| የአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አሜሪካ |
አመታት ውስጥ ቤተክርስቲያኒቱ በተለያዩ ሁኔታዎች ክርስቲያኖች ሲገፉ፣ ቤተክርስቲያንን ልክ እንደግል ንብረት የሚያዩ የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፣ የሰበካ መንፈሣዊ አስተዳደር ጉባኤ፣ ቀሳጢ ዲያቆናት እና ጥቂት ባልቴቶች በሚፈጥሩት አልባሌ ከሕገ ቤተክርስቲያን ውጪ በሆነ መልኩ የቤተክርስቲያኑን አስተዳዳሪ ልክ ከጳጳስ በላይ የማንገስ ብሎም ሰውየው በተለይ ሁኔታ እራሳቸውን ከሕግም፣ ከምዕመናን በላይ እራሳቸውን የተለዩ ልዩ ፍጥረት አድርጎ የማየት ፤ አገልግሎት እንኳንስ ለመነኮሴ ለማንኛውም የቤተክርስቲያን አገልጋይ ጠዋት በኪዳን፣ ማታ በነግህ ጸሎት ጽሙድ ሆኖ አገልግሎት መስጠት የተለመደ እና ትክክለኛ ሃይማኑቱ የሚጠይቀው ሆኖ ሳለ ፤ ነገር ግን የቤተክርስቲያኑን አስተዳዳሪ ጸሎታቸው የተለየ እና ጽርሐአርያም የሚደርስ አድርጎ አግኖ የማሳየት ሁኔታ በእነዚህ ከላይ በጠቀስናቸው አድር ባይ ካህናት፣ ቀሳጢ ዲያቆናት እና ሥራ ፈት ባልቴቶች በተደጋጋሚ የቤተክርስቲያንን ችግር የሚያባብሱ እና ችግሩን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ የሚወስዱ የቤተክርስቲያን ፈተናዎች እንደሆኑ ከማንም የተደበቀ እንዳልሆነ በተለያዩ ክስተቶች ላይ ስንመለከት ቆይተናል፤ አሁንም በዚህ አጥቢያ የተከሰተው ይሄን አይነት ጉዳይ ነው።
እንደምናስታውሰው እራሱን “አባ ዮሐንስ” ብሎ የሚጠራው ክብረ ክህነት ይኑረው አይኑረው የሚታወቅ በሌለበት አንዳንድ አድርባይ ካህናት “አባታችን ቡራኬዎ ይድረሰን” በማለት ሥራ ፈት ባልቴቶች ደግሞ “የውየውን ፎቶ ያለበት የጸሎት መጽሐፍ” በማሰራት “ጻድቁ አባታችን” እያሉ፤ እንዲሁም ቀሳጢያን ዲያቆናት እና የበታች አድማቂዎች “የጸሎትዎ በረከት ይደርብን አባታችን” እያሉ የጸሎት ሕይወት የሌለውን ሰው የጸሎት አባት ማስመሰል፣ የምንኩስና ሕይወት የሌለውን ሰው ፤ ገዳማዊ ባሕታዊ በማሰኘት፣ ሌላው ቀርቶ እንኳንስ ለሌላው ምሕረት ሊያመጣ ለራሱ ከገባበት መውጣት የማይችለውን ሰው “ደመና ጠቅሰው ዛሬ አዲስ አበባ ታይተዋል አባታችን” በማለት የሚዘባበቱ እንደዚህ አይነት ባልቴቶች ለቤተክርስቲያኒቱ ትልቅ ፈተና ሆነዋት ቆይተዋል፤ አሁንም በዚህ በአሜሪካ በሚገኘው አጥቢያ ሰውየውን ያለቅድስናቸው “ቅዱስ ናቸው” ያለሥራቸው “የጸሎት አባት ናቸው” የመሣሰሉትን በማለት ሰውየው ከወጡበት የውሸት እና ከንቱ የልዕልና ግንባታ መረድ የተሳናቸው ይመስላሉ። አንዳንዴም ሰይጣን ባላሰብነው መንገድ ክቦ ክቦ እላይ ያደረሰን እና ወጥተን ወጥተን ለመውረድ በሚከብድበት ቦታ ላይ ያወጣበትን መሰላል ይወስዳል ይባላል። ከዚያም ሁለት አማራጭ ነው ያለው ፤ ወድቆ መሰባበር ፤ ወይም ባልዋለበት እራሱን ጻድቅ ነኝ፣ ወይም ከፈጣሪ ጋር በሚስተከከል መልኩ እራሱን ማስቀመጥ እና ለክርስቲያኖች ፈተና መሆን ነው፤ አሁንም የተፈጠረው ይሄው ነው።
ነገሩን ትንሽ እናብራራው ፤ ከታሪኩ ስንነሳ ቦታው ከዛሬ 17 ወይም 18 ዓመት በፊት አቡነ አብረሃም በቦታው በሊቀ ጳጳስነት ሲያገለግሉ በነበሩበት ወቅት የተተከለ አጥቢያ ነበር፤ በወቅቱ በኪራይ ቤት ለበርካታ ዓመታት ብዙ አገልግሎት ይፈጽምበት እንደነበር እንዲሁም በብዙ ችግር ውስጥ ሆነው በርካታ ሥራዎችን የሰራ አጥቢይ እንደነበር እና በተለይ በአሜሪካን ላሉ አጥቢያዎች በሙሉ የመልካም አስተዳደር እና ሕገ ቤተክርስቲያን የሚያከብር እና የሚያስከብር እንደመሆኑ መጠን በርካቶችም አርዓያ የሆነ አጥቢያ እንደነበር ይመሰክራሉ፤ ነገር ግን እንደ ብዙዎች የአሜሪካን ሃገር አጥቢያ ከኪራይ ቤት ወጥቶ የራስ የሆነ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ለመግዛት በሚደረገው ሂደት ላይ እያለ ችግሮች እዚህም እዚያም መታየት ጀመረዋል፤ በዚህ መሃል እጅግ በርከት ያሉ አገልጋዮች ተገፍተው ተባረዋል፤ በዋናነት በአስተዳዳሪው እኔ ብቻ ፤ ወይም እኔ የመጨረሻው ወሳኝ አካል እኔ ብቻ ነኝ ማንም እኔን ሊይዝ ወይም ሊነግረኝ አይገባም በሚል፤ ሰውየውም የብዙ ምዕመናን ተቃውሞም ስላልገጠማቸው በዚሁ ጸባይ ቀጥለው ዛሬ ላይ አጥቢያውን እጅግ በከፍተኛ ሁኔታ ከሚያውኩ ቁጥር አንድ ከሆኑ አካላት አንደኛው የአጥቢያው አስተዳዳሪ ናቸው።
በዚህ አጥቢያ በተለይ ካለፉት ሁለት ዓመት ወዲህ ብዙ ችግሮ ተከስተዋል፤ ከተከሰቱ ችግሮ ች መካከል ለመጥቀስ በጥቂቱ የሚከተሉት ናቸው፤
1ኝ/ በአጥቢያው ላይ በቦታው እራሳቸውን ብቸኛው የመጨረሻ ወሳኝ አካል እንደሆኑ ማየት፤
2ኛ/ ለሚወጣው ገንዘብ፣ የተለያዩ ስብከተ ወንጌል ወይም ተመሣሳይ አገልግሎት ያለ ማንም ጥያቄ ወሳኝ አካል መሆናቸው፤
3ኛ/ በሰውየው አምሳያ የፈጠሯቸው ቀሳጢ ዲያቆናት እና ባልቴቶችን አዘጋጅቶ ሰውየውን የተለዩ የሰው ፍጥረት እንዳልሆኑ ማሳየት
4ኛ/ እዚህ ቦታ የሚሾመኝም የሚያነሳኝም ከፓትርያሪክ ውጪ ማንም የለም ብሎ ማሰብ፤
5ኛ/ ለሕገ ቤተ ክርስቲያንም ሆነ ለቃለ አዋዲው ፍፁም አለመገዛት፤ እና ቃለ ዐዋዲውን ጠምዝዞ መተርጎም፤
6ኛ/ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለረጅም ዓመታት የማይሻሩ የሰበካ አስተዳደር አባላትን አይወርዱም ብለው መከላከል፣
7ኛ/ ያልፈለጓቸውን የቤተክርስቲያን አባላት በተለያዩ ምክንያቶች ማሸማቀቅ እና ማሳደድ፤ ብሎም ከዚያ አጥቢያ ማስወጣት፣
8ኛ/ በምዕመኑ ላይ ፍጹም ፍራቻን እና ጥርጣሬ እንዲፈጠር ዘወትም ሰዎችን በተለያዩ መንገዶች ማስፈራራት እና ማሸበር፤
9ኛ/ ገንዘብን በተመለከተ እባጥቢያው ላይ ያለ ሰውየው ፈቃድ ገንዘብ ሰብሳቢም ሆነ ሂሳብ ሰራተኛ እንዲሆን ማድረግ፤
10ኛ/ ሰውየውን የሚመክር መንገድ የሚያሳይ አይዞህ የሚል ሥውር አካል ከኃላ ሆኖ ሰውየውን ወደ ገደል የሚወስድ ወይም ወደ መቀመቅ እየከተተ እንዳለ የሚያሳዩ ብዙ ጥቆማዎች እንዳሉ ያሳያል፤
በአጠቃላይ በዚህ አጥቢያ እየሆኑ ካሉት እና አጥቢያውን ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ እየወሰዱ ያሉ ብዙ ሁኔታዎች እንዳሉ ሰምተናል፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ምእመኑ በፍፁም ትእግስት ሕገ ቤተክርስቲያን ይከበር ፤ የአስተዳዳሪው ሥራልጣን ይወሰን፣ የቤተክርስቲያኑ ጠቅላላ ጉባኤ ሥልጣን ይታወቅ እና ፍጹም የሆነ ሕገ ቤተክርስቲያን ሰፍኖ ሰበካ መንፈሣዊ ጉባኤን ያለማንም ተጽዕኖ እንምረጥ አስተዳዳሪው ከሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት ይታቀቡ ሰላም ቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ይስፈን፣ ልጆች በሰላም ይደጉ ካልተፈለገ እና ካልተገባ እሰጣ ገባ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ይቅር ሰላም እናውርድ በማለት በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም ፤ ወደ ሃገረ ስብከቱም ተደጋጋሚ አቤቱታዎች ቢያቀርቡም ፤ ሃገረ ስብከቱም ብዙ ነገሩን በትክክል የተረዳም አይመስልም ወይም የጥቅም ተጋሪም ሊሆን ይችላል፤ እንደሚታወቀው በዚያ ሃገረ ስብከት የበላይ የሆኑት አባት በብዙ የአስተዳደር እና የሥነ ምግባር ችግር ያለባቸው ሰው እንደሆኑ ይታወቃል፤ በመሆኑም በአጥቢያው ያለውም ችግር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍታት ያልፈለጉትም ምናልባት አንዳንድ ከአካባቢው በደረሰን መረጃ እንደተረዳንው የዚህ አጥቢያ አስተዳዳሪ ለሃገረ ስብከቱ ሰዎች ደጎስ ያለ ገንዘብ በመስጠት ዓይኖቻቸውን ከእነሱ አጥቢያ ላይ እንዲያነሱ እና መጥተውም እሳቸውን አሞግሰው እና “አባታችሁን ስሙ” በሚል ተናግረው ብቻ እንደሚሄዱ በተደጋጋሚ መረጃዎች ደርሶን ነበር፤ አሁን ላይ ችግሩ በጣም ከመባባሱ የተነሳ የአሜሪካን ፖሊስ በአስተዳዳሪው እና በእርሳቸው ግብረ በላ በሆኑ ሰዎች ፖሊስ ተጠርቶ በቤተክርስቲያኒቱም ገብተው ማስፈራራት እና ሌሎች ስራዎችን ሰርተው እንደሄዱ ሰምተናል።
በአብዛኛው በአሜሪካን የሚገኙ አጥቢያዎች ብዙዎቹ በሰዎች ስም ስለሚመዘገቡ እና ከስም የዘለለ ቤተክርስቲያንም ምንም መብት ስለሌላት እነዚሁ ስማቸው በግዢ ወይም በባለቤትነት የተመዘገቡ ሰዎች ፖሊስ ይጠራሉ፤ ያልፈለጓቸውን ሰዎች እንዲወጡ ብሎም በዚያ ቦታ እንዳይደርሱ ያሳግዳሉ፣ የቀረውም ምእመን አርፎ ተገዝቶ እንዲኖር ብዙ ሥራዎችን ይሰራሉ፤ እንዲህ ያሉት አካሄዶች ደግሞ ቆይቶ ለቤተክርስቲያንም ፈተና ከመሆኑም ባሻገር ምእመኑ ያልጠነከረው እና በቅጡ በሃማኖቱ ሥር ያልሰደደው እንደዚህ አይነት የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎችን ሲያይ ይሸሻል ወደ ሌላ ሃማኖት ይሄዳል፤ አለያም ቤተክርስቲያን አዘውትሮ መሄድን ይቀንሳል፤ አብዛኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ካህናት እና መነኮሳት ተመሳሳይ ጸባይ እና አስተዳደር ነው ያላቸው ብለው እንዲያስቡ ፤ ብሎም እንዲሸሹ የሚያደርጉ አካሄዶች ናቸው፤ ታዲያ መፍትሄው ምንድነው? ምእመናን በተለይ በአሜሪካን ሃገር ውስጥ የራሳቸውን ድርሻ ለሸፍጠኛ መነኮሳት ሰጥተው የሚቀመጡበትን መንገድ በፍፁም መቀጠል የለበትም የሚለውን አስምረን ለማለፍ እንድወዳለን፤ ከዚህ አንጻር የሚከተሉትን አግባብ ያላቸውን አካሄዶች እንዲሄዱ ሃሳብ እንሰጣልን።
1ኛ/ ብዙ የተማሩ እና አንቱ የሚባሉ ምእመናን በአሜሪካ እንደሚኖሩ ይታወቃል፤ እነዚህን ሰዎች ተጠቅመው ሰውየውን ማነጋገር እና አርፈው ሥራቸውን እግዚአብሔር የመረጣቸውን ሥራ ብቻ እንዲሰሩ መምከር ማስመከር፤
2ኛ/ ትክክለኛ የሆኑ የአስተዳድር መንፈሣዊ ጉባኤ ያለ አስተዳዳሪው እና ከማንም ሰው ነጻ የሆኑ የሚሰሩ በሙያም፣ በምግባርም፣ በሰዎችም እንዲሁም በፈጣሪ የሚታዘዙ እና ተቀባይነት ያላቸውን ሰዎች መምረጥ እና እንዲሰሩ ማድረግ፤
3ኛ/ አስተዳዳሪው ተመክረው እምቢ ካሉ ፤ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ደብዳቤ በመጻፍ እንዲነሱ ደብዳቤ መጻፍ እና ማስነሳት፤
4ኛ/ የአስተዳዳሪ ሥራ ፍፁም መንፈሳዊነትን ብቻ ያለውን የቤተ መቅደሱን እና የቤተክርስቲያኑ ተጠሪ የመሆን ሲሆን፤ በፍጹም አስተዳደር ላይ ጣልቃ እንዳይገቡ፣ በገንዘብ ላይ እጃቸውን እንዳያስገቡ፣ በስብከተ ወንጌል ላይ እጃቸውን እንዳያስገቡ አበክሮ በሕግም በማንኛውም መንገድ መገደብ፤
5ኛ/ መነኩሴው የራሴ የሚሏቸውን ሰዎች በተለያየ የሥራ ድርሻ የመደቧቸውን አቅማቸውን እና ችሎታቸውን መዝኖ ብቃት ባላቸው ሰዎች መተካት እና ማሰራት፤ የሚሰሩት ለመነኩሴው ሳይሆን ለቤተክርስቲያን ብቻ እንዲሆን አበክሮ መግለጽ፤
6ኛ/ ቀሳጤ ዲያቆናትን አደግን አደግን የሚሉትን ሥርዓቱን እና ሕገ ቤተክርስቲያኑን ማስተማር ፤ በተቻለ መጠን ከወላጆች ጋር በመሆን ማረቅ እና ማስተካከል፤ በዚህ ከቀጠሉ ነገ ለቤተክርስቲያንም ለምእመናንም ከባድ ፈተና ሊሆኑ ስለሚችሉ ዛሬ ላይ ማስተካከል ካልተቻለ ነገ ከባድ ፈተና ይገጥማል ብለን እናምናለን፤
7ኛ/ ባልቴቶችን ሳይገባቸው እና በማያገባቸው እየገቡ የሚፈተፍቱ እንደሚኖሩ ይጠበቃል፤ ሊደገፉ የሚፈልጉት ካል ቤተክርስቲያን ብቻ ነች እንጂ አንድ መነኮስ ላይ መደገፍ መጨረሻው ወድቆ መሰበር እንደሆነ ለብዙዎች ትምህርት ሊሆን የሚችለው ፤ ከዚህ በፊት “ባሕታዊ ገ/መስቀል” በሚል የሚጠራው ሰውዬ የደረሰበትን የሞራል ልዕልና ሁላችንም የምናስታውሰው ጉዳይ ነው እና የእርሱ እጣ ፋንታ እንዳይገጥመን መጠንቀቅ የሚያስፈልግ የመስለናል፤
በመጨረሻ በዚህ ጽሁፍ ዙሪያ አስተያየት ወይም መልስ ሊሆን የሚችል ካለ ጽሁፉን ያለምንም ማስተካከያ እንደምናስተናግድ ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን፤ ጽሁፎችን ወይም አስተያየቶችን ወይንም ፎቶግራፎችን ማጋራት ከፈለጋችሁ በሚከተለው የኢሜል አድራሻ ቢልኩልን እንደምናስተናግድ ከወዲሁ ቃል እንገባለን፤
kurtegnalejoch@gmail.com
ቸር ይግጠመን አሜን
ahun yemtelut hulum neger leke new enem yeteklehamanot memen negne, aba hulegezie ene becha negn leke negne belew yemilut, sewyew gebregeb yetemarum aymeslum eko betam yesadebalu, sewn ayakebrum betam yekotalu esachew yastemaruachew diakonat hulu betam leke besachew wetew sew yenekalu betam hulum neger enesu becha awaki argew new yemiasbut.
ReplyDeletemeftehe belachehu yaskemetachut leke new sewyewen kezi mabarer new yemiasfelegew arfew alkemetem kalu, eske zarie teru sew neberu neger gen ezehi addisu bota kegeban jemero betam tsebayachew telewetwal betam. endhum yetewesenu sewoch alu betam erasachewn kebetekrstian belaye yadergu andu engineer negn yelal neger gen yehetsan leje aymero new yalew yesachew aleklaku new, lelaw demo endezi betam sewyewn yesekelwachew nachew alawekuwachewm enji sewyew lemanem yemeimelesu aydelum selezi begize tsebaye masamer kalchalue mabarer ena lememenu selam mestet bechegnaw amarach new
በለው እኔ እኮ የሚገመኝ ግን ስድብ የኦርቶዶክስ መገለጫ ሆነ ማለት ነው ??? ለማንኛውም አፍ ሲከፈት ጭንቅላት ይታያል ይባላል : እግዚአብሔር በቅርብ ለሁሉም እንደየስራው እንደሚሰጥ እንጠራጠርም : እውነት ፃድቁ ፍርዳቸው እሩቅ እንዳይመስላችሁ በየቤታችን እየገባ ይከፍለናል እናተም በስድብ በርቱ እውነት ቅድስ ሚካኤል ሚዛኑን ያንሳ በዚህ ልክ ብልግና እና ስድብ እኔጃ አላውቅም ምን አይነት አስተዳደግ እንደሁነ እላውቅም ምን አይነት አስተምር አይ ትምህርት ሞልቶ ፈሰሰ አይ አስተማሪ ...... ተሳዳቢ አስተማሪ ተሳዳቢ ልጅ ነው የሚያፈራው ምክንያቱም ልጅ የአባቱን ወይም የአስተማረውን ሰው ነው የሚከተለው በሉ በርቱ እግዚአብሔር ይርዳችሁ በዚህ ቀጥሉ ውጢቱን እንግዲህ በቅርብ እንጠብቃለው ወይ ሰው ወይ እግዚአብሔር ያሸንፍል
Deleteመጀመሪያ ከመፍረድ ጠጋ ብሎ ማዳመጥ መማር አይቀድምም?? ደግሞ እግዚአብሔር የሾመውን ማን ሊያነሳው ይችላል? እሳቸውን አንስቶ ቦታውን መቀራመት ለፈለገው ሰው ለመስጠት ከሆነ ስህተት ነው ሰው ላይ ከመፍረዱ ችግሩ ማን ጋር ነው ምንድነው ??
Deleteማንም ማንንም አይንቅም ዲያቆናቱንም የማይሆን ንግግር እየተናገራችሁ ለማሸማቀቅ ስትሞክሩ ያልሆነ ነገር በቤተክርስቲያን ላይ እጅ አታስቀስሩ!!!!
አይ ጥጋብ ልክ ነህ ማባረሩ ከተጀመረ ከካህናቱ ይጀመራል ግን ቅድስ የሚካኤል ፍርድ በቅርብ እንጠብቃለን ማህበረ ቅድሳን እና ማህበረ ባለወልድ ለማህበር እንጂ ለቤተክርስቲያን የቆመ አይደልም ድርም እናውቃለን ቤተክርስቲያኑ በማህበር ለማደራጀት አታስብ ስራፈቶች ግዚያችሁን በከንቱ አትጫወቱበት ስሩበት ሞት አይቀርም በቅርብ የየአንዳድ ካህን ጉድ ይወጣል ማን ተሳዳቢ እንደሁነ ከቤተክርስቲያኑ YouTube መስማት ይቻላል ለምን የቤተክርስቲያኑ ብር ካልበላን ብሉ ስድብ ድንፍታ ....... ማን ምን እንዳደረ ያውቀዋል
Deleteይህንን ፅሁፍ የፃፈው ሰው መጀመሪያ ስርአተ ቤተክርስቲያንን ፈፅሞ አያውቃትም አውቃለሁም ካለ የሰፈር ወሬ ይመስል አሉባልተኛ የበዛበት መልእክት እንጂ ምንም አስተማሪ ፍሬ ነገር የለውም!!!! ይሄ ሁሉ ነገር የሆነው ባጭሩ "" ከኋላ የመጣ አይን አወጣ" እንደተባለው አባ ፍቅረማርያምን ጠምዝዞ ቦታውን ለማን መስጠት እንደተገለገ ግልፅ ነው ግን አትልፉ!!! እግዚአብሔር የሾመውን "ማንም "" አያወርድም።።።
ReplyDeleteዲያቆናቱንም ለማሸማቀቅ ከሆነ እናንተን 95% ይበልጧችኋል። የዛሬ ልጅ ቀላሎች አይደሉም።በመጨረሻም እግዚአብሔር ልብ ይስጣችሁ!!!
እውነት ግልጽ ማውራት ከፈለክ ለምን አራስህን ደብቀህ ታወራለህ? ለምን ማንነትህን አትገልጽም? እውነት ሥርዓት አዋቂ ከሆንክ እውነታውን መናገር ትጀምር ነበር፤ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ብዙ መረጃዎች እጃችን ገብተዋል በሙሉ ቀስ ብለን እንለቀዋለን። እንተ እንደምትለው አይነት ከሆኑ እኛም አናክብራቸው ነበር ነገር ግን አንድም አንተ የምትለውን ሰብዕና የሌላቸው መሆናቸውን ከመረጃዎቹ ለመገንዘብ ችለናል። የያዝናቸውን መረጃ ብንለቅ እጅግ ከባድ የሆነ ነገር ሊፈጥር ይችላል፤ እኛ ደግሞ አንተ የምትለው አይነት ሰዎች ስላልሆንን እንጂ መረጃዎችን እንደመጡ ዝም ብለን ብንለቀው ሊፈጠር የሚችለውን ከወዲሁ ስለምንገነዘብ ብቻ ነው፤ ለማንኛውም አስብህ ተናገር ፤ አፍህ ላይ የመጣውን ከማውራት፤
Deleteቸር ይግጠመን
እውነቱን መድሃኔዓለም ያውጣው የህ መለእክት የ3ኛ ወገን ነው እጅ አለበት ብዬ አምናለሁ ሀሳብ አንደበታችሁ ቤተክርስቲያንን አውቃለሁ ብሎ እንደሚያስብ ሰው እንሁን
ReplyDeleteበእውነት ከላይ የተገለጸው ክብረ ነክ አገላለጽ ትክክል አይደለም፤አይገባም፡፡ለቤተ ክርስትያን ከሚቆረቀር አማኝ ድህረ ገጽ እንዲህ ያለ ክብረ ነክ ንግግር ነውር ነው፡፡ ጸሃፊው ቢያንስ የቤተ ክርስትያን አባቶችን በሚገባቸው ክብር መጥራት ግዴታ አለበት፡፡ ስህተት አለ ተብሎ ቢታመን እንኳን እንዲህ ባለ በወረደ ቃላት በመዝለፍ መደማመጥ አይቻልም፡፡ አንድ ተከሳሽ በፍርድ ቤት ተፈ'ርዶበት ቡን እስከሚያገኝ ንጹህ ነው ስለሚባል በበሬ ወለደ ክስ አባቶችን እንዲህ መዝለፍ ድፍረት ካለ ትንሽ ጥፋት ቢገኝ ምን ሊያደርጉ ይሆን? ጸሃፊውን እግዚአብሄር ይቅር ይበለው፡፡ አባ ፍቅረ ማርያም ከላይ የተገለጸው በፍጹም አይገባቸውም፤እንዴውም የሚገባቸውን ምስጋና አላገኙም፡፡ ለ16አመት ጽምጹ ሳይሰማ የቆየ ቤተክርስትያን ዛሬ ምን ተፈጠረ? ለማንኛውም በዝርዝር እመለጽበታለህ፡፡ አንድ ነገር ልበልና ላብቃ፡፡ከላይ በአባ ፍቅረ ማርያም ላይ የተዘረዘረው በሬ ወልውድው ክስ ሃሰት ነው፡፡ ጸርቶ መብላት ያቃተው ጥቅም ፈላጊ ቤተክርስትያኑን ተቆጣጥሮ በመዳፍ ለማስገባትና በሌላ ቦታ እንደሚሰማ የግል ሃብት ለማድረግ ያሰበ ኃይል ይኖራል፡፡ ችግር ካለ በህግና ተቋማዊ አካሄዱን ተከትሎ ኡፈታል እንጅ እንዲህ ያለው ክብረ ነክ ባዶ ጩኸት አሳማኝ አይሆንም፡፡ ግርግር ለሌባ ያመቻል እንዲሉ ሃይማኖቱን የሚወድ ካለ ከእንደዞህ አይነቱ ክብረ ነክ ንግግር እራሱን ያርቅ!
ReplyDeleteክብረ ነክ ነው ያልከው? በጣም የሚያሳዝን ነው እንደነዚህ አይነት አባት መስለው ለብድ ለብሰው የገቡትን ሰዎች ማውጣት እና ቤተክርስቲያንን ከእነዚህ አይነት ስዎች ማጋለጥ ሥራችን ነው፤ አንተ/አንቺ ቲፎዞ ልትሆኚ ወይም ልትሆን ትችላለህ፤ የእኛ ሥራ ደግሞ ለምድ ለብሰው "አባት" የሚባሉትን ማጥራት እና ማውጣት ነው ተልዕኳችን ስለዚህ ከቲፎዞነት ወጥተን እውነታውን እንከተል፤ እኛ እንደሆንን በአካል አናውቃቸውም፣ በርስት ወይም በሌላ የሚያገናኘን ነገር የለንም በሰውየው ላይ፤ ነገር ግን በቤትክርስቲያናችን ውስጥ ለምድ ለብሰው የሚያደናግሩትን አንፋታቸውም
DeleteThe recent claims against Aba are misleading and do not represent the truth of who he is. We acknowledge that, like anyone, he may struggle with the complexities of modern management. However, these administrative shortcomings should not be used to attack his character. Above all, Aba is a spiritual father and a faithful servant. His life’s work is to lead souls to God, and that is how he should be recognized and respected.
ReplyDeleteጥሩ ግምገማ ነው ለአባ ያልዎትን ሃሳብ ገልጽዋል፤ አባ በአመት ውስጥ ለምን ሦስት አራት ጊዜ ኢትዮጵያ ይመላለሳሉ?
Deleteእንደ አባት ለምን አባቶች በሚኖሩበት ቦታ አያርፉም በኢትዮጵያ ለምንም ጎተራ አካባቢ በሚገኘው ኮንዶሚኒየም ይቀመጣሉ?
እውነተኛ አባት ከሆኑ ለምን በሚኖሩበት አጥቢያ ትክክለኛ የሰበካ ጉባኤ እንዲመረጥ አይፈልጉም? ለምን
በእጃችን ያሉትን መረጃዎች ለመግለጽ በጣም ሃይማኖት ይዞን፣ ሊመጣ የሚችለውን ከባድ ነገር በመፍራት እና በማሰብ ነው አለበለዚያ ግን ጥሩ አይመጣም ፤ በተለይ ከዚህ አጥቢያ አባል ከሆንክ ትንሽ ታገስ