቆየቱን ጨምሮ ጠቅሷል።

አክሎም “ኮሚቴው ይህንን ስህተቱን በግልጽ አምኖ ይቅርታ የማይጠይቅ ከሆነና ኃላፊነቱን በአግባቡካልተወጣ ከዛሬ ጀምሮ  
ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ኮሚቴ አማካኝነት ለመደራደር ፈቃደኛእንደማትሆን ሊታወቅ ይገባል” የሚል ጠንካራ አቋም አንቀባርቋል። የመግለጫውን ሙሉ ቃል ከዚህ በታች እንድትመለከቱ እንተይቃለን።

ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን።




በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
የኢትዮጵ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሰላምና የአንድነትጉባኤ ያወጣውን የተሳሳተ 
 መግለጫ አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ
ወአልቦ ማኅለቅት ለሰላሙ  ለሰላሙ ፍጻሜ የለውም፡ ኢሳ. 97

የኢትዮጵ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ልኡክ ሰላምና አንድነት ለመወያየትከኅዳር 28 እስከ 3 ቀን  
2ዐዐ5 . በዳላስ ቴክሳስ ጉሳኤ ተገኝቶ ስለሰላምና አንድነት ሥምረትበተካሄደው ስብሰባ የበኩሉን ጉልህ ሚና መጫወቱ ይታወሳል፡፡ስለ ሰላሙ ሥምረት ያለውንም አቋም ሁለታችን ወገኖች በጋራ ባወጣነው መግለጫ በግልጽተቀምጧል፡፡  
ለወደፊትም ለሰላሙ መሳካት ያለውን ፍላጎት በጋራ መግለጫው በሚገባ ተገልጿል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ የሰላምና የአንድነት ጉባኤው ታሕሣሥ 12 ቀን 2ዐዐ5 . ያወጣው መግለጫ በዘለፋየተሞላ፣የቅዱስ ሲኖዶስን  
ሉዓላዊነት የተዳፈረ፣ ሚዛናዊነትን ያልተከተለ፣ አሳሳች ትርጉም የሰጠ፣የአደራዳሪ ወይም የአስታራቂ መርህን የጣሰ፣ የተጀመረውን  
የሰላም ጉዞ የሚያደናቅፍ ሆኖ ስለተገኘየቅዱስ ሲኖዶስ ልኡክ ይህንን መግለጫ ለማውጣት ተገዷል፡፡

በመሠረቱ የጉባኤው ኮሚቴ ከመጀመሪያው ቀን አንሥቶ እንደዚህ ያለ ሚዛናዊነት የጎደለው አዝማሚያእየተከተለ እንደመጣ 
 በየጊዜው ያወጣቸው መግለጫዎችና መፍትሔ ናቸው ብሎ ያቀረባቸው ሐሳቦችምስክሮች ናቸው፡፡
ይህን ቅንነትና ሚዛናዊነት የጎደለው አካሄድና አመለካከት እንዲያርም በልኡኩ በኩል ተደጋጋሚማሳሰቢያዎች እንደተሰጡት  
በአንደበቱ ቢክድ እንኳ ኅሊናው እንደሚረታው እርሱ ራሱ አይስተውም፡፡

ከሁ በላይ የሚያስገርመው ነገር ቢኖር ሁለታችንም የጉዳዩ ባለቤቶች ከቅዱስ ዶስ ውሳኔሉዓላዊነት በመለስ የሰላሙ ጉዞ  
እንዳይደናቀፍ ጠብቀን በምንገኝበት በአሁኑ ጊዜ አስታርቃለሁ እያለየሚገኝ አካል ሆን ብሎ የሰላሙን ሂደት ለማደፍረስ ይህን  
ያህል የቸኮለበት ምሥጢር ምን እንደሆነሊገባን አለመቻሉ ነው፡፡

ይሁንና እስከ አሁን ድረስ ባይገባንም አሁን ግን ከመግለጫው ይዘትና መንፈስ አንጻር ስናስተውልሰላሙ እንዲመጣ ያልፈለገ  
የሰላም ጉባኤ ኮሚቴው ራሱ እንደሆነ በአንደበቱ መስክሮ አረጋግጦልናል፡፡የጉባኤው ኮሚቴ በቅዱስ ሲኖዶስ ላይ በሰነዘረው  
የድፍረት ድፍረት የሰላሙ ሂደት ቢሰናከልተጠያቂው እርሱ ራሱ መሆኑን ሊገነዘብና በግልጽ ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል፤ ኮሚቴው  
ይህንንስህተቱን በግልጽ አምኖ ይቅርታ የማይጠይቅ ከሆነና ኃላፊነቱን በአግባቡ ካልተወጣ ከዛሬ ጀምሮ ቤተክርስቲያናችን በዚህ  
ኮሚቴ አማካኝነት ለመደራደር ፈቃደኛ እንደማትሆን ሊታወቅ ይገባል፡፡

ይህም ማለት የማስታረቅ ልምድና ብቃት ያለው፣ ፍጹም ገለልተኛና ለቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነትበሐቅ የሚቆረቆር፣  
ሚዛናዊነት ያልተለያቸው የተለያዩ የመፍትሔ ሐሳቦችን በማፍለቅ ማግባባትየሚችል ወገን ሲገኝ ቤተ ክርስቲያናችን የሰላም  
በሯን ትዝጋለች ማለት አለመሆኑን የቤተክርስቲያናችን ተከታዮችና ወዳጆች ሁሉ በግልጽ ሊያውቁት ይገባል፣ ምክንያቱም  
እግዚአብሔር ራሱለሰላም ፍጻሜ የለውም ብሎ ነግረናልና፡፡

በመጨረሻም ማንኛውም ለእውነት የቆመ ወገን ሁለታችን ወገኖች በጋራ ያወጣነው መግለጫ፣የጉባኤው ኮሚቴ ካወጣው  
መግለጫ ጋራ ምን ያህል እንደሚቃረንና የቅዱስ ሲኖዶስን ሉዓላዊሥልጣን እንዴት እንደሚዳፈር ቃል በቃል በማነጻጸር መረዳት  
እንደሚቻል እያስገነዘብን ቤተክርስቲያናችን ለሰላም ሲባል እስከአሁን ባደረገችው ጥረት ከግማሽ መንገድ በላይ እንደተጓዘች 
 ሁሉአሁንም ለሰላሙ ሥምረት እጇን እንደማታጥፍ ለሰላም ወዳጅ ወገኖቻችን ሁሉ አበክረን እንገልጻለን፡፡
ወአልቦ ማህለቅ ለሰላሙ
1.              አባ ገሪማ ዶክተር የብፁዕ ወቅዳስ ፓትርያርክ ልዩ /ቤት የውጭ ግንኙነት የበላይ ኃላፊ ሊቀጳጳስ፣
2.             አባ አትናቴዎስ የደቡብ ወሎ /ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣
3.             አባ ቀውስጦስ በሰሜን ሸዋ የሰላሌ /ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣
4.             ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ የመ////ቤት መንፈሳዊ ዘርፍ //አስኪያጅ፣

ታህሣሥ 13 ቀን 2ዐዐ5 .
ዋሽንግተን ዲስ፣ አሜሪካ

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment