Monday, June 11, 2012

ዝቋላን መልሰን እናልማ


“ይህን ቦታ ወደ ቀድሞ ሁኔታ የመመለስ ሃላፊነት አለብን”
(አንድ አድርገን ሰኔ 4  2004 . )- የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም መጋቢት 9 2004 . ለቀናት በዘለቀው እና ለማጥፋት አዳጋች የሆነው እሳት ደኑ ላይ ብዙ ጉዳት እንዳደረሰ ይታወቃል በጊዜው እሳቱን ለማጥፋት በርካታ ምዕመናኖች ከአዲስ አበባ  ከአዳማ እና ከደብረዘይት ወደ ቦታ አምርተውየተቻላቸውን ሁሉ አድርገው እንደ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድ እሳቱን በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ይታወቃል ይህን በእሳት ምክንያት ገዳሙ ያጣውን ደን መልሶ ለማልት ‹‹ደጆችሽ አይዘጉ›› መንፈሳዊ ማህበር የመጀመሪያዙር የዛፍ ተከላ ፕሮግራም ሰኔ 24 እና ሰኔ 25 ቦታው ድረስ በመሄድ በሺህ የሚቆጠሩ ምዕመናና የሚሳተፉበትየጉድጓድ ቁፋሮ እና ዛፎችን የመትከል መርሀ ግብር አውጥቷል በዚህ የተቀደሰ መንፈሳዊ አገልግሎት ገንዘብያላችሁ በገንዘባችሁ ጉልበት ያላችሁ በጉልበታችሁ ትሳተፉ ዘንድ ጥሪያቸውን ያስተላልፋሉ  ይህን የዛፍ ተከላፕሮግራም ለመርዳት የምትፈልጉ ሰዎች ችግኞችን በመግዛት  ብር በማዋጣት እና ቦታው ድረስ በመሄድ የጉልበትአገልግሎት መስጠት ይምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
ወደ ገዳሙ የሚደረገው የጉዞ ቀን ቅዳሜ ሰኔ 24 2004 . ሲሆን የመመለሻ ቀን ደግሞ እሁድ ሰኔ 25 ይሆናል ይህን የተቀደሰ አላማ ላይ አሻራዎን ለማሳረፍና ከአባታችን ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በረከት ለመቀበልየምትፈልጉ ሰዎች የትራንስፖርት ወጪዎትን ብቻ በመሸፈን ማህበሩ ባዘጋጀው የጉዞ መርሀ ግብር ላይ በመገኝትየታሪካዊውን ገዳም ደን መልሶ የማልማት ፕሮግራም ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ዛፍ የመትከል መርሀ ግብሩ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ሰዎች ጉድጓድ ለመቆፈር የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችን (ዶማ ወይም አካፋ) መያዝ ይጠበቅቦታል ፤

የማይቀርበት ታላቅ የበረከት ስራ….”


ይህን አላማ ለመርዳት ወይም መርሀ ግብሩ ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሰዎች  ለበለጠ መረጃ (0911-201649  0911-216440 ፤ 0913-255249 ፤ 0911-015623 ፤ 0924-373474) በመደወል ሙሉ መረጃ ማግኝት ይችላሉ፡፡

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment