Monday, December 31, 2012

ላስ ቬጋስ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን ለቅ/ሲኖዶስ የተማጽኖ ጥሪ አቀረቡ



(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 22/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 31/2012/ PDF)፦ በአሜሪካ ላስ ቬጋስ ከተማ የምትገኘው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋዶ የሐመረ ኖኅ ኪዳነምሕረት ወቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምዕመናን ወቅታዊውን የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ አስመልክቶ የተማጽኖ መግለጫ አወጡ፣ ለቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት እንዲደርስላቸውም ጠየቁ በእርቀ ሰላም የተጀመረውን ወደ አንድነት የመምጣት ጭላንጭል ማክሰም ለሚቀጥሉት የማይታወቁ አያሌ ዘመናት የምእመናንን አንገት የሚያስደፉ ሁኔታዎች እንደሚፈጥር ግልፅ ነው” ያለው መግለጫው ብፁዓን አባቶች ዕርቀ ሰላሙን ከግብ እንዲያደርሱ ጠይቋል፡፡ የመግለጫውን ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ተመልከቱ።
ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን።

 የተፈረመበትን የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ ይህንን ይጫኑ።

ከአሥር የማያንሱ ሊቃነ ጳጳሳት አስመራጭ ኮሚቴ በመመረጡ አይስማሙም


·            ወጣቶቹ ሊቃነ ጳጳሳት እንዲህ መስመር የሣተ አቋም የያዙበት ምክንያት ምንድር ነው? አረጋውያኑን በማስፈራራትም፣ በመናቅም የሚገፉት እስከመቼ ነው?
·            አሜሪካ ለዕርቅ የተጓዘው ልዑክ ሪፖረቱን ነገ ማክሰኞ ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፤
 (ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 22/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 31/2012/ PDF)፦ ከመንግሥት ጋር ቃል እንደተገባቡ የሚነገርላቸው ጥቂት ሊቃነ  ጳጳሳት “ቤተ ከህነቱን ተቆጣጥረናል፣ ከመንገዳችን  የሚገታን አይኖርም” ሲሉ እየተሰሙ ባሉበት በአሁኑ ወቅት ቁጥራቸው ከ10 የማያንስ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የፕትርያርክ መሾሙን እሽቅድምድም እንደማይስማሙበት በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡ መንግሥትም በበኩሉ የሰላምና የዕርቅ ኮሚቴውን ልዑክ በሚሳዝን ሁኔታ ከሀገር በማባረር በግልጽና በአደባባይ ለዕርቁ እንቅፋት መሆኑን በድርጊቱ አረጋግጧል፡፡ በአንድ በኩል የሃይማኖት ነጻነትን እየሰበኩ በሌላ በኩል ልዑካንን ማሰር ማንገላታት ብዙዎችን አሳዝኗል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶሱ የማን ነው? የእኛ ነው ወይስ?


(ከመልዕክተ ተዋሕዶ - ዘሮኪ/ PDF)፦ እንግዲህ ላለፉት 20 ዓመታት ከችግራችን ጋር ተወልዶ፥ ያደገው መንግሥት ፥ አቋሙን በግልጽ አሳውቆናል።  “ነገ ልትዳሪ ነው ሲሏት፥ ካልታዘልኩ አላምንምእንዳለችው ሙሽራ መሆኑ ይብቃን፥ እርማችንን እናውጣ። ስለ ነገ እናስብ፥ ስለ ቤተ ክርስቲያን እናስብ፥ ስለ አባቶቻችን እናስብ። የግዴታ ማክሰኞን መጠበቅ ያለብን አይመስለኝም።
ቅዱስ ሲኖዶስ በመጪው ማክሰኞ  በሚያደርገው ስብሰባ ላይ፥ ካስታወሰን መልዕክታችንን መነጋገር ያለብን፥ ዛሬንና ነገ ብቻ ነው። የመንግሥትን አቋም ባይገርመንም የሚጠበቅ ስለሆነ ሰምተነዋል። የቅዱስ ሲኖዶስ ግን ማክሰኞ ይለይለታል። ቅዱስ ሲኖዶስ የማነው ወይ የኛ የኦርቶዶክስያዊያኑ ነው! አለበለዚያ፥ ተጠሪነቱ በቀጥታ ለመንግሥት ነው። እንደኔ እንደኔ  የቅዱስ ሲኖዶስም ቢሆን፥ ግልጽ ይመስለኛል።  ይህንን ለመረዳት፥ ወደ ፊት ሁለት ቀን ጠብቆ ማየት ሳይሆን፥ ወደ ላ ብዙ ዓመታትን ማስታወስ ይበቃል። ያለፉትን ሁለት ሶስት ሳምንታት ብቻ እንኳን ስርመረምሩ፥ እውነታው ቅዱስ ሲኖዶስ ከመንግሥት ፍላጎት ውጪ አንድ ቀን እንኳን በነጻ አስተሳሰቡ ውሎ ማደር እንዳልቻለ ግልጽ ነው። ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ የቅዱስ ሲኖዶስ አካሄድን ነቅፈው፥ መሆን ያለበትን ተናግረው ውለው ሳያድሩ የደንነት ክፍሉ ኃላፊ “ንቡረ ዕድኤልያስ አብርሃ ዝም ነው ሰኟቸው። በግዴታም ፈረሙ። ነገ ወደ አገር መግቢያ የላችሁም ተባሉ። ተስማሙም። ይህ በቂ አይመስላችሁምን? ጠብቀን እንስማው፥ ካላችሁ ግን ፥ ታገሱ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ዓላማውን ግልጽ አድርጓል፤ እኛም አውቀናል


  • የመንግሥት ደጋፊ የጡመራ መድረኮች “አስታራቂ ኮሚቴው” ላይ ዘምተዋል፤
  • ከጳጳሰቱ መካከል የዕርቁ እንቅፋት የሆኑት አባቶች በግልጽ ታውቀዋል፤ ስማቸውን ከማውጣታችን በፊት አሁንም ሐሳባቸውን ይቀይሩ እንደሆነ እንጠብቃቸዋለን፤
  • ጉዳዩን ያቀነባበሩት የአዲስ አበባው ልዑክ አባል የሆኑት ን/ዕድ ኤልያስ አብርሃ ናቸው ተብሏል፤
  • የአዲስ አበባው ልዑክ አባቶች ዲሲ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ከተጠሩ በኋላ ተገደው እንዲፈርሙ ተደርገዋል፤
(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 20/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 29/2012/ PDF)፦ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ጣልቃ አልገባኹም በሚል ሰሞኑን መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ መንግሥት ለዕርቁ ጉዳይ ከቅ/ሲኖዶስ ጋር ለመነጋገር ወደ አዲስ አበባ የሄዱትን የሰላምና አንድነት ጉባኤውን አባል ሊቀ ካህናት ኀ/ሥላሴ ዓለማየሁን አስሮ ወደ አሜሪካ ከላካቸው ወዲህ ለዕርቁ ያለው የተስፋ ደጅ መዘጋቱ እሙን ሆኗል። መንግሥት የዕርቁ ድርድር ለይስሙላ እንጂ “ከምር” እንዲሆን አልፈለገም ነበር።
ነገሩ ከምር ሲሆን ግን “የጭቃ ጅራፉን” መምዘዝ ይዟል። ለዲፕሎማሲ ይጠቅመኛል ብሎ የፈቀደው ዕርቅ መሰካት ሲጀምር ከዲፕሎማሲው ከማገኘው ትርፍ በሩን መዝጋት ይሻለኛል ያለ መስሏል። የራሱን ፓርቲ አባል በፓትርያርክነት ለማስቀመጥ በጠራራ ፀሐይ ወረራውን ቀጥሏል።  

የኢትዮጵያ መንግሥት ሊ/ካ ኃ/ሥላሴ ዓለማየሁን በግድ ወደ አሜሪካ መለሳቸው


  •     Listen VOA Interview
  •    ዲፖርት አደረጋቸው፤ 
  •     ጉዳዩን ያቀነባበሩት የአዲስ አበባው ልዑክ አባል የሆኑት ን/ዕድ ኤልያስ አብርሃ ናቸው ተብሏል፤
(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 20/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 29/2012/PDF)፦ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ጣልቃ አልገባኹም በሚል ሰሞኑን መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ መንግሥት ለዕርቁ ጉዳይ ከቅ/ሲኖዶስ ጋር ለመነጋገር ወደ አዲስ አበባ የሄዱትን የሰላምና አንድነት ጉባኤውን አባል ሊቀ ካህናት ኀ/ሥላሴ ዓለማየሁን አስሮ ወደ አሜሪካ መለሳቸው። እዚያው አስሮ ያላስቀራቸው አሜሪካዊ ዜግነት ስላላቸው ነው ተብሏል። ከእርሳቸው ጋር ለዚሁ ጉዳይ ወደ ኢትዮጵያ የሄደው የሰላምና አንድነት ጉባኤው ሌላ አባል ዲ/ን አንዱዓለም ዳግማዊ ስላለበት ሁኔታ አልታወቀም። ዝርዝሩን እንደደረሰልን እናቀርባለን። 
ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን።

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

Wednesday, December 26, 2012

የዴንቨር ደብረ ሰላም መድኅኒዓለም ያወጣው መግለጫ


ቀን ታህሣሥ 14, 2005 . .
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

·         ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ - አዲስ አበባ 
·         ለሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብጹአን አባቶች - አሜሪካ
·         ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራዲያዊ ሪፖብሊክ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ - አዲስ አበባ

Tuesday, December 25, 2012

ከአዲስ አበባ ቅ/ሲኖዶስን ወክሎ የመጣው ልዑክ የሰላምና አንድነት ጉባኤውን መግለጫ ተቃወመ

  •    አስታራቂ ጉባኤው ይቅርታ ካልጠየቀ በውይይቱ አንሳተፍም ብሏል፤
(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 16/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 25/2012/READ THIS IN PDF)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አባቶች መካከል የተጀመረው ዕርቀ ሰላም ከግብ እንዳይደርስ “የ6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ” ጉዳይ እንዲቀጥል አስመራጭ ኮሚቴ መቋቋሙን ተቃውሞ የሰላምና አንድነት ጉባኤው ራሱ ጠንካራ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። በተለይም አዲስ አበባ ያሉት አባቶች ጉዳዩን በጥሙና እንዲያስቡበት ያሳሰበው ጉባኤው ይህ ሁሉ ልፋት መና እንዳይቀር ተማጽኗል።
ይህንኑ ደብዳቤ በጽሙና የተቃወሙት ከአዲስ አበባ የመጡት ልዑካን ዛሬ ለደጀ ሰላም በላኩት መግለጫ “የሰላምና የአንድነትጉባኤ ያወጣው መግለጫ የተሳሳተ መሆኑን አበክሮ ገልጿል። 


Monday, December 24, 2012

የብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ወቅታዊ ቃለ መጠይቅ

ዕንቁ ፡- ብፁዕ አባታችን ስለ እድገትና ትምህርትዎ በአጠቃላይ ስለ ራስዎ ይንገሩን ?

ብጹእ አቡነ ሕዝቅኤል፡- የቀድሞ ስሜ መልአከ ምህረት አባ መኮንን ሀብተማርያም ይባላል፡፡ከአባቴ መሪጌታ መኮን ኃይሉና ከእናቴ ወ/ሮ አታላይ ደርሰህ ግንቦት 7 ቀን 1948 ዓ.ም በደበቡብ ወሎ አማራ ሳይንት ልዩ ስሙ ደብረ ብርሃን ለንጓጥ ሥላሴ በተባለው ቦታ ተወለድኩ፡፡ ከሙሉጌታ አበበ እሸቴ ከፊደል እስከ ዳዊት በተወለድኩበት ደብር ከተማርኩ በኋላ በዚያው በአማራ ሳይንት ደራው መድኃኒዓለም ከመሪ ጌታ አፈወርቅ ሳህሉ ቁም ዜማ አቋቋም ፤ ቦረና ቅዱስ ቂርቆስ ደብር ከመጋቤ ምስጥር ደስታ ብዙነህ ቅኔ ከነ አገባቡ ተምሬአለሁ፡፡

ከብጹዕ አቡነ ገብርኤል በ1956 ዓ.ም የዲቁና ማዕረግ ተቀብያለሁ፡፡ ከዚያ ጎጃም መርጡ ለማርያም ከየኔታ ኢሳያስ ቅኔ ከነ አገባቡ ፤ ከመምህር ሀብተ ኢየሱስ መጽሐፈ ነገስት ትርጓሜና የቅኔ መንዶችን ፤ ደብረ መድሃኒት መድኃኒዓለም ከየኔታ አስካል የቅኔ መንገዶችን ከነ አገባቡ ፤ ብቸና ቅዱስ ጊዮርጊስ ከየኔታ ፍሰሐ ወልደሚካኤል ምስጢርና የቅኔ ሙያን አዳብሬያለሁ፡፡ ከየኔታ ፍስሀ ወልደ ሚካኤል በ1969 ዓ.ም በቅኔ መምህርነት ተመርቄአለሁ፡፡

Saturday, December 22, 2012

ቅድሚያ ለእርቀ ሰላም ከሰሜን አሜሪካ ሰንበት ት/ቤት አንድነት ጉባኤ



በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ቅድሚያ ለእርቀ ሰላም!

ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ /ቤት
   አዲስ አበባ
የተከበራችሁ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አባቶቻችን፣ በቅድሚያ ቡራኬያችሁ ይድረሰን። ቤተ ክርስቲያናችን ለሁለት አሥርት ዓመታት በፈተና ውስጥ እንድትቆይ ያደረገውን የልዩነት ግድግዳ አፍርሶ አንድ ሲኖዶስ፣ አንድ ፓትርያርክ፣ አንድ አስተዳደር እንዲኖራት ለማድረግ የተጀመረውን የእርቀ ሰላም ዓላማ በመደገፍ ልዑካንን በመሰየም የጀመራችሁት ሂደት አስደስቶናል። ነገር ግን የእርቀ ሰላሙ ሂደት ሳይጠናቀቅ ወደ ፓትርያርክ ምርጫ ጉዞ መጀመሩ በእጅጉ እንድናዝን አድርጎናል።
እንደሚታወቀው በአሁኑ ወቅት በሰንበት /ቤት ውስጥ የምንገኝ ወጣቶች አብዛኛው ዘመናችንን ያሳለፍነው ቤተክርስቲያናችን  በሁለት ሲኖዶስ ተከፍላ የልዩነት፣ የውግዘት እና የመራራቅ ባዕድ ሥርዓቶችን ስናስተናግድ ነው። ይህም በሰንበት /ቤት ተሳትፎ ለቤተክርስቲያናችን የሚገባውን አገልግሎት እንዳንሰጥ ትልቅ መሰናክል ሆኖ ቆይቷል። ቢሆንም ጊዜው ደርሶ የተጀመረው የእርቀ ሰላም ሂደት ትልቅ ተስፋ ሰጥቶን ነበር። ነገር ግን በተቃራኒው እየተከናወነ ያለው የፓትርያርክ ምርጫ ጉዞ የተቀረ ዘመናችንን በተስፋ እና በበለጠ መነሳሳት እንዳንጓዝ እያደረገን ይገኛል።

“ከፓትርያርክ ምርጫ - ዕርቅና አንድነት ይቅደም” ስንል ምን ማለታችን ነው?



(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 12/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 21/2012/PDF)፦ እንደሚታወቀው ቤተ ክርስቲያናችን በመስቀልያ መንገድ ላይ እንደምትገኝ ተደጋግሞ የተገለጸ ነው ዋነኛዎቹ ርዕሰ ጉዳዮች ሁለት ናቸው። የመጀመሪያው ለ20 ዓመታት በውግዘት የተለያዩ አባቶች አንድ እንዲሆኑ፣ አንዲት ቤተ ክርስቲያን፣ አንድ አስተዳደር፣ አንድ ቅ/ሲኖዶስ እንዲኖረን ማድረግ ነው። ለዚህም “ተስፋ ሰጪ” ሁኔታ ላይ ተደርሷል። ይህ ዳር እንዲደርስ እናድርግ። ሁለተኛው ደግሞ 20 ዓመት ለቆየው መለያየት ዓምድና ምልክት የነበረው የፕትርክናው ሥልጣን አንዱ የመወያያ አጀንዳ ስለሆነ ከዕርቁ በፊት ሌላ እርምጃ አይደረግበት የሚለው ነው። ይህንን በሚጋፋ መልኩ በጥቂት የቅ/ሲኖዶስ አባላት ግፊትና በመንግሥት ተጽዕኖ 6ኛ ፓትርያርክ ለመሾም “አስመራጭ ኮሚቴ” ተቋቁሟል። ሁለቱ አጀንዳዎች የሚገናኙት እዚህ ላይ ነው።

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ።



ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፤ በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን።”
      (DEC. 21/2012ታኅሣስ 12/2005 ዓ/ም/PDF):- በዚህ ታሪካዊ የዕርቀ ሰላም ንግግር ላይ ከኢትዮጵያና ከአሜሪካ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተሰይመው የተላኩት ልዑካን በፍጹም መከባበር ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሰላምና አንድነት በስፋት ተወያይተዋል።

በውይይቱም ወቅት ሁለቱም ወገኖች ከላካቸው አካል ይዘውት የመጡትን መሠረተ ሐሳብ በሰፊው የተነጋገሩበት ሲሆን የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ አገራቸው መመለስ ለዕርቀ ሰላሙ ስኬታማነት ዋነኛ መሠረት መሆኑን በጋራ ተስማምተዋል። ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ ልዑካን በኩል የቀረበው ዋና ሐሳብ “ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ ቅድስት አገራቸው ገብተው፣ ክብራቸው ተጠብቆና የሚያስፈልጋቸው ሁሉ ተሟልቶላቸው እርሳቸው በፈለጉት ቦታ ይኑሩ”፤ የሚል ሲሆን የዚህ ፍሬ ሐሳብ አመክንዮ ደግሞ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ መንበራቸው ቢመለሱ ታሪክ ይፋለስብናል የሚል ነበር።  

ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ መነሻ በማድረግ በዋሸንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የተሰጠ መግለጫ



የቤተ ክርስቲያንን አንድነት መጠበቅ እና ማስጠበቅ መንፈሳዊ ግዴታችን ነው። 
(ታኅሳስ 13  2005 ዓ. ም/ PDF):- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የራሷ መንበረ ፕትርክና ከማግኘቷ በፊት ለ 1600 ዓመታት ከግብጽ በሚመጡ ሊቃነ ጳጳሳት በመንበረ ማርቆስ ሥር ስትተዳደር መቆየቷ ይታወሳል ። በእነዚህ ባሳለፈቻችው ዘመናት የቤተ ክርስቲያን አንድነት እንዲጠበቅ በነበራት ጽኑ አቋም ብዙ መስዋዕትነት ከፍላለች። ችግር በገጠማትም ጊዜ ከግብጽ የሚመጡ አባቶች ሲቀሩባት እንኳን  ስለ አንዲት ቤተ ክርስቲያን ምስክርነቷን እየሰጠች ፤ በርካታ ሊቃውንትን ፤ በቅድስና የከበሩ አባቶችን  ይዛ ፤ ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት ስትል ግን ከመንበረ ማርቆስ ሊቃነ ጳጳሳት እንዲላኩላት ስትማጸን ኖራለች።
በተለይም “ ወሰብአ ኢትዮጵያ ኢይሢሙ ላዕሌሆሙ  ሊቀ ጳጳሳት እማእምራኒሆሙ ወኢበሥምረተ ርእሶሙ” ኒቅያ   ፵፪፡ ፶  የሚለውን  ምንባብ በማንሳት  ፤ በሥርዋጽ የገባ መሆኑን ለማስረዳት አድካሚና ተደጋጋሚ ጉዞ ወደ ግብጽ በማድረግ  ፤ መጽሐፋዊና ታሪካዊ ማስረጃን በማቅረብ በመንበረ ማርቆስ ለሚገኙ አባቶች ችግሩን በማስረዳት በውይይት ለብዙ ዘመናት እንደ ተራራ ገዝፎ የተቀመጠውን ችግር በማቅለል  የቤ ክርስቲያን አንድነት እንደተጠበቀ የራሷ መንበረ ፕትርክና እንዲኖራት አድርገዋል ። የቀደሙት አባቶችቻን በተግባር ያስተማሩን ትምህርት የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለመጠበቅ ሲባል የማይከፈል መስዋዕትነት አለመኖሩን ነው። ዛሬም የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚፈታተኑ፤ መዋቅራዊ አንድነቷን የሚያናጉ፤ አለመግባባትና መለያየትን የሚፈጥሩ ችግሮች  በተለይም  በሰሜን አሜሪካ  እየታዩ መምጣታቸው  ፤ ትክክለኛ ፍርድ እና ውሳኔ የሚጠይቁ ጉዳዮች መብዛታቸውን ስንመለከት፤ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ እና ሃይማኖታዊ አመራር መዋቅራዊ ተዋረዱን ጠብቆ መጠናከር እንዳለበት ያስገነዝበናል። እኛም በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት የምንገኝ አብያተ ክርስቲያናት የቤተ ክርስቲያን መዋቅር ይጠበቅ በማለት በተደጋጋሚ ለቅዱስ ሲኖዶስ በማሰማት ላይ የምንገኘው ይህንኑ ችግር ለማቃለል እገዛ እንዲያደርግ ነው

Friday, December 21, 2012

የቅ/ሲኖዶሱ አባላት በውሳኔያቸው ተከፋፍለዋል


  • የዕርቀ ሰላሙ ልኡካን በሲኖዶሱ ውሳኔ ላይ የወሰዱት አቋም በመንሥኤነት ተጠቅሷል
  • ‹‹ይኾናል ብለን አንጠብቅም፤ ኾኖ ከተገኘ በጣም እንቃወማለን›› /አቡነ አትናቴዎስ/
  • ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ከሲኖዶሱ ስብሰባና ውሳኔዎች ራሳቸውን አግልለዋል
  • ዋና ጸሐፊው ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ፈቃደኛ አልኾኑም
  • ማኅበረ ቅዱሳን በዕርቀ ሰላሙ እና በፓትርያሪክ ምርጫ አጣባቂኝ ውስጥ ገብቷል
የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ትላንት፣ ታኅሣሥ 10 ቀን 2005 ዓ.ም ከቀትር በኋላ የፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንብ አጽድቆ ምርጫውን የሚያስፈጽም 13 አባላት ያሉት አስመራጭ ኮሚቴ ሠይሟል፡፡ የኮሚቴው አባላት ከቅ/ሲኖዶስ አባላት፣ ከመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ መምሪያ ሓላፊዎች፣ ከገዳማት አበምኔቶች፣ ከሰንበት ት/ቤቶች አንድነት፣ ከመንፈሳውያን ማኅበራት እና ከታዋቂ ምእመናን ‹‹የተውጣጡ ናቸው›› ተብሏል፡፡
የኮሚቴውን መቋቋም ተከትሎ ለዕርቀ ሰላሙ ንግግሩ ወደ አሜሪካ የተላኩትና በቅ/ሲኖዶሱ የተሰጣቸውን ተጨማሪ የሰላም ተልእኮ ለመፈጸም በዚያው ከሚገኙት ሦስት ብፁዓን አባቶች መካከል ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ÷ ትላንት ሌሊቱን ከዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪኩ እና ከቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ጋራ በስልክ ተነጋግረዋል፡፡ በጥቅምት ቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ውሳኔ መሠረት በደብዳቤ መላካቸውንና በዳላሱ የሰላም ጉባኤ በወጣው የጋራ መግለጫ መሠረት ዕርቀ ሰላሙን ከሚያደናቅፉ ተግባራት ለመቆጠብ ተስማምተው መፈረማቸውን ያስታወሱት ብፁዕነታቸው÷ ቅ/ሲኖዶሱ የልኡኩን ሪፖርት ሳያዳምጥና የሎሳንጀለሱን የሰላም ጉባኤ ውጤት ሳይጠብቅ አስመራጭ ኮሚቴ መሠየሙን እንደማይቀበሉት ማስታወቃቸው ተዘግቧል፡፡
ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ እና ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ
ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ እና ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ