መምህር ዮሴፍ ዛሬም አልተፈታም፡፡ ውሳኔ ለመስጠት ለዛሬ የተቀጠረ የነበረ ቢሆንም አሁንም ፖሊስ ይግባኝ በማለቱና ወንጀል
ሊያገኝበት ስላልቻል ለቀጣይ ማክሰኞ ቀጥረውታል፡፡ ለቀጣይም ዮሴፍ ላይ ወንጀል ማግኘት አይችልም፡፡ የማራዘሚያ ዘልዛላ ምክንያት ግን ይፈበርክ ይሆናል፡፡
| መምህር ዲ/ን ዮሴፍ |
ሊያገኝበት ስላልቻል ለቀጣይ ማክሰኞ ቀጥረውታል፡፡ ለቀጣይም ዮሴፍ ላይ ወንጀል ማግኘት አይችልም፡፡ የማራዘሚያ ዘልዛላ ምክንያት ግን ይፈበርክ ይሆናል፡፡
ዮሴፍ እንዳይፈታ እየታገለ ያለው ታጋይ የሚባለው ቤተ ክርስቲያንን ይታገልና ሥርዓቱን ያገለግል ዘንድ በቤተ ክርስቲያን ስም የሆነ ተቋም ''እመራለሁ'' የሚል ሰው ነው፡፡
ምንም እንኳን አሁን እንደተገለጠው ዮሴፍ አንድ ታጋይ የሚባል የቀድሞ ደረሳ እስረኛ ቢሆንም ለዮሴፍ መንገላታት ግን ዋና ተጠያቂው የቤተ ክርስቲያን ጠላት የሆነው ሥርዓቱ ነው፡፡ እንደ ታጋይ ያሉ አረመኔዎች የግል ታሳሪዎቻቸውን ያለ ምንም ወንጀል በመንግሥት ማረሚያ ቤት የሚያጉሩ ከሆነ ተጠያቂው ሥርዓቱ ነው፡፡
ይኸ ሥርዓት ገና ከጥንስሱ የቤተ ክርስቲያን ጠላትነቱን ያስመሰከረና ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ ጥራዝ ነጠቆችን፣ ሆዳሞችንና ከሐዲዎችን በመሰብሰብ በራሷ ልጆች በሚመስል መልኩ በተደጋጋሚ እያቆሰላት ይገኛል፡፡ ሥርዓቱን የሚያገለግሉ፣ ቋንቋዋን የሚናገሩና አልባሳቷን የሚለብሱ ሰዎችን የሚፈልጋቸው ከውስጥ ያለውን መከራ ለማጽናት ነው፡፡
በነገራችን ላይ በቤተ ክህነቱ የተሰገሰኩ የሥርዓቱ አገልጋዮች እንደ ታጋይ ሰሞኑን ያሳሰሯቸው በርካታ የቤተ ክርስቲያን ሰዎች አሉ፡፡ ታስረው የተፈቱም አሉ፡፡ ይኸን እንደ ሀገር ለመረዳት መሞከር በእጅጉ ያማል፡፡ በአጭሩ የሥርዓቱ አገልጋዮች የፈለጉትን ሰው አግተው ለፈለጉት ጊዜ በመንግሥት ማረሚያ ቤት ማቆየት እየቻሉ ነው፡፡
የዮሴፍን ልዩ የሚያደርገው፣ ግለሰባዊ ጠብ ውስጥ እንኳን የማይገባ፣ ከንባብና ከሥራው ውጭ ሐሜት ውስጥ እንኳን የማታገኘው ታታሪ የቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪ መሆኑ ነው፡፡ የዮሴፍ ጥፋቱ የሚያውቀውን እውነት ያለ ምንም መቀባባት ይናገራል፣ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደርስን በደል ፈጽሞ አይታገስም፡፡
ንጹሑን ዮሴፍን ፍቱት፣ ጊዜ ሰጠን ብላችሁ ሥርዓቱን የውርጋት ግለሰቦች መቀለጃ አታድርጉት፡፡ ከግለሰቦቹ ጋር ግን የምናወራርደው ሒሳብ ይኖረናል፡፡
ምንጭ፡ ኢትዮ ቱንቢ ሚዲያ
No comments:
Post a Comment