Wednesday, January 25, 2012

ጸብአቴ የማነ ብርሃን ማናቸው?

በዚህ ሰሞን በአትላንታ ጆርጂያ እራሱን ገለልተኛ ብሎ የሚጠራው የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የቦርድ አባላትና የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ የነበሩት ጸብአቴ የማነ ብርሃን ከረር ያለ ውዝግብ ምዕመናኑን ለሁለት ከመክፈሉ ባሻገር፥ የምዕመናንን ጆሮ ጭው የሚያደርግ ነገር መፈጸሙን ስንሰማ፣ ከአካባቢው የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ሞክረን በጉዳዩ ተሳታፊ ከሆኑት ምዕማን ጋር ግንኙነት በማድረግ ስለተፈጠረው ሁኔታ እንዲያብራሩልን ጠይቀናቸው ሙሉ መረጃውን ሰጥተውናል። የእኛ አላማ አንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን ሥርዓቷ፣ ቀኖናዋ፣ ትውፊቷ ተጠብቆ አገልግሎቱን መፈጸም ሲሆን አንዳንድ ጥቅም ዓይናቸውን ያሳወራቸውን አባት ተብዬዎች ግን፣ ዝም ብለን አናልፍም ሕዝበ ክርስቲያኑን ስለማንነታቸው በማሳወቅ መለየት። የበግ ለምድ ለብሰው በውስጣችን የገቡትን ነጣቂ ተኩላዎች ማውጣት የኛ አነሳስ ነው።

ከቦታው ሆነው የዘገቡልን ባልደረባችን እንደገለጹልን ጸብአቴ የማነ ብርሃን ወደ አሜሪካ ከመጡ ጀምሮ ቤተክርስቲያንን ከእናት ቤተክርስቲያን ለይተው ገለልተኛ በሚል ከአሁኑ አባ ፋኑኤል ከቀድሞው አባ መላኩ ጋር መክረው እና ቀምረው ሕዝበ ክርስቲያኑን እኛ ገለልተኞች ነን በሚል ከእናት ቤተክርስቲያኑ ለይተው ለራሳቸው እንዲመች ብቻ አድርገው የሕዝቡን ጥሪት ሲመዘብሩ እና ቤተክርስቲያኒቱን ተረካቢ ትውልድ ለማሳጣት ያደረጉት በደል እና ግፍ አልበቃ ብሎአቸው ዛሬ ደግሞ በተለየ መልኩ ሕዝቡን ሊከፋፍሉት እና ሊያምሱት ቆርጠው ተነስተዋል፤ በዚህም መሠረት ላለፉት አስርተ ዓመታት ሲያደርጉ የቆዩትን በጥቂቱ ለመዘርዘር እንሞክራለን፦

፩/ የቤተክርስቲያን የምዕመናን ተወካይ (ቦርድ) አባላትን ሕዝብ መምረጥ ሲገባው፥ ላለፉት ረጅም ዓመታት እዚህን ተወካዮች እኝሁ ጸብአቴ የማነ ብርሃን ነበሩ፤
፪/ የቤተክርስቲያኒቱን ሕግና ደንብ በተመለከተ ምንም አይነት ጥያቄ፣ ማንም የቤተክርስቲያኑ አባል የመጠየቅ መብት አልነበራችውም፥ ይንን ገፍቶ የሚመጣ ቢኖር ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከቤተክርስቲያን እንደሚባረር በተደጋጋሚ ይናገሩ ነበር፤
፫/ የቤተክርስቲያኑ ገቢም ሆነ ወጪ በምንም መልኩ ኦዲት ተደርጎ አያውቅም፥ እርሳቸው በሚፈልጉት መልኩ ብቻ በፈለጉት ሰው ብቻ ሂሳብ ተመርምሯል ለማለት ብቻ የማስመሰል ሥራዎችን ይሠሩ ነበር፥
፬/ የቅድስት ቤተክርስቲያን ሥርዓትና ቀኖና የመቀየር፣ የመጨመር፣ ወይም ከናካቴው የመለወጥ ሥልጣን የርሳቸው ብቻ ነበር፥ በየትኛውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምስጢራተ ቤተክርስቲያን ሲፈጸሙ ይታያል ነገር ግን ጸብአቴ የማነ ብርሃን ባሉበት ደብር ግን ቅዱስ ሥጋው እና ክቡር ደሙ ሲፈተት መጋረጃው ተገልጦ በግልጽ ልክ ካቶሊኮች እንደሚያደርጉት ሥርዓቱን ባልጠበቀ መልኩ ይካሄድ ነበር፤
፭/ ቤተክርስቲያኑ ለስም መተዳደሪያ ደንብ አለው ይባላል፥ ነገር ግን ጸሐፊውም፣ ወስነው ያጸደቁትም፣ ሕጉ የሚሠረውም ለርሳቸው ለጸብአቴ የማነ ብርሃን ብቻ ነበር።

በዚህ መሠረት ይመሩት የነበሩት ቤተክርስቲያን ብዙ ምዕመን ያለው ሲሆን ምዕመኑም ሆኑ የቦርዱ አባላት የታዘዙትን ከመሥራት ውጪ ጥያቄ መጠየቅ፣ ወይም ማብራሪያ መስጠት፣ ብሎም ደግሞ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ሥለሚሰሩት መናገርም ሆነ መጠየቅ በጥብቅ የተከለከል ነበር፥ ሰሞኑን ግን ያ ለአስተ ዓመታት ታምቆ የነበረው የምዕመናንን ትዕግስት ያሳጣው አንድ ክስተት ተፈጽሟል። ጸብአቴ የማነ ብርሃን ቤተክርስቲያን፣ ምዕመናን እንዲሁም በደሙ የመሠረታት ክርስቶስ በአጠቃላይ የቤተክርስቲያን የሆነውን ታላቁን ኃላፊነት የእረኝነት ተልዕኮዋቸውን ወደ ጎን ትተው እንደ ካህኑ ኤሊ ልጆች አፍኒን እና ፊናስ እናት የሆኑ ምዕመናንን ለረከሰ ኃጢያታቸው እና ግብራቸው ማዋላቸውን የቦርዱ አባታት መረጃ ይደርሳቸዋል፣ በነገሩ የተደናገጡት የቦርዱ ተወካዮች ማስረጃ ሊሆኑ የሚችሉ ማንኛውንም መረጃዎች ካሰባሰቡ በኃላ ነገሩ ህዝብ ሳይሰማው እና ሰው ሳይታወክ በሚል ጸብአቴውን ለስብሰባ ይጠሯቸዋል በዚያም የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡዋቸው በአክብሮት ይጠይቋቸዋል መልሳቸውም " በእርግጥ ሁለት ሕይወት ነው ያለኝ" የሚል ነበር። ይህንን የሰሙ የቦርዱ አባላት ምዕመናን ይህንን ከሚሰሙ እርሶ ከዚህ አገር በሰላም ብናሰናብቶትስ፣ አንደኛ የተከበሩበት ስሞት ከሚጠፋ፣ ሁለተኛ ከእርሶ በላይ የሆነ ካህን ወይም ጳጳስ ጋር ሄደው ንሰሐ ይውሰዱ እና ሕይወቶትን ያስተካክሉ በሚል ሰላማዊ ሃሳብ ያቀርቡላቸዋል፥ በዚህም ስምምነት ላይ ደርሰው የቦርዱ አባላት ምዕመናኑ በማያውቀው መልኩ ከቤተክርስቲያኑ አካውንት በጥሬው $47,000.00 በዶላር ተቀብለው በቦታቸው ካህን ተክተው ላይመለሱ ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ።

ከሰባት ወራት ቆይታ በኃላ፣ በኢትዮጵያም ጵጵስና ለመቀበል ብዙ ደጅ ጥናት ቢያደርጉም ሳይሳካላቸው በመቅረቱ ለቦርዱ አባላት በላኩት የe-mail መልዕክት ተመልሰው ለመምጣት እንዳሰቡ እና እነርሱም ምዕመናንን አስተባብረው እንዲቀበሏቸው መመሪያ ጭምር ይልካሉ፤ የቦርዱም አባላት በነገሩ ግራ ቢጋቡም በምንም አይነት መንገድ እንደማይቀበሏቸው እና አብረዋቸው መሥራት እንደማይፈቅዱና ሕሊናቸው እሺ እንደማይላቸው በመግለጽ መልዕክቱን ይመልሱላቸዋል። በዚህ ጊዜ ነበር ጸብአቴው የማስፈራሪያ ደብዳቤታቸውን በመጻፍ ለቦርዶ አባላት በድጋሚ በመላክ ደብዳቤውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ ብሎም በማናለብኝነት ተመልሰው ወደ አሜሪካ ጠቅላይ ግዛት ወደሆነችው አትላንታ ያመራሉ፥ ነገር ግን እርሳቸው እንደጠበቁት ሳይሆን ምዕመናኑ ከቦርዱ አባላት ጋር በመሆን በአንድ አቋም ከቤተክርስቲያን እንዲወጡና በድጋሚም እንዳይመለሱ ይጠይቋቸዋል። የምዕመናኑ ተወካይ አቋም እንዲሁም የጸብአቴው መልቀቂያ እዚህ ይጫኑ

በዚህ ሁኔታ የተጀመረው ቅራኔ ዛሬ ደግሞ ጸብአቴው የሬዲዮ የአየር ሰዓት በመግዛት የመለያየት ዘመቻቸውን ጀመረዋል፣ በዚህ ሬዲዮም ላይ እንደ እርሳቸው አይነት ሕይወት መኖር በቤተክርስቲያን ክልክል እንዳልሆነ "ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ጅግራ ናት" እንደሚሉት ምንም ችግር እንደሌለው ምዕመናኑን ለማደንዘዝና ለሥርዓተ ቤተክርስቲያኑ ግዴለሽ እንዲሆን ሲማረው የነበረውን የእውነተኛዋን የተዋሕዶ ትምህርት ትቶ የርሳቸውን ቅዠት እንዲቀበል ብሎም እንዲቀላቀልበት ያላሰለሰ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፥ እነዚህ ተረፈ አፍኒን እና ፊኒያስ እንዲህ አይነቱን የነውር ሥራቸውን ይዘው ንሰሐ እንደመግባት ይባስ ብለው መናፍቁን ፓስተር ልዑለቃልን በመጋበዝ ሥራቸው ትክክል እንደሆነ እና ምንም ጥፋት እንደሌለባቸው የአዞ እንባቸውን እያነቡ ህዝብን በማደናገር ላይ ይገኛሉ። እነዚህን ክብርን የማያውቁ የከበራቸውን መድኃኒዓለምን የካዱና ከሥርዓቷ ውጪ ያሌለውን እንዳለ አስመስለው ለመስበክ ከላይ እታች እያሉ የአትላንታን ህዝበ ክርስቲያን የሚያደነቁሩትን ልናውቅባቸው እና ጠንቅቀን ቅድስት ቤተክርስቲያንን ከነሥርዓቷ ለተተኪው ትውልድ የማስተላለፍ የእያንዳንዱ የኦርቶዶክስ ቤተሰቦች ሃላፊነት ስለሆነ፥ ከደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ምዕመናን እና የምዕመናኑ ተወካዮች ጎን ሆነን የበግ ለምድ ለብሰው ሊነጥቁ የመጡትን ተኩላዎች ወግዱ ልንላቸውን ብሎች ልንዋጋቸው እንደሚገባን የደብረ ብሥራት የምዕመናን ተወካዮች ላሳዩት ቆራጥ አቋም ልንኮራባቸው እና ልናመሰግናቸው ይገባል እንላለን።

ምዕመናን እነዚህን አባት መሳዮች ገለልተኛ እያሉ ሲከፋፍሉን፣ ያለ ሥርዓቷ የሚጓዙትን ቀሳውስት፣ ዲያቆናት፣ መነኩሳት፣ አላማቸው አውቀን በጨለማ የሚሰሩትን ኃጢያት የበላይ እንዳይኖራቸውና በቀኖና ቤተክርስቲያን እንዳይዳኙ እና እርምጃ እንዳይወሰድባቸው ምዕመናን እኛ ብቻነን የምናውቀው ብለው በጨለማ ያኖሩንን ጊዜ አስበን፣ ሰማያዊ ሳይሆን ምድራዊ ዓላማ የያዙ አለማዊያን መሆናቸውን አውቀን በዚህ እኩይ ተግባራቸው እንዳትተባበሯቸው የቀደሙ አባቶቻችን የወረሱንን አሰረ ፍኖት ህግና ደንብ ልንጠብቅ ይገባል እንላለን።
እግዚአብሔር አምላክ ለሕዝባችን መልካም እረኛ ይስጠን አሜን
የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክስቲያን ድረ ገጽ
አድራሻ:
3818 Clarkston Industrial Blvd.
Clarkston, GA 30021
ስልክ: 404-508-1330
ከአትላንታ ጆርጂያ
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

48 comments:

  1. ምን ዋጋ አለው አንዱን ሲያባርሩ ሌላው አጭበርባሪ ይተካል፡፡ በዚህ ወር ውስጥ እኮ ነው የባህሬን ሐመረ ኖህ ኪዳነ ምህረት ገዳም አስተዳዳሪ የነበሩ ቆመስ አባ ኃ/ሚካዔል የሚባሉ ባህሬን እያሉ ከ5 ሴቶች በላይ ደፍረው ከህዝቡ ጋር ሲጣሉ አሁን አትላንታ እዚሁ ቤ/ክርስቲያን ይመስለኛል መጥተው እያገለገሉ ያሉት!!!

    ReplyDelete
    Replies
    1. እናንተ ሀጢአተኞች የሰውን ስም እንዳጠፋችሁ ትኖራላችሁ በናንተ እልህ አሁን ጳጳስ ይሆናሉ ጠብቁ ሚስትስ ቢያገቡ ምን አለበት በሀዲስ ኪዳን ጳጳስ ያንዲት ሴት ባል የሆነ ነው የሚለው 1ኛ ጢሞ3፤1 ጀምሮ ተጽፎ አል እና ምኑ ላይ ነው ነውርነቱ ምቀኞች

      Delete
    2. flee from sexual immorality. all other sins a man commits are outside his body, but he who sins sexually sins against his own body do you not know that your body is a temple of the holy spirit
      the other thing is i need to tell you is in ethiopia orthodox thwahedo their is no such thing the way you have dreamed may be in tehadeso we have a very tight role bible said efollw your fothers who spoke the word of god to you consider the outcome of their way of life and imitate their faith.

      Delete
    3. አቤቱ ፈጣሪ ተመስገን ለዚህ ያበቃሃን እነሱ ሲያወሩና ስም ሲያጠፉ: ፀባቴ ደግሞ ስራቸውን ሲሰሩ ማየት እንዴት ደስ ይላል እስቲ ከእሳቸው ተማሩ::
      ለነገሩ ማንም አይደርችስባቸው በእውቀት: የችግሩም መንስኤው እሱው ይመስላል ቅናት
      ጊዜ አታጥፉ ይልቁንም ልምከራችሁ እሳቸው የተፈጠሩት ቃሉን ለማስተማር በተረጋጋ መንፈስ ለማስተላለፍ ስለዚህ የዘመኑ አዋቂ ነን ባዮች የሰው ጭንቅላት አታዙሩ ደስ የሚለው ደግሞ የራሳቸውን ቤተክርስቲያን መክፈታችውን በሬድዮ ሲያስዋውቁ እሰይው! ነው ያልኩት እንግዲህ እረፉት
      በርቱ አባታችን እግዚአብሔር ይጠብቆት::

      Delete
  2. wey girem min waga alew techemari liba gebtewal eza ahun.sew 2 bahryat alut enesum,melakawi ena enssawi , bewnetu enezi sewoch gin melakawi bewstachew yelem enssawiw bicha new yalew bewstachew::

    ReplyDelete
  3. liba biweta leyla liba geba bewnetu enezi sewoch melakaw kersachew rekewal kesachew yelew enssawi bicha new.

    ReplyDelete
  4. wey grm liba biweta techemari leyba geba :: endo bewnetu egih sewoch enssawi bicha new yelew bewstachew. melakawi bahri binorachew ema bendezi aynet fetena baltefetenu neber .

    ReplyDelete
  5. በጽሁፉ ውስጥ የተጠቀሱት አንዳንድ መርጃዎች ማስተካከያ ቢያስፈልጋቸውም ታሪኩ በሙሉ እውነት መሆኑ ምንም ጥርጣሬ የለውም። ከእሳቸው ጋር በመሆን ለበርካታ ዓመታት ቤተክርስቲያኗን በቁጥጥሯ ስር አድርጋ ለጸባቴ የማነ ብርሃን ተባባሪ በመሆን የኖረችውና አሁንም እሳቸውን ለመመለስ በምዕመናን ላይ ፈርዳ እሳቸውን ወደ ቤተክርስቲያን ለመመለስ በመንቀሳቀስ ላይ የምትገኘውን ወ/ሮ ኢትዮጵያ መንግስቱን "ተይ" የሚል ሰው ያስፈልጋል

    ReplyDelete
    Replies
    1. ልብ በሉ! ወ/ሮ ኢትዮጵያ የሰበካ ጉባኤ አባል ናት:: ለምን ይሆን ጸብአቴ እንዲመለሱ የምትታገለው? ግልጽ ነው:: የሚወራው ነገር ውሸት መሆኑን ሚስጥሩን ስለምታውቅና ገንዘቡን አዋጥቶ ቤተክርስቲያንን ለገነባው ህዝብ እውነተኛ እረኛ ያስፈልገዋል ብላ ስለምታስብ ነው:: ይልቁኑ አቶ ሳሙኤልና አበሮቹ እንደነጣቂ ተኩላ በክርስቶስ ደም የተዋጀውን መንጋ ከመበተን እንዲታቀቡ ሃይ ሊባሉ ይገባል ባይ ነኝ:: ኃይማኖታችን የሚያስተምረን የሰውን ክፉ እንድንመኝ ወይም መውደቂያ ጉድጉዋድ እንድንቆፍር ሳይሆን የወደቀን እንድናነሳ የደከመን እንድንደግፍ ነው::
      እሰየው! አባ ቤተክርስቲያን ከከፈቱልን ከነዚህ ውሸታሞች ድራማ ሽሽት በየሰንበቱ የተለያየ ደብር መሄዳችን ቀርቶ እንደቀድሞአችን ከአባታችን የወንጌል ገበታ ቀርበን ከበረከቱ እንቁዋደሳለን::
      እግዚአብሔር በምህረቱ በይቅርታው ቤቱን ለመበተን የተነሱትን ያስብ::

      Delete
    2. አንድም ከሴት ጋር የያዘቻቸው እሷ መሆኑን አይዘንጉ። እሷም ቢሆን አንድም ቦታ ላይ እሳቸው ድርጊቱን አልፈጸሙም ያለችበት ቦታ እንደሌለ ልብ ይበሉ። ህዝቡን የሚበትነው፣ በሃሰት ሕዝብን የሚከፋፍለው ማን እንደሆነ እግዚአብሄር ያውቀዋል። አንድ ቀን ያ እንኳን ከአንድ የሃይማኖት አባት ቀርቶ ከአንድ ተራ ሰው የማይጠበቅ ኢሜላቸው ለዝብ ይፋ ሲሆን፣ ማንነታቸው በግልጽ ይወጣል። እስከዚያው ድረስ ግን እሳቸውም ሆኑ እናንተ እውነትን እየካዳችሁ ኑሩ።

      Delete
    3. wondme/Ehte,
      Ethiopian beglle Anagrenatal esua yemetelew, tefatun Atfetewal negergin yekerta yedereglachew new yemtelew. enam atsasat, hezbu yekerta beyadergllachewum, endegena gebtew mekedes gen aychilum, Antem endesua menalebe yemetel kehone, mote alebet elhalew ewunetu endih new,

      Delete
  6. ewnet new btfenedu kahen papas mehon atecelum endawerachehu yeabatochine sem eyatefachihu tenoralachehu enji kahen weyem papas mehon atechelum!!!

    ReplyDelete
  7. Let all of us pray ! It is a very sad story. I never heared such kind of history in my life. I am hoping the church will get out of this mess and stand by its feet. Every thing comes for a reason. May be this is a time to clean up and rebuild. May God help us!

    ReplyDelete
  8. አሁን ደግሞ እዚሁ አትላንታ ውስጥ ከአንዲት ሴት ጋር በመሆን ምስኪያዙናል መድኃኔአለም በሚል ስም ቤተ ክርስቲያን ከፍተው በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው። እኝህ ሰው ይህንን ነገር ሁሉ አድርገው፣ ምንም እንዳልተፈጠረ በማስመሰል እንደገና ወደ ቤተ መቅደስ ገብተው ቅዳሴ ለመቀደስ፣ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበልና ለማቀበል በድፍረት መነሳታቸው ምን ያህል ለቤተ ክርስቲያኗና ለተከታዮቿ ንቀት እንዳላቸው የሚያሳይ ነው። አብራ ይህንን ቤተ ክርስቲያን የከፈተችውም ግለሰብ በደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሰበካ ጉባኤ አባል የነበርችና እሳቸው ያደረጉትን ነገር በሙሉ ለሰበካ ጉባዔው አባላት በተናገሩበት ወቅት አብራ የነበረችና ጉዳቸውን የሰማች ግለሰብ መሆኗ ነገሮችን የበለጠ ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ ያደርገዋል። እሳቸው ራሳቸው "ድርጊቱን ፈጽሜአለሁ፤ የሁለት አለም ሰው ነበርኩ" ካሉ እርሷ "አይ አላደረጉም ውሸቶትን ነው" ማለት "ከባለቤቱ ያወቀ" የሚለውን ተረት ያስተውሰናል።

    ReplyDelete
    Replies
    1. ይልቁንስ ይህች ሴትዮ የሰበካ ጉባኤው አባል ከነበረች መሆኑ የረጋ ዐዕምሮ ላለው አስተዋይ ሰው እውነትም ጥቂት በጥቅም የታወሩ የኮሚቴው መሪዎች የእግዚአብሔርን ቤት ለማፍረሥ እንደተነሳሱ ያመለክታል:: በእውነት እሳቸው አደረጉ እና አሉ የተባለውን ነገር በወሬ በማናፈስ የምዕመናንንና እና የጨቅላ ሕጻናትን ዐዕምሮ ከመበከል አልፎ የመናፍቃን መዘባበቻ እንድንሆን በር መክፈት ሳይሆን ጸብአቴ ራሳቸው በወንጌል ኮትኩተው ያሳደጉት ጉባዔ ፊት ቀርበው ስለሁሉም ነገር ማብራሪያ እንዲሰጡ መደረግ ነበረበት:: በተቃራኒው እነዚሁ ጥቂት ግለሰቦች ጠበኞችን አስታራቂ ለሆነችው ለእግዚእብሔር ቤት ጉዳይ ከዚቹ ቤተክርስቲያን ካዝና ብዙ ገንዘብ ከፍለው ነው የዓለምን ሕግና ኃይል በመጠቀም አባ ወደ ደብሩ አካባቢ እንዳይጠጉ ያሳገዱትና እውነቱ እንዳይታወቅ ያፈኑት::
      ግድ የላችሁም የሰይጣን መጠቀሚያ አትሁኑ: በማታውቁትም ነገር ገብታችሁ የሰውን ኃጢአት አታውሩ:: ፈራጅ ጌታ ነው::
      መድኃኔዓለም ማስተዋሉን ይስጠን!!!

      Delete
    2. እውነቱን ለመናገር ፍላጎቱ ቢኖራቸውና ለበርካታ አመታት በእምነት ሲከተላቸው የነበረውን ህዝብ ቢያከብሩ ኖሮ፣ በሬድዮ ሲወጡ እውነቱን በተናገሩ ነበር፤ እውነቱን ለመናገር ለምን የግዴታ ቤተክርስቲያን መምጣት አስፈላጋቸው? በሬድዮ ለሚሰማቸው ሁሉ ለምን እውነቱን አልተናገሩም? "የጻፍኩዋቸው ኢሜሎች ሰይጣን አድሮብኝ ነው የጻፍኩት" ብለው ለጠበቃ የጻፉትን ምነው በሬዲዮ አልተናገሩም? አሁንም ለህዝበ ክርቲያኑ ያላችሁን ንቀት ትታችሁ፣ ሁላችንም ወደንስሃ የምንመለስበትንና ለእውነት የምንቆምበትን መንገድ ብናመቻች የተሻለ ይመስለኛ። አሁን ያለው አካሄድ ጸባቴንም ቢሆን የሚጠቅማቸው አይደለም። "የመናፍቃን መዘባበቻ አንሁን" ለተባለው እንዲህ እንዲሆን ያደረገው የነገሩ ሁሉ ምንጭ መልስ ሊሰጥበት ይገባል። ምንግዜም ቢሆን ለምንውስዳቸው እርምጃዎች፣ የሚያስከትለውን ነገር ጨምሮ ማሰብ ተገቢ ነው። በመጨረሻም አንድ መርሳት የሌለብን ነገር ያለ ይመስለኛል ይኸውም የሁሉንም ልብ መርምሮ የሚያውቅ፣ ወቅቱ ሲደርስ ሁሉንም የሚገላልጠው አምላክ መኖሩን አለመርሳት ነው።

      Delete
    3. ቀናችሁ ደግሞ ምን ትሆኑ እግዚአብሔር የፈቀደውን ያረጋል እሱ ስሙ ይክበር::የናንተን ክፋት አይቶ ሁሉን ያሳካ ይምስላል እኛም የምንጸልይበት በታ አገኘን:: በቃ የናፈቀንን ትምህርት ሊመግቡን ነው አባታችን ተመስገን:
      እድሜና ጤናን ለአባታችን እንዲሰጥልን እንጸልያለን::

      Delete
    4. በእዉነት በጸባቴ ትምህርት ምንያህል ህይወትህ ተለዉቷል ለንስሃ ፈታን ነህ?ከቡድነኝነት ነጻ ወትተህ ለእዉነት ትቆረቆራለህ? ሌላዉ ቀርቶ ጸባቴ ህማማት ሊገባ በሆሳና ተክሊል አድርገዉ ሲያጋቡ ካቶሊክ በኛቤ/ክ ድጋሚ አይተመክም ሲሉ አሳ ጹሙ አልልም ብለዉ ሲያስተምሩ በተለይ የድፍረታቸዉ ታራ መንካቱ በመቸረሻቸዉ በቅዱሰ ስጋዉና ክቡርደሙ ላይ በፈጸሙት ብዙዎችን ያሳዘኑበት እዉቀት የማያስፈለገዉን የማንአለብኝነትን ስህተትሲሰሩ በቤ/ክያኗ ዶግማና ቅኖና ለምዕመኑ ድፍረቱና መለያየቱን በማስፋፋት ጸባቴ ምን አሉ የሚል እንጂ ቤ/ክ ምን ትላለች የማይል ልብ ፈጥረዉ እንደበለአም አህያ እንደ ፈለጉ ሲጭኑት ዛሬ $70000 እንፈልጋለን የጊፍት ቀን ነዉ እያሉ በቅዱሳን ስዕል ስር ሳጥን አስክምተዉ ያለ ቆጠራ ገንዘብ ሲሰበስቡ የቤተ/ክ ህግ እራሳቸዉ ጽፈዉ ባንድ በራሳቸዉ ፊርማ ሲያጸደቁ ኧረ ስንቱን ልዘርዝረዉ ይህ ሁሉ ሃገር ያወቀዉ ጸሃይ የሞቀዉን ባደባባይ ሲሰሩ እንዲህ ድፍረቱ ሞልቶ እየፈሰሰ ለኔ በግሌ በተጨባጭ የማዉቀዉ ቢኖረኝም ከጀርባ ሌላ የጨለማ ስራ መስራታቸዉ ለጸባቴ ከመቆም ለእዉነት መቆም ጽድቅ ነዉ ብሎ ለሚያስብ ሰዉ ብዙ የሚያነጋግር አይመስለኝም ባይሆን ወዳጅም ቢሆኑ ምን ይሻላል ማለትነዉ ለሳቸዉም የሚጠቅመዉ በመጨረሻ እስቲ አስተዉሉት የሳቸዉ ትምህርት በስብከት ዘዴ ትምህርት የሰዉን ልብ ለመማረክ ታሪክ አስተምር ይባላል እሳቸ ዉም ይህንን ነዉ የሚያደርጉት እስቲ አስተዉል ጸባቴ መቼ የሃዲስኪዳን ትምህርት መንግስተ ሰማያት ቀርባለች ንስሃ ግቡብለዉ አስተምረዉ ያዉቃሉ? ከፍቅረ ንዋይ ተጠበቁ ከዝሙት ታቀቡ ብለዉ ያዉቃሉ?

      Delete
    5. You are such a layer don't preach us we knew Tsebate he taught us a bible not gossip like you by writing something lies you think we believe you no way. About his Teaching you should open your ears when he was teaching if you closed your mind you don't get it.stop accusing one person and do the right thing instead.
      We know Tsebate work don't try to tell lies no one believe you.
      you are one of those calls them self Mehabere kidusan you should call your self Mehabere Erkusan.
      You are giving names for all priest bad names someone to stop you. You guys are the worst for E.T.O.C everyone should open their eyes what you are doing in our Church.
      God watching you it is not going to long to see the truth of your Maheber.
      hope you should stop and pray

      Delete
    6. pleas trust me I am not Mahber kidusan but I am orthodox tewahido which one is laying የትኛዉ ነዉ ከዘረዘርኩት ዉሸት ከሰዉ ድጋፍ ዉጣና እግዝአብሄርን ተደገፍ ጸባቴ ላከበራቸዉ ቤተክርስትያን አዋረዷት እንደናነተም አይነት አጨብጫቢ የንስሃ በር አትዝጉባቸዉ እንደ አባትና ልጅ እዉነት ተነጋገሩ

      Delete
  9. Menew Ewnet Betisifu Mane Yamenal Belachcohu New Yemetelefut Enga Yemenawckachewn Tsebaten New Lela Esachew Enquan Degie Ababt, Lesew Asabi, Erherhu, Ewnetegna, Hulun Ekul Yemiyayu, Difin DebreLibanos Yenager Selesachew Len Yemayelu Yedeha Abat Nachew Sem lematefat Yegna sew Manbelot Yekenabachew Sew Ale Meselenge Engi Yehe Yetelat Wore New Manem Ayamenachehum Atelfu Giziachihun Atabakenu
    Lenegeru Yetewahedo Beteseboch Dehena Neger Mawrat Ayshalem Lesew yemitekem Timihert Yehe Seytan Mesaria Mehon Aydelem Betam New Yemiasazenw Betam Asafari Nacehu
    Esti Manen Lemasdeset New Betam Serafet Nacehu. Andegizem Ewnet Sitsifu Ayechem Semichem Alwkeme EGziabehere Yekir Yebelachehu. Beka Yehe Yehaymanot Politica Bikeribachu, Endew Zembelachu Kirakinbo Wore Batametu. Yesachewn Chinklat Magenet Atechleum Dedboch

    ReplyDelete
  10. Enante Leboch Afachehun ZEgu Yehe Yesem Matefia Website new Ende Menew Serafetachehu yekir Yebelachihu

    ReplyDelete
  11. I don't think this is an Orthodox tewahdo church website. Our religion do not teach us to lie & talk about anyone. Those people are trying to destryo this great man, however the truth will come out soon or latter. The church board members are trying to sound honest, is this the whole truth did they tell us everything?

    ReplyDelete
  12. This web is totally wrong, no matter what you say we love him. You are nothing but full, we will support our teacher no matter what you say. But I know you are chicken to post this comment.

    ReplyDelete
  13. በስመ አብ!! ምን አይነቶች ስይጣናት ናቸው እዚህ ገጽ ላይ የምትጽፉት? እኔ የባህሬን ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ምዕመን ነኝ። እኒ እዚያ ያለሁት ያልሰማሁት በሀሰት የኝህን አባት ሰም ብታጠፉ ምን ታገኙበታላችሁ? ለምንስ የሰውን ጭንቅላት በሀሰት ትበርዛላችሁ?
    እግዚአብሔር ይቅር ይበላችሁ። አባ ኃይለሚካኤል የስንቱን ህይወት በመጽሀፍ ቅዱስ ሲመግቡ ቆይተው ስንቱን ወደ እግዚአብሄር መልሰው በራሳቸው ፈቃድ ወደ አሜሪካ የሄዱት።
    እባካችሁ በሀሰት የሰው ስም አታጥፉ፤

    ReplyDelete
  14. ወይ ጉድ! አሁን እናንተ ናችሁ ወይስ እርሳቸዉ ናቸው ህዝቡን ግራ እያጋባ ያለው? አሜሪካን ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተክርስቲያናት ሁሉም ራሳቸዉን ችለው የሚተዳደሩ ከመሆናቸውም በላይ በተደጋጋሚ በአገራችን ለሚገኙ የተቸገሩ ወገኖች የእርዳታ እጃቸውን እንደሚዘረጉ ይታወቃል:: ለጥቅም የተነሳሱና ከዚህ ቀደም የተለያዩ ደብሮችን በማወክ ተባርረው እዚህ የመጡ በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦች የሸረቡትን ሴራ እዉነትነቱን ሳታጣሩ አብራችሁ ማናፈሳችሁ ማንነታችሁን ይናገራል:: እኔንየሚያሳዝነኝ ቤተክርስያናችን ስርዐትና ወንጌል እንዳልተማርንባት: ወግ እንዳላየንባት ዛሬ ሃይ የሚል አዋቂ አባት ጠፍቶ የዝሙት ወሬ በወረቀት እየታተመ የሚሰበክባት ሆነች! ይገርማል እንደፖለቲከኛ የራሳቸዉን ሰዎች በህዝቡ መሃል ሰግስገው ጉባኤው ጥያቄ አለኝ ሲል... "ዝም በል አንተ!"... "ዝጋ!" ሲሉ ካየሁ ጀምሮ እኔም ቤተሰቤም የምንወዳት ቤተክርስቲያን መሄድ አቁመናል
    በነገራችን ላይ እግዚአብሔር ይህን አያይም ብላችሁ እንዳትሞኙ ያን ጊዜ ግን...ምርኮዉን ለማስመለስ የተነሳ ጊዜ ግን እናንተን አያርገኝ!!!

    ReplyDelete
  15. Yes, I agree we all need to pray hard!! Gabriele exposing this mess the guy thought he is untouchable and he can get away with this kind of sad crime. So as an Ethiopian Orthodox Christian we all have a big responsibility to stand up and support this church member. Please let’s not be outsider and watch when Gabriele showing us the miracle and needs our help not involving is missing the blessing. No priests are bigger than our God!! I am sure God is in our side and please let’s involve and find out the root of this problem and clean up not only this Church all Ethiopian Orthodox church in America. It is our responsibility to keep it clean and pass it to our kids.

    ReplyDelete
  16. Yes, I agree we all need to pray hard!! Gabriele exposing this mess the guy thought he is untouchable and he can get away with this kind of sad crime. So as an Ethiopian Orthodox Christian we all have a big responsibility to stand up and support this church member. Please let’s not be outsider and watch when Gabriele showing us the miracle and needs our help not involving is missing the blessing. No priests are bigger than our God!! I am sure God is in our side and please let’s involve and find out the root of this problem and clean up not only this Church all Ethiopian Orthodox church in America. It is our responsibility to keep it clean and pass it to our kids.

    ReplyDelete
  17. As a member I was at the meeting and I was listning very carefully. When the chariman talked about our spritual father's "Double Life" no body from the commette member say anything. If this is a lie, atleast one person from the commette member for his/her concsious and fear of God will say something but nobody did. That was the bottom line for me to swallow the truth. If you know the commettee members personaly you would appreciate them for thier bravery. For those of you blindly fallow the guy becareful you will get hurt.May God bless our church.

    ReplyDelete
    Replies
    1. Listen to yourself, my friend. If you were listening very carefully like you said you did, how could you have not noticed the fact that the chairman was the only person doing all the talking and making all the accusations and how could you have missed the bitterness in the faces of the other members? Has it occurred to you why half of the committee members walked away after a fierce dispute with the chairman and two other ill minded buddies of him? Do you know that the chairman even threatened to call the police when they disagreed to what he proposed to do and say to the congregation? Do you also know that the chairman was the only person that was preparing all the flyers that they distributed and the committee members found it by surprise?
      As a member of the EOT church, even if everything they said was true, did it cross your mind that a priest shouldn't be judged by an ordinary person and a lawyer as if there were no Godly ways to handle issues in our church? You still don't get it, do you?
      Wait, wait before you applaud the 'braves', have you at least tried to reach out to Tsebate and find out the other side of the story? Oh yes, you are too busy to find out the truth...
      Tell you what, you are the one that is following the wrong guy and need to watch out. We, on the other hand, follow God - not a person,the truth - not politics and drama.
      Guess what, THE TRUTH SETS FREE!!
      God bless the EOTC!!!

      Delete
    2. If you had followed God and stood for the truth, you would not have written this message. You can write this kind of senseless message to those who didn't attend the meeting, but to us, it's clearly showing us who we are dealing with.

      Delete
    3. My friend, if I haven't followed God and stood for the truth, trust me, I wouldn't have taken time out of my hectic schedule to even utter a word about this whole thing.
      By the way, who are you referring to by "we" in your last statement? For once, you are telling the truth. You know who you are up against. Yes...Your maker - God.
      Please tell me which one of my statements didn't make sense to you. The same mind set and stubborn attitude that is tearing the Ethiopian Community apart is trying to tear apart the house of God. You don't have the courage, nor the capability to confront Tsebate in front of the congregation solely because he has nothing to hide from the congregation, he rather explains whatever he does with scriptures from the Holy Bible and makes sure that the people have understood it. On the contrary, you focus your energy on confusing the people with baseless stories and allegations that have no value to the central belief of our Church.If you know Tsebate, he is always open and forward to opinions. How come you and all the other clergy members didn't challenge him about the doctrinal issues you whine about now? I know why...you all believed that what he taught about it was correct.
      Don't worry, the time has come...you can no longer tell the Christians that you will determine their destiny. The people know what's best for them here on earth and in their next lives. Soon the Ethiopian community will wake up to find out what these moochers are doing to their integrity.
      God bless the EOTC!!!

      Delete
  18. Oh well- You could try as much as you can to insult this great man. However- your are showing exactly what and who you are. As of our great teacher- we will be sure to support him and learn form him. We are glad we hear the good news he is back now to teach again, and for sure I will be wherever he is going to be teaching. I will triple my member fee to make sure he is fully supportd in his need. as far as Gabriele- I will not give a penny as far as I know this so called hand picked Members are controling theat place. Sure- I will go to pray thier, but contribute any penny to them, oh no thank you. Only an evil forgets his teacher.

    ReplyDelete
    Replies
    1. Do you know who selected them? If you don't know it, it is Tsebate. Where have you been for the last nine years. Why you haven't asked Tsebate about their selection? About your contribution, you should know better than that. You don't contribute for Tsebate or the Committee. Whether you contribute to Gabriel or other churches, it has to be from your heart, and you should know why you contriute. Please lets not be childish.

      Delete
  19. I thank God for this day but I thank God for give me to see things differently, I pray for those who misjudge and misunderstood, please stop accusing people this is not Christianity or Gods work
    when I see on this website I don't see good things who ever organize this website is not a Christian work just posting bad about every priest please post something important we don't want to see this kind of stuff from you if you call yourself Christian. I will pray for you to change I believe that God Changes people and God changes things I pray for peace and love.
    God please continue to bless our priest who were misjudged
    God bless all

    ReplyDelete
  20. እግዚእብሔር ይቅር ይበላችሁ እናንተ ስም አጥፊዎች በቃ ምን ትሆኑ እግዚአብሔር የሳቸውን ቦታ አይሰጣሁም: ቤተክርስቲያን የሰላም እንጂ የጦርነት ቦታ አይደለችም አርፋችሁ ተቀመጡ: ማንም ላያምን ባትለፉ ጥሩ ነው ሰላም ስጡን ወሬ ይብቃ::እኛ ጸባቴን እናውቃቸዋለን በጥሩ ምግባራችውና ደግነታቸው ብዙ ስለእሳቸው ማውራት ዋጋ የለውም ጥሩ ስራቸው ይመሰክራል::
    የተዋህዶ ልጆች ስራ ይሰራ ወሬ ይቁም ::

    ReplyDelete
  21. All his support if you realy care about him tell him to get help it will be a matter of time before he does it again. What makes me so sad is no one is talking about the Qurban the way he disrepect Jesus's body & Blood all this years! Go a head and flow him, you all deserve him anyway.You are not worshiping God you are Worshiping man. He is a smart man, and he is loughing at your supidity...

    ReplyDelete
  22. I don't care what anybody says. Only God knows the truth and everyone is involve in this mess some how. But still mad love for Tsebate... he was such a great father and I am sure he still is and always will b. And please us being as the next generation this is not the kind of things that we expect from our elder Ethiopian fellas. Fered ye egziabher new..... so instead of wasting ur time on such silly things how bout take ur time and think about how u can change the next generation and teach us more about our religion. This is the type of things that are pushing us away from our culture, religion..... Putting something like this on the intern-ate is not going to do no good for any of you guys. So how bout you all mature and act like your age because it is obvious that everyone is running some kind of business in the church or they are involve in some kind of mess. So it feels like everyone is pointing finger on each other to hide your side. People might not see but dont forget there is always God watching you. May God open your eyes and bless your soul. #Mesgana new seraye bezemene bedmeye lewalelg weleta men lekfelw legeta.

    ReplyDelete
  23. I have heard and read about Tsebate and his evil deed. I wish he would stay separate from the Church until he confessed and return to God. Those of the people who are for Tsebate and stand against the Church guidance think twice before you suggest and write the verse from Timothy. As an Orthodox you should have known the difference between monk and priest. It is time blind leads blind to fall to pit.

    ReplyDelete
  24. please stop accusing people I am tired of listening this accusation. Let God be the judge we don't know anything we heard from one side of story so we need to stop and pray for peace, because of that I am going to stop to go my beloved Gabriel Church people there is some kind of unhealthy felling.
    Church is a place of worshiping not gossiping I see a lot of women and men are gossiping every Sunday.
    before you talk about people examine yourself what you are doing.
    you are the worst one you should not be in the church.
    hope one day you will change because all this year you did not get anything you just coming to church.
    God is good he will change you
    God bless all who was accused

    ReplyDelete
  25. እኛ እዚሁ አትላንታ ተቀምጠን ሁሉን እያወቅን ከሩቅ ከአረብ ሃገር ሳይቀር ምኑንም ሳታውቁ ስለሳቸው ትከራከራላችሁ? ጸባቴን ሁላችንም እንወዳቸዋለን እናከብራቸውም ነበር። በእውቀታቸው ልናደንቃቸው እንችላለን ነገርግን እውነትን መካድ በራሱ ሃጢአት ነው። እሳቸው ዛሬ በሴት ተሰናክለው እግዜር አጋለጣቸው እንጂ በማን አለብኝነት ሥርዓት ሲቀይሩ እንደፈለጉት አምባገነን ሆነው ሲኖሩ ሁሉም እያጉረመረም ዝም ነበር ያለው። የእግዚአብሔርን ቤትን ግን ደፍሮ የሚቀር የለምና ጊዜው ሲደርስ በማይችሉት መንገድ መጣባቸው።
    ለመታሰቢያ ፍልሰታንና አቢይ ጾም ከጾማችሁ ይበቃል፣ ካቶሊክን ዳግም ማጥመቅ አያስፈልግም ብ ለው ሲያቆርቡ፣ ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን እንደ ካቶሊኮች በህዝብ ፊት በግላጭ ሲያደርጉ ከማዘንና ጥሎ ከመሄድ በቀር ማንም አልደፈራቸውም ነበር። እኔና ሌሎች አትላንታ የምንኖር ክርስቲያኖች ይህንን ብንክድ እግዜር ብቻ ሳይሆን እሳቸውም ጭምር ያዝናሉ። ምክንያቱም አምነውበት እንደሚያደርጉት አሁንም ቢሆን ሳይዋሹ ይናገራሉ። ደስ ከሚሉኝ ነገራቸው አላደረኩም ብለው አያውቁም የማደርገውን አደረኩኝ ብለው ማብራሪያ ይሰጣሉ እንጅ። ሌላው በሩቅ ያለ ሰው ግን አደረጉም ብሎ ይጣላል። ኧር ወደ ልባችን እንመለስ የሳቸው ወዳጅ መሆን ማለት ሌላ ነገር እውነትን መቀበሎ ደግሞ አንድነገር ነው። እሳቸው ባመኑበት ነገር እባካችሁ አትድከሙ።
    ስንት ነገር ሊያደርጉ የሚችሉ ታላቅ ሰው ለዚህ በመብቃታቸው እኔ በበኩሌ በጣም አዘንኩ እንጂ አልተደሰትኩም ነገርግን የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ስለሆነ በወዳጅነትና በአድናቂነት የሚሻር አይደለም። ከምንደግፈው ሰው ይልቅ ለእግዚአብሄርና ለእውነት ማድላት የህሊና ነጻነት ነው።
    በሆሳዕና ቤተ መቅደሱን ያስከበረ ጊታ ዛሬም እንደሚሰራ በማየቴ ግን ተገርሜአለሁ። እኛ በይሉኝታ በወዳጅነት ተይዘን ዝም ብንልም እርሱ ዛሬም ይናገራል። ጌታ ሆይ ሁሌም እውነትን እንከተል ልብን ስጠኝ። ለሁላችንም

    ReplyDelete
    Replies
    1. ክዚ በላይ አሰተያየት የሰጠህው ወንድመሜ በመጀመሪያ እራስህን መርመር ስለሰው ክማውራትህ በፊት አንተ ማን ነህ እና ነው ስለሰው የምታውራው ክርሰትና በወሬ ነው የሚገለጠው ያለህ ማን ነው? እሰከዛሬ የት ነበርክ? ለነገሩ አንተ እራስህ ከነሱ አንዱ ትኦናለህ የሚያዋጣቹ ዝም ማለት ነው የሳችወውን ያህል አንድም እውቀት የላችሁም ወሬ ብቻ ደግሞ ቤተክርሰቲያን ስለከፈቱ አይናቹ ደም ለበሰ ምክኒያቱም ስው ይንደይሸሻቹ ፈርታቹ ነው ታዲያ ሰው እኮ የሚመጣው ጥሩ የሚያሰተምር አባት ሲያገኝ እንጂ እየዞረ የሰውን ስም የሚያጠፋ ቤተክርሰቲያንን የሚያፈርሰ እዛ ምን ይገኛል ብሎ ይመጣል ኡፍ ለማንኛውም እኛ ተገላገልን የንንተን ወሬ ከመሰማት እሰከዛሬ የምንሄድበት አተን ነበር እግኢአብሔር ይመሰገን ቤተክርሰቲያን ተከፈተልን ለንንተ እግዚያብሔር ልቦና ይሰጣችሁ

      Delete
  26. We need to look the whole affair of the Tsebate and the Bisrate Gabriel Parish Council with open mind and a sense of clarity and responsibility. Tsebate may or may not have committed what he has been charged of. But till now, his accuser, or the Parish Council, has been acting as examiner, investigator, prosecution, witness and judge, all at the same time and in the same breadth. We live in a country where one is innocent until proven guilty. Tsebate has the right, and the Parish Council a duty, to set up an independent body, made up of persons, who are well-qualified in religious matters and of integrity and character to investigate the allegations and make their own recommendations. Both the Tsebate and the Parish Council should abide by the body's recommendation and conclusion. Otherwise, none of the parties are credible and trial by public media is not acceptable at least in this country we live in. Atlanta has got plenty persons of letters and integrity who could act as honest investigators. Both parties should stop media campaign and trial by mass media and submit themselves to the rule of law. Let us hope they will do.
    Several of you accuse Tsebate of many frivolous issues, such as opening the curtain of the Sancta Sanctorum during the celebration of Qurban, non-rebaptizing Catholic converting to ETC faith and so on. As for baptism, there is only ONE and the converts from one Christian Church to another cannot be rebaptized, because whether you're Orthodox, Catholic or Protestant, there is only One Baptism and One Christ and One Apostolic Church. Opening the curtain or closing it during the Holy Mass celebration has nothing to do with violating doctrine because the practice is purely cultural, and not doctrinal or one of the canons of faith. The doctrinal issues are those listed in the Nicean Creed, and as far as I know nobody so far is charging the Tsebate for violating any of those creeds. In this respect, Tsebate should be commended for moving with changing time instead of stressing outdated and old-fashioned cultural values that have nothing to do with the Christian faith or doctrine. Our brethern churches of Alexandria and others have moved away from many of these obscurantist ideas and (Old Testament) cultural traditions long time ago, and our Church should follow the same reformist path and move with the changing time. In this regard, we need someone of Tsebate's ilk, mind-set and vision who would lead the Tewahedo church with forward-looking, and not backward-gazing, mind, and bring it and its institutions to the 21st Century thinking and acting rather than leaving them buried under many of their asphyxiating medieval values, practices and outlook.
    Many perhaps think that I am Tsebate's supporter. Definitely, I am not, even though I appreciate his preaching. I have heard the charges and the counter-charges of both parties, those of Tsebate's through reading and the grapevine, and those of the Parish Council, through reading, gossips, and also attending in person many of the meetings in which it presented its charges against the Tsebate. The evidence presented by both parties have deep holes and I am not convinced by any of them beyond reasonable doubt. Thus, the need for an independent and credible inquiry by a neutral and honest body. Otherwise, please stop conducting and judging anyone based on this constant torrent of innuendos, gossips, lies, and half-truths that both parties are feeding us. They'll help none execpt leaving many confused and bewildered, and their faith shaky, if not in tatters.

    ReplyDelete
  27. Be with God, follow Jesus not one priest...,
    just simple thing Tsebate love him self and I do not think lately he is a monk.I know Tsebate for the last 10 years, the first three years he was really a Monk. he love people than him self, he does not allowed people to use his name or church to ask Money. he was truely a monk, how ever starting 2004 he start acting not as a priest but as one of those leaders in Africa, he become a dictator and selfish. for example he does not want answer any question about the church management, any thing about him and Ethiopia Mengistu.before 2003 he was preaching as no body should pay for baptism,but after 2003 he changed and saying if you do not pay you do not get service. He become selfish, he brought his brother in the name of "Merigeta" with the church visa. Do you think all this ok? I am telling you,I can say a lot because I know a lot, how ever according to our bible " who am I to tell his seine" please lets follow Jesus not some priest. If we follow Jesus we will win in any circumstances, but if you follow people, they can not protect you.
    God Bless Orthodox tewahedo Church.

    ReplyDelete
    Replies
    1. Dear Anonymous: Your response does not address the issues raised by the above Anonymousn writer, who states that as both the Tsebate and his accuser, the Parish Council, are not credible, an independent body should be set up to investigate the allegations and actions of both parties, the accuser and the accused. If so, what your new allegations of Tsebate's arrogance, lack of transparency, or iresponsiveness ... have to do with the issue? If the Parish Council has nothing to hide and believes that its allegations are correct, substantiable and truthful, why is it afraid of setting up an independent body as many have been demanding for quite a while? Had the Parish Council complied with this demand, all these divisions and cynicisms would have been avoided. I am sure you do not accept blindly whatever the Parish Council tells you. If you do, there may be a problem. What you need at this moment is to add your voice to the rightful demand for an independent, trustworthy, and neutral body to be set up to investigate the Parish Council's "allegations." Without this being done, adding new charges is a futile exercise, because it only means "bewadeqe zaf mesar yebezal".

      Delete
    2. What are you going to investigate? Parish Council are not the one who committed adultery.They are not the one who stood by the Makdas and give Qurban every sunday! I will tell you what their crime is thsy should have told the church members as soon as they found out. Instead of sending with dignity. They are paying for it now. So please lets not forget the real issue here. The issue is Tsebate committed adultery.

      Delete
    3. please stop accusing people I am tired of listening this accusation. Let God be the judge we don't know anything we heard from one side of story so we need to stop and pray for peace, because of that I am going to stop to go my beloved Gabriel Church people there is some kind of unhealthy felling.
      Church is a place of worshiping not gossiping I see a lot of women and men are gossiping every Sunday.
      before you talk about people examine yourself what you are doing.
      you are the worst one you should not be in the church.
      hope one day you will change because all this year you did not get anything you just coming to church.
      God is good he will change you
      God bless all who was accused

      Delete
  28. before making judgment about others make sure your hands are clean

    ReplyDelete