Thursday, December 4, 2025

✍️መንግሥት በወንድማችን ዮሴፍ አንጻር ቤተ ክርስትያን ላይ የሚያደርገውን ቀልድ ቀጥሎበታል፡፡

ሁላችንም እንደምናውቀው መምህር ዮሴፍ የታፈነው ዕለተ ቅዳሜ ከሥራ ገበታው ላይ እጅግ አጸያፊ በሆነ መልኩ፣ መታሰሩን እንኳን
ዲ/ን ዮሴፍ ፍሰሐ 

ለቤተሰብ እንዲናገር ሳይፈቅዱለት ነበር፡፡ ከዚያም በወንድሞች የየማጎሪያ ቤት ዳሰሳ ከብዙ ድካም በኋላ በማእከላዊ የቶርቸር ቻምበር ውስጥ ለብቻው ጨላማ ክፍል ውስጥ አስረውት የከረሙ መሆኑ ተደረሰበት፡፡ በጨለማ ቤት ባሰሩባቸው ቀናት ማንም ሳያውቅ ፍርድ ቤትም አቅርበውትም ነበር፡፡ ልብ አድርጉ! ያንን ያደረጉት ጠበቃ እንዲቆምለትም ሳይፈቅዱ፣ ቤተሰብ እንዲጠይቀውም ሳያደርጉ ነበር፡፡ 

ከሳንንት እንግልት በኋላ ቤተሰብ እንዲጠይቀው ፈቀዱ፣ ከዚያም የታሰረበትን ወሕኒ ቤትና የፈርድ ቤት ቀጠሮው ከታወቀ በኋላ ጠበቆች ቆሙለት፡፡ ባለፈው ፍርድ ቤት አቅርበውት ምንም በደል ስላላገኙበት ፖሊስ ተጨማሪ 10 ቀናት ያስፈልገኛል በማለቱ ለታኅሳስ 2 ቀጥረውት ነበር፡፡

 የታሰረው በፌስቡክ በለጠፈው ሆኖ ሳለ ሌላ በደል ፍለጋ ትርጉም የማይሰጥ ስለሆነ ቀጠሮው ማጠር አለበት የሚል ይግባኝ ጠበቆቹ ስላስገቡ ትናንት ከቀኑ ሰምንት ሰዓት ላይ በድጋሜ ፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር፡፡ አሳፋሪው የፖሊስ መከራከሪያ 'ላይክና ሼር ያደረጉ አባላቱን እያፈላለኩ ነውና ከወጣ ተፈለጊዎቹን ይሰውርብኝል' የሚል በዐለም ላይ ተሰምቶ የማይታወቅን ደደብ ካልሆንክ ብቻ ልትናገረው የማትችለውን መከራከሪያ ቢያቀርብም ፍርዱ ቤቱ ውሳኔ ለመስጠት ለዛሬ 8፡30 ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር፡፡ 

በዛሬው ቀጠሮም ፍርድ ቤቱ ''በ20 ሺህ ብር ዋስ ወጥቶ ከውጭ ሆኖ ክሱን መከታተል ይችላል'' የሚል ፍርድ ይፈርዳል፡፡ ከዚያም ለዋስትና የሚከፈለው 20 ሺህ ብር ከተከፈለ በኋላ አጅሬ ፖሊስ ይግባኝ ጠይቆ እንዳይወጣ አድርገውታል፡፡ 

በአጭሩ ዮሴፍ የታሰረው ወንጀል ስላለባት አይደለም፣ ከላይ እስከ ታች፣ ከቤተ መንግሥት እስከ ቤተ ክህነት ተደራጅተው የቤተ ክርስቲያን ድምጾችን በማንገላታትና በማማረር ቤተ ክርስቲያንን ድምጽ አልባ ካደረጉ በኋላ የሚፈልጉትን እኩይ ዐላማቸውን በነጻነት መፈጸም ነው፡፡ የማዝነው ይኸንን የሚተባበሩ የክርስቶስን መስቀል የጨበጡ የዱር አራዊቶችም መኖራቸው ነው፡፡ 

የዮሴፍ እስር የቤተ ክርስቲያን መከራ ምሳሌ ነው፡፡ ሰቃልያነ አይሁን ክርስቶስን ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት እንደነበረው ሁሉ ሰቀላያነ ቤተ ክርስቲያን እና ቀታልያነ ኦርቶዶክሳውያን ደግሞ ዘመን ገጠመን ብለው ዮሴፋውያንን ከላይ ታች እያዳፏቸው ይገኛሉ፡፡ 

ሰሞኑን ጉዳዩን እየተከታተልን ቢሆንም ለፌስቡክ እንካኡን ለመጻፍ ያልፈለግነው ፍርድ ቤቱ ያለበደሉ የታሰረውን ንጹሑን ዮሴፍን በነጻነት ወስኖ፣ ውሳኔውም ተከብሮለት ወደ ቤቱ የሚገባ መስሎን ነበር፡፡ ድራማው ግን በውኃ ቅዳ ውኃ መልስ ሰዎችን ተስፋ አስቆርጦ ቤተ ክርስቲያንን የመውረር፣ ልጆቿንም ያለ ተቆርቋሪ የመጨፍጭፈ ረጅም እቅድ መሆኑን ተመልከተናል፡፡ 

የዮሴፍ እንግልት አሁንም ስላላቀ፣ ነገ ቀጠሮ ሦስት ሰዓት ላይ ቀጠሮ አለው፡፡ ዐዲስ አበባ ያላችሁ ኦርቶዶክሳውያን ምስኪኑን ልጃችሁን በወንጀለኞች ወደሚንገላታበት ልጦስትራ ሄዳችሁ ከጎኑ ትቆሙ ዘንድ እንጠይቃለን፡፡ 

ፍትሕ ለመምህር ዮሴፍ፣ ፍትሕ ዮሴፍ ለታሰረላቸው የአርሲ ኦርቶዶክሳውያን!

ዶ/ር አረጋ አባተ


የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment