| ሊቀ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል |
Sunday, December 28, 2025
የሠለስቱ ደቂቅ የነገረ መለኮት ትርጓሜ
Thursday, December 18, 2025
ጾመ ነቢያት: አስተምህሮ፣ ስብከት፣ ብርሃንና ኖላዊ
የነቢያት ጾም
| ልደተ ክርስቶስ |
ነው፡፡ “ነቢያት የጾሙት ስለምንድን ነው?” ቢሉ ለአዳም የተሰጠውን “አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ” የሚለውን የተስፋ ቃል በማሰብ ከሰማየ ሰማያት ይወርዳል፣ ከድንግል ማርያም ይወለዳል፣ በሞቱም ሞት የተፈረደበትን የሰው ልጅ ነፃ ያወጣዋል ብለው ነው፡፡ “ይህንን ጾም የትኞቹ ነቢያት ናቸው የጾሙት?” ቢሉ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ፵ ቀን ጾሟል (ዘጸዓት ፴፬ ፥ ፳፯)፤ ነቢዩ ኤልያስም ፵ ቀን ጾሟል (፩ኛ ነገሥት ፲፱ ፥ ፩)፡፡ በተጨማሪም በተለያየ ዘመን የነበሩት ነቢዩ ዕዝራ፣ ነቢዩ ነህምያ፣ ነቢዩ ዳንኤል እንዲሁም ክቡር ዳዊት ጾመዋል፡፡
Monday, December 15, 2025
በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ አባቶች እና ወንድሞች በአሜሪካን ምክር ቤት ፊት ቀርበው የአርሲ ክርስቲያኖችን ጭፍጭፋ መረጃዎችን አጋርተዋል
ዲያቆን ፋሲካው ካሳውን ያካተተ አንድ ጠንካራ አይሰበሬ ባለማዕተብ ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች ልዑክ ባለፈው ሣምንት በሀገረ አሜሪካ በዋሽንግተን ከተማ በአሜሪካ የሚኖሩ፣ እዚያው ተወልደው ባደጉ፣ ዜግነትም ባላቸው ኢትዮጵያውያን የተዋሕዶ ልጆች ያላሰለሰ ተጋድሎና ጥረት በኋላ ከአሜሪካ መንግሥት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የመንግሥቱ ባለሥልጣናት ጋር ታሪካዊ የሆነ የመጀመሪያ ደረጃ ፍሬያማና ውጤታማ ውይይት መደረጉን የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል።
Sunday, December 14, 2025
የሆሮ ጉዱሮ ወለጋ ሃገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ኤዶም ቀሲስ ዱጉማ በታጣቂዎች ተገደሉ!!
ሀገረ ስበከት ሥር በምተገኘው በሐረቶ ማርያም በዓሉን አክብረው ሲመለሱ ሻንቡ ከተማ መዳረሻ ሲደርሱ መልአከ ኤዶም ቀዲስ ዱጉማ እና በርካታ የህገረ ስብከቱ ሠራተኞችና ወጣት የማሕበራት አገልጋዮች በሕገ ወጥ ታጣቂዎቹ ተወስደው የቆዩ ሲሆን ሌሎቹ ተፈትተው ቆይተው ወደ ቤተሰቦቻቸው የተመለሱ ሲሆን በትናንትናው ዕለት የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ኤዶም ቀሲስ ዱጉማ አፋ እና ቀሲስ ደሳለኝ ነሞምሳ በሕገ ወጥ ታጣቂዎች መገደላቸው ተገልጿል፤
ዛሬም ኦሮዶክሳውያኑ ተደራጅተን እራሳችንን መከላከል ካልቻልን፤ አንድ በአንድ ተለቅመን እንደምናልቅ ጥርጥር የለውም! " Oromoon Oromoo hin Ajjeesu ማለትም ኦሮሞ ኦሮሞን አይገድልም "የሚለው የኦነግ/ብልጽግና ፍልስፍና ለኦሮሞ ኦርቶዶክስ ሲሆን አይሠራም።ለምን? "ኦርቶዶክስ የአማራ ሃይማኖት ስለሆነ ?"የኦሮሞ ብሔርተኝነትን መስፈርት አያሟላም።እውነታው ይኽ ነው።ዛሬ በወለጋ የተገደሉት ሁለቱም ካህናት ኦሮሞ ናቸው ነገር ግን ግን ከሞት አላመለጡም።ይኽን በመጻፌ ፖለቲካ ውስጥ ገባህ እባል ይሆን?
Friday, December 12, 2025
በአሜሪካ የሚገኘው የአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ፈተናዎቹ እና ችግሩ አስተዳዳሪው ናቸው
| የአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አሜሪካ |
አመታት ውስጥ ቤተክርስቲያኒቱ በተለያዩ ሁኔታዎች ክርስቲያኖች ሲገፉ፣ ቤተክርስቲያንን ልክ እንደግል ንብረት የሚያዩ የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፣ የሰበካ መንፈሣዊ አስተዳደር ጉባኤ፣ ቀሳጢ ዲያቆናት እና ጥቂት ባልቴቶች በሚፈጥሩት አልባሌ ከሕገ ቤተክርስቲያን ውጪ በሆነ መልኩ የቤተክርስቲያኑን አስተዳዳሪ ልክ ከጳጳስ በላይ የማንገስ ብሎም ሰውየው በተለይ ሁኔታ እራሳቸውን ከሕግም፣ ከምዕመናን በላይ እራሳቸውን የተለዩ ልዩ ፍጥረት አድርጎ የማየት ፤ አገልግሎት እንኳንስ ለመነኮሴ ለማንኛውም የቤተክርስቲያን አገልጋይ ጠዋት በኪዳን፣ ማታ በነግህ ጸሎት ጽሙድ ሆኖ አገልግሎት መስጠት የተለመደ እና ትክክለኛ ሃይማኑቱ የሚጠይቀው ሆኖ ሳለ ፤ ነገር ግን የቤተክርስቲያኑን አስተዳዳሪ ጸሎታቸው የተለየ እና ጽርሐአርያም የሚደርስ አድርጎ አግኖ የማሳየት ሁኔታ በእነዚህ ከላይ በጠቀስናቸው አድር ባይ ካህናት፣ ቀሳጢ ዲያቆናት እና ሥራ ፈት ባልቴቶች በተደጋጋሚ የቤተክርስቲያንን ችግር የሚያባብሱ እና ችግሩን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ የሚወስዱ የቤተክርስቲያን ፈተናዎች እንደሆኑ ከማንም የተደበቀ እንዳልሆነ በተለያዩ ክስተቶች ላይ ስንመለከት ቆይተናል፤ አሁንም በዚህ አጥቢያ የተከሰተው ይሄን አይነት ጉዳይ ነው።
Thursday, December 11, 2025
Press Releases Carter defends Christians against corrupt Ethiopian government in new resolution
introduced a resolution condemning the
The Ethiopian government for its many human rights violations, including the persecution of Christians, and urging the Secretary of State to use all available diplomatic tools to protect innocent civilians against their abusive, corrupt government.
The resolution condemns Ethiopia for “actions that threaten regional stability, violate fundamental human rights, and undermine the strategic interests of the United States in the Horn of Africa,” citing “acts of war crimes, crimes against humanity, and genocide,” and the targeting by “violence, intimidation, and persecution” of the Ethiopian Orthodox Church and other religious institutions.
“Practicing your Christian faith is not a crime. Terrorists are running Ethiopia into the ground, and with it the lives of countless innocent people, particularly religious minorities. From intimidation to famine and genocide, the Ethiopian government has given the United States no option but to limit its power by using every tool available to hold them accountable for these, and many other abuses,” said Rep. Carter.
Good News፦ ትግሉ ተቀጣጥሏል
Friday, December 5, 2025
መምህር ዲ/ን ዮሴፍ ዛሬም በግፈኞች እሥር እንዲቀጥል ተደጓል! እግዚኦ ለዳኝነት!!
| መምህር ዲ/ን ዮሴፍ |
ሊያገኝበት ስላልቻል ለቀጣይ ማክሰኞ ቀጥረውታል፡፡ ለቀጣይም ዮሴፍ ላይ ወንጀል ማግኘት አይችልም፡፡ የማራዘሚያ ዘልዛላ ምክንያት ግን ይፈበርክ ይሆናል፡፡
Thursday, December 4, 2025
✍️መንግሥት በወንድማችን ዮሴፍ አንጻር ቤተ ክርስትያን ላይ የሚያደርገውን ቀልድ ቀጥሎበታል፡፡
| ዲ/ን ዮሴፍ ፍሰሐ |
ለቤተሰብ እንዲናገር ሳይፈቅዱለት ነበር፡፡ ከዚያም በወንድሞች የየማጎሪያ ቤት ዳሰሳ ከብዙ ድካም በኋላ በማእከላዊ የቶርቸር ቻምበር ውስጥ ለብቻው ጨላማ ክፍል ውስጥ አስረውት የከረሙ መሆኑ ተደረሰበት፡፡ በጨለማ ቤት ባሰሩባቸው ቀናት ማንም ሳያውቅ ፍርድ ቤትም አቅርበውትም ነበር፡፡ ልብ አድርጉ! ያንን ያደረጉት ጠበቃ እንዲቆምለትም ሳይፈቅዱ፣ ቤተሰብ እንዲጠይቀውም ሳያደርጉ ነበር፡፡
ወልዲያ ከተማ ውስጥ የሚገኙ በርካታ የዓብነት ተማሪዎች ከቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ታፍሰው መወሰዳቸው ታወቀ
| የጠለፋ ወንጀል በኢትዮጵያ ተባብሷል |
እንደሆነ በተደጋጋሚ ያወጣናቸው መረጃዎች ጠቁመዋል።
"ዓራት ዓይናው ታላቁ አባት መላከ ገነት አምደብርሃን የኔታ ይባቤ በላይ ትላንት ምሽት ለዛሬ ሌሊት አጥቢያ አርፈዋል " - ቤተክርስቲያኗ
| መልአከ ገነት አምደብርሃን የኔታ ይባቤ በላይ |
ሲሏቸው ማውራት አልቻሉም' ነው ያሉን" - የሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት
በምዕራብ ሐረርጌ የታፈነው ጩኸት እና በአርሲ የቀጠለው ዘር ፍጅት!
Wednesday, December 3, 2025
ይድረስ ለኦርቶዶክሳውያን ሚዲያዎች
ላይ በሚፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ከወረዳው አስተዳዳሪ እስከ ቀበሌ ድረስ ያሉ ካድሬዎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እጃቸው እንዳለበት የታወቀ ነው አቶ አብደላ ግን ትልቅ ሚና ያለው ሰው ነው፦
Tuesday, December 2, 2025
“ ስንዴውን እየሸከፈ ነው”
| ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ |
ዘሪውም ዲያብሎስ ነው።እንክርዳዱም የሚዘራው ሰዎቹ ሲተኙ ነው። ሰዎቹ ያላቸው ታላላቁ የእግዚአብሔር ሰዎች ናቸው። ማንቀላፋታቸው ዕረፍታቸው ሲሆን ሰዎቹ ሲተኙ እንክርዳድ መዘራቱ ታላላቆቹ ሲያርፉ በዲያብሎስና ግብር አበሮቹ አዲስ እንክርዳድ ሥርዓት ይዘራልና።አብረውም እስከ መከር ይቆያሉ።መከሩ የዚህ ዓለም ማለቅ ሆኖ አጫጆቹም መልእክት ናቸው።ያን ጊዜ ንጉሥ ስንዴውን ከእንክርዳዱ የሚያበጥርበት የማያሳስት ሥልጣን የተባለ ነፋስ አለው።እንክርዳዱን በእሳት አቃጥሎ ስንዴውን በመንግሥተ ሰማያት ጎተራ ይሰበስባል ነበር የተማርነው።ማቴ፲፫፥፴፱-፵፪
