Friday, June 8, 2012

እውን የማኅበረ ቅዱሳንና የኦርቶዶክስ "ተሐድሶ" ፍልሚያ ወይስ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ህልውና ጉዳይ?


(አዲሱ ተስፋዬREAD IN PDF):- ከትላልቆቹ ያገራችን ባለስልጣናት ጀምሮ ታች እስካለው ሕዝብ ድረስ  ማኅበረቅዱሳን  የበርካቶች መነጋገርያ ከሆነ ከራርሟል:: የሰሞኑን ግን ለየት የሚያደርገው ራሱን " ኦርቶዶክስ “ተሐድሶ” "በማለት የሚጠራው ድርጅት በማኅበሩና በተዋሕዶ እምነታቸው ላይ ጽኑ አቋም ባላቸው  ኦርቶዶክስ ሃይማኖትአባቶች ላይ ለማንበብ የሚዘገንኑ (character assassinating) ጽሑፎችን እያስነበበ ነው  ከዚህም አልፎ የ”ተሐድሶ”  ቡድኖች አቡነ ጳውሎስን የተቃወሙ አባቶች ላይ ስማቸውን የሚያጠፋ በርካታ መጽሀፍትእስከመታተም ተደርሷል (አቡነ ሳሙአልን አቡነ አብርሃምን አቡነ ሚካኤል እና ሌሎች ጳጳሳትን ስም እያጠፉ የወጡትመጻህፍትን ያስታወሷልአንዳንድ ሃላፊነት የጎደላቸውና የድረገጻቸውን traffic rank ከመጨመር የዘለለ አርቀውማሰብ የተሳናቸው የፖለቲካ ዌብሳይቶችም እነዚህኑ ጽሑፎች በየድረ ገጻቸው ላይ በመለጠፍ ለብዙዎች አስነብበዋል
ጽሑፎቹን ያነበቡ በርካቶች የዋሀንም የችግሩን መሰረታዊ ምክንያት ባለመረዳት "የ”ተሐድሶ” ና የማኅበረ ቅዱሳንጦርነት"በማለት እንደዘበት ሲመለከቱትና ሲገረሙበት ይስተዋላል ውስጠ ሚስጥሩን ያወቁና ውዝግቡ "የውክልናጦርነት " መሆኑን የተገነዘቡ ጥቂቶችም የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ህልውናዋን ጥያቄ ውስጥ ያስገባ”  ችግርውስጥ መግባቷን ይተነትናሉ ለመሆኑ ግን የማኅበረ ቅዱሳንና የ”ተሐድሶ”  ገመና ምን ይመስላል። ከሁለቱምበስተጀርባ ያለው አካል ማነውየሁለቱ አካላት መሰረታዊ አለመግባባትስ ምክንያቱ  ምንድነው?
ቅድመ ነገረ “ተሐድሶ”
በርካታ ሚሲዎናውያን ከረጅም ግዜ ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ ማቅናታቸው ይታወቃል በተለይ የካቶሊክናየፕሮቴስታንት ሚሲዮናውያን ለዚህ ተጠቃሾች ናቸው:: እነዚህ ሁለት የሚሲዮን ቡድኖች እርስ በርስየማይስማሙና የማይገናኙ ቢሆኑም የሚያመሳስላችው ግን በርካታ ባህርያት ነበሯቸው  ሁለቱም  " ሀይማኖትለመስበክ ነው የገባነውቢሉም ÷ በተግባር ግን በገቡበት ሀገር ስራቸው ፖለቲካዊ ነበር  የሁለቱምሚሲዮናውያን ኢላማ  ያልተጠመቀው ሕዝብ ሳይሆን ባርባና በሰማንያ ቀኑ የተጠመቀው የተዋሕዶ ተከታከታይእንደነበር በወቅቱ የተጻፉ የታሪክ ማስረጃዎች ያስገነዝባሉ የካቶሊኮቹ ሚሲዮናውያን ይሄ ቅሰጣቸው ሲታወቅናካገር መባረራቸው እንደማይቀር ሲያውቁ እነሱን ወክሎ የነሱን ስራ የሚያስፈጽሙ " ቅባትና ጸጋየሚባሉቡድኖችን ፈጥረው  የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲ ያንን ከሁለት ለመክፍልና አዳክሞ ለመጣል ከፍተኛ ስራ ቢሰሩምያሰቡት ሳይሳካ ቤተ ክርስቲ ያንም ሳትከፈል እስካሁን ቆይታለች።

“ኦርቶዶክስ “ተሐድሶ” ”
የፕሮቴስታንት ሚሲዮናውያንም የተጠቀሙት ተመሳሳይ ስልትና ሴራ ነው። በመጀመርያ ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡያስፈቀዱት "ሀይማኖት ለሌለውና ላረማዊው ወንጌልን  ለሌላውም ክርስቲያን ደግሞ  ስልጣኔን  እናስተምራለን በማለት ሲሆን ራእያቸውም “የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እንደግፋለንየሚል ነበር ።ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ በግዜውለነበሩ የመንግስት አካላት ያስገቡት የተልእኮ እቅድ የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ማገዝ እንጂ ሌላ ቤተክርስቲያን መክፈት ወይም ቤተ ክርስቲያኗን የሚቃወም ሥራ መስራት አልነበረም።

 " In 1924 the Ethiopian missionary Association was formed with a mission statement to revive the orthodox church and not setup a separate church " [i]
ምንም እንኳን በወረቀት ያሰፈሩት ዓላማ ይሄ ቢሆንም በተግባር የሚያደርጉትና ያደርጉት እውነታ ግንከዚህ የተለየ ነበር  ይህንንም የታሪክ ሊቃውንቱ እንዲህ ሲሉ ይገልጹታል
 "Missionary efforts in Ethiopia have generally had to goals: to reform the Ethiopian Orthodox Church and to establish independent congregations taught and supervised by the missionaries. The missionary effort of the nineteenth and twentieth centuries often ended up doing both” [ii]
አሁን አሁን ራሳቸው የሚያውጧቸው ድርሳናት ላይ የወቅቱን የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲ ያንን የማደስ (ሚሲዮናዊ ማድረግ ድብቅ ዓላማቸውን እንዲህ ሲሉ  ገልጸውታል::           
"Modernizing Ethiopian society wasn’t the main agenda of protestant missionaries of the 17th century. Their main agenda was reforming Ethiopian church".[iii]

ዋና ዓላማቸው በግልጽና በግልጽ እንዳስቀመጡት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ማደስ በሚልፈሊጥ መከፋፈልና ማፈራረስ ነበር  ከራሳቸው ድርሳናት መረዳት እንደሚቻለው ጻጋናቅባትን የካቶሊክሚሲዮናውያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲ ያንን ለመከፋፈልና አዳክሞ ለመገርሰስ የፈጠሯቸውእንደሆኑ ሁሉ   “ተሐድሶ” ም ( ኦርቶዶክስ ተሃድሶየፕሮቴስታንት ሚሲዮናውያን ቤተ ክርስቲ ያንንለመከፋፈልና አዳክሞ ለመገርሰስ ይረዳቸው ዘንድ የፈጠሩት እንቅስቃሴ ነው 

ኦርቶዶክስ “ተሐድሶ”    ሚሲዮናወያኑ በኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከጥንት ጀምሮ አውጀውየነበረውን ጦርነት በውክልና የሚዋጋ (proxy war) ወኪል እንጂ በራሱ የቆመ ወይም ኢትዮጵያዊ መሰረትያለው ቡድን አይደለም። የሚታዘዘውም  የሚመራውም  አይዞህ ባዮቹም እነዚሁ ምስጢረ ብርቱዎቹሚሲዮናውያን ናቸው። ነገር ግን በእግዚአብሔር ቸርነት በቅዱሳን ጸሎትና ትጋት ያሰቡት ለበርካታ ክፍለ ዘመናትየተጠነሰሰ ሴራ ሳይሳካ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እስክ 21ኛው ክፍለ ዘመን ደርሳለች። አሁን ባለንበት 21ኛውክፍለ ዘመንም ካላፈው ስህተታቸው በመማር አዲስ ወረራና ደባ ጀምረዋል  በመሰረቱ ማንኛውም የሃይማኖትድርጅት እምነቱን ማሰራጨትና መብቱ ሊሆን ይችላል  በማያምኑበት እምነት ቤት ውስጥ ገብቶ ሌላውንመዝለፍ   ለማፍረስ ማሴር ግን ወንጀል ነው 

 የደርግ መንግስት ወድቆ አማጺው ቡድን አዲስ አበባ ሲገባ የነበረውን ክፍተት በመጠቀም ከተለያዩ የሚሲዮን ድርጅቶችቤተ ክርስቲ ያኒቷ ላይ የስድብና የትንኮሳ ውርጅብኝ ይዝንብ ጀመር። ከዛም አልፎ ተርፎ በወቅቱ ለነበሩት ጠቅላይሚኒቴርና የአመራር አካላት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እንዲሸሹና ቤተ ክርስቲ ያኒቷንም በተቻላቸውእንዲያዳክሙ የሚያሳስብ መልእክት ከነኝሁ ሚሲዮናውያን ቤተመንግስት ድረስ በድፍረት አስከመላክ ደረሱ።መቀመጫውን አሜሪካን ያደረገው ዎርልድ ሚኒስትሪስ ለአቶ ታምራት ላይኔ የላከውና መላው ኣለም ያነበው ዘንድበዌብ ሳይቱ እስካሁን የለጠፈው መልክት ቅንጫቢ  ይሄንን ይመስላል::

To the Government of Ethiopia:
My name is Jonathan Hansen. I am an ordained minister of the Gospel of Jesus Christ, the living God. I travel now primarily to countries where God has given me a message for either a person, the Christian community, the government or the nation…

The divine warning from the Lord was:"Remove yourself from the prostitute if you want to live!"

God in his mercy is telling the Ethiopian government to remove itself from the influence of the Orthodox Church. It does not preach and teach the true Gospel of Jesus Christ, but the doctrine of demons (fallen angels)….



"Your previous government slept with the prostitute of death then; the current government is also sleeping with this Angel of Death. Both governments listened and took her advice. God has warned this present government to break away from her or it will die too; that the next government will continue to sleep, eat and drink with this same prostitute and together they will join others in going against Israel. The prostitute is the Orthodox Church." [iv]

ወዲያውም ራሱን “ኦርቶ ጴንጤ” የሚል ቡድን ቤተ ክርስቲ ያንን ያምሳት ጀመር  የዚሁ ቡድን ዓላማም አንድ ነበር-የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት በማጥፋት በፕሮቴስታንታዊ አስተምሮ መተካት። ለዚህም ዓላማው መሳካትየመለመላቸውና በስውር ሲያሰለጥናቸው የነበሩት አንዳንድ የቀድሞው የሃይማኖተ አበው አባላት ቤተክርስቲያኒቱንአመሷት::በተለይ በሀረር  ናዝሬት  ባሉ አብያት ክርስቲያናትና ምእመናን ላይ ከባድ ወከባና ውዥንብር ፈጠረ  ጥቂትየማይባሉ ምእመናንም ከናት ቤተ ክርስቲ ያናቸው ለማስኮብለል ቻለ። ይሄው ራሱን ኦርቶ ጴንጤ እያለ የሚጠራውቡድን ግን  እንዳሰበው ብዙ ርቀት ሳይጓዝ ከማኅበረ ቅዱሳንና ከበርካታ የተዋሕዶ አባቶች ትጋት አናቱን ተመታ።በርካታ ፊታውራሪዎቹም ተወግዘው ተለዩ።

አዲሱ ስልት  - ቤተ ክርስቲያኗ ጉያ ውስጥ ተደብቆ ኦርቶዶክስንመገዝገዝ
ይህንን የተመለከቱት አዝማቾቻችው ግን የተረፉት የ”ተሐድሶ”  አባላት እስኪጠናከሩ ድረስ አንገታቸውን ቀብረውናመስለው በተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዲቀመጡና ቤተ ክርስቲ ያኗን በስውር እንዲገዘግዙ  መከሩ። ይህንንምምስጢር ፓስተሮቻቸው በተለያየ ግዜ ገልጸውታል::
“the movement grew swiftly and incorporated evangelical themes into the orthodox liturgy. Eventually it grew so large that the group was expelled from the orthodox church. Now called the reform orthodox church , the 70,000 plus believers maintain a connection to their orthodox roots but exibit an evangelical emphasis .[v]

ይህም ራስን ደብቆ የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲ ያንን ውስጥ ውስጡን መገዝገዙ ምን ያህል ውጤታማ እንደሆነ አዝማችየሆኑት አንዱ ፓስተር እንዲህ ሲሉ ገልጠውታል::
“They are doing a good job of staying close enough to their roots to be attractive to other orthodox believers and seekers”, one missionary said recently. [vi]

የዚህ ቡድን ዓላማ ቤተ ክርስቲያንን ወደ ሚሲዮናውያን ካምፕ መለወጥ መሆኑ በመታወቁ ከቤተ ክርስቲያን ቢገለልምበርካታ አባላቱ ግን ራሳቸውን ደብቀው ውስጥ ውስጡን ሲደራጁ የቤተ ክርስቲያን ያልሆነ ትምህርትን ሲያስተምሩ ቤተ ክርስቲ ያኗን ሲንዱ ነበር:: AD 2000 የተባለውም ድረ ገጽ ይህንኑ ኩነት እንዲህ ሲል ይገልጸዋል::
“Orthodox hierarchy has refused the group permission to meet in churches or address  congregations. The group doesn’t want to leave the Orthodox Church but to bring reforms and help people move beyond nominalism and experience a vibrant relation with Christ “[vii]

ይሄው ስውር የ”ተሐድሶ”  ቡድን ግን እንዳሰበውና እንደታዘዘው የተዋሕዶ ወጣቶችን በጅምላ ወደ ሚሲዮናውያን ጎራመውሰድ አልቻለም:: ለዚህም ዋናው ምክንያት "ሀይማኖት እንዳባቶቻችን ጥበብ እንደጊዜአችንበሚል መንፈስ ወጣቱበዘመናዊው ጥበብ እንዲበረታ ነገር ግን ያባቶቹን ተዋሕዶ ሃይማኖትን ግን ሳይበርዝና ሳይከልስ እንዲከተል ሌት ተቀንየሚጥረው ማኅበረ ቅዱሳን ነበር:: እንዳሰበው እንዳይንቅሳቀስ ዋነኛ ጋሬጣ የሆነበትን ማኅበረ ቅዱሳንን ካላፈረሰ የትምእንደማይደርስ የተረዳው የሄው የ”ተሐድሶ”  ቡድን  ማኅበረ ቅዱሳንን ለማፈራረስ ያስችለኛል የሚለውን ሁሉ ሴራጎንጉኖ አስፈላጊውን ዝግጅት ካደረግ በኋላ ላይ ግልጽ ትንኮሳና ሴራ ጀመረ::

ማኅበረ ቅዱሳን

ማኅበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ስርተዋቅሮ በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በተቀመጠለት መተዳደርያ ደንብ መሰረት መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት በመስጠትላይ የሚገኝ ማኅበር ነው::[viii] ይሔው ማኅበር ወደ 80 ሺህ የሚጠጉ አባላት ሲኖሩት በሰሜን አሜሪካ ዩሮፕ እስያበርካታ ያፍሪካ ሀገራት ቀጠናና ንኡስ ማእከላት አሉት:: ይሄው ማኅበር በአለማችን ላይ ካሉት ጠንካራ ከሚባሉክርስቲያናዊ ማኅበራት አንዱ ነው:: Big dreams, Tough reality : Ethiopia students at crossroadsበሚለው ጽሑፉ ላይ Peter Lemiuex ማኅበሩን እንዲህ ሲል ይገልጸዋል::
“the Ethiopian Orthodox student association Mahibere Kidusan, or “Fellowship of Saints,” which holds weekly meetings such as this one. Organized under the Sunday School Department of the Ethiopian Orthodox Church, Mahibere Kidusan has chapters in some 20 universities across Ethiopia as well as in other African countries, in Europe and in the United States. Some 80,000 Ethiopian Orthodox students are currently enrolled in its three-year church education program, which runs parallel to the university’s academic curriculum. The size and global reach of its deeply committed membership are all the more impressive since Mahibere Kidusan obtained its official license only 18 years ago. Almost a testament to its prominence, a nearly finished seven-story building close to campus will house its headquarters.” [ix]

ማኅበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ባሉ  በያንዳንዱ ዪንቨርስቲዎች ባሉ ግቢ ጉባአያት  እያደረገ ያለውንም እንቅስቃሴ እንዲህሲል ይቃኘዋል።
“Mahibere Kidusan champions the Orthodox faith as a bulwark against society’s many temptations. More controversially, it views the Orthodox Church as a bastion of traditional Ethiopian culture and identity — distinct from the West and the East — that its members should embrace and protect from outside influences. The message resonates strongly with today’s Ethiopian Orthodox youth, who bear witness to their rapidly changing society.” [x]



በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ የመሸጉ የ“ተሐድሶ”  አቀንቃኞችና የማኅበረ ቅዱሳንናፍልሚያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብዛኛዎቹ ወጣቶች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በማኅበረ ቅዱሳንየታቀፉ ናቸው  በየዩንቨርስቲ ያሉት ወጣቶች ማኅበሩ በሚያካሂዳቸው የግቢ ጉባኤያት የታቀፉ ሲሆኑ በቀጥታየማኅበሩ አባልና ደጋፊ ናቸው በየክፍለ ሀገራቱና ክፍለ ዓለማቱ ያሉ የማኅበሩ አባላት ተቀዳሚ ተልእኮ ደግሞ ባሉበትአጥቢያ የሰንበት ትምህርት ቤት አባል መሆን ስለሆነ የማኅበረ ቅዱሳን ቅዱሳን አሻራ የሌለበት ሰንበት ትምህርት የለምማለት ይቻላል  አብዛኛው ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ባመራር ወይም ባባልነት ማኅበረ ቅዱሳን አለ እያንዳንዱየማኅበሩ አባል ደግሞ ባለበት ወረዳም ይሁን ዞን የማኅበረ ቅዱሳን መዋቅር ስላለና ባለበት ሰንበት ትምህርት ቤትያለውን ሁኔታ በንቃት በመከታተል በወረዳው ወይም በዞኑ ላለው የማኅበሩ መዋቅር ስለሚያሳውቅ ማሀበሩና የማኅበሩአባላት ባሉበት ቦታ ኑፋቄ ማስተማር ፈጽሞ የማይታለም ነው ይህ ደግሞ ወጣቱ ከተዋሕዶ ትምህርት የራቀትምህርተ ሃይማኖት እያስተማረ በቤተ ክርስቲያኗ ላይ እንዲያምጹ ውስጥ ውስጡን ለሚሰራው የ”ተሐድሶ”  ቡድንከባድና የማይገፋ እንቅፋት ሆነ የ”ተሐድሶ” ና የማኅበረ ቅዱሳን መሰረታዊ ልዩነት  ከ”ተሐድሶ”  ወገኖች በግልጽእንደተቀመጠው አንድ ነው  ይሄንኑ ጉዳይም Rightside news ባንድ ወቅት ባቀረበው መሰረት የለሽ ክስ ላይእንዲህ ሲል አስነብቧል፦

“a group within the EOC called "Mahibere Kidusan" ("Fellowship of Saints") had incited members to …. The increasingly powerful group's purpose is to counter all reform movements within the EOC and shield the denomination from outside threats.”[xi]
ይሄው የ”ተሐድሶ”  ቡድን ማኅበረ ቅዱሳንን አፍርሶ ማኅበሩ የሚመራቸውን ግቢ ጉባኤያት ለመረክብ መጀመርያ ማኅበሩን ማፍረስ በሚል ዓላማ በተለይ ላለፉት ሁለት አመታት ማኅበረ ቅዱሳንን በመንግስት አካላትና አባ ሰረቀ ብርሃንን በመሳሰሉ የውስጥ አርበኞች ለማስመታት ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም አልተሳካም::ይልቁንም የግንቦቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ማኅበሩ ላደረጋቸው አስተዋጾዎች ከፍተኛ ምስጋና በማቅረብ የአዝ ሰንሰለቱም ከሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃ መምሪያ ወጥቶ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ስራ አስኪያጅ እንዲሆን ወስኗል:: የማኅበሩም ከሳሽ የነበሩትን ምስጢረ ብዙ የውስጥ አርበኛ አባ ሰረቀ ብርሃንንም ልዩ ምርመራ እንዲካሄድባቸውና ከዚህ በፊት ጽፈውት ለነበረው በኑፋቄ ለተበከለው የሊቃውንት ጉባኤ መልስ አንዲያዘጋጅ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነ ሲሆን ሌሎችም የ”ተሐድሶ”  የውስጥ ሴረኞችን በማውገዝ ቅዱስ ሲኖዶስ ለሁለተኛ ግዜ የ”ተሐድሶ” ን ቅስም በመስበር ታሪካዊ ሥራ ሰርቷል[xii]::

ማኅበረ ቅዱሳንን ማፍረስ ህልም አንደሆነ የተረዳው ይሄው ራሱን “ተሐድሶ”  እያለ የሚጠራው ቡድን ተሳዳቢ ምላስ ወደ ሊቃነ ጳጳሳቱ ዞሯል:: የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሆኑትንና የቤተ ክርስቲያኒቷ ዓምድ የሆኑት ጳጳሳት ላይ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ጀምሯል:: ዋናው ዓላማም ሕዝቡ በጳጳሳቱ ላይ ያለውን እምነትና አክብሮት እንዲያጣና በምሬት ከቤተ ክርስቲ ያኗ እንዲርቅና በምነታቸው የጸኑትን ሊቃነ ጳጳሳት ታሪክ መንፈሳዊ ወኔና ጥንካረ ለመስበር ታልሞ ነው:: በህይወት የሌሉትን አቡነ ሚካዔል በህይወት ካሉትም እነ አቡነ አብርሃም አቡነ ሳሙኤል ... ላይ የጳጵሳቱን ስም የሚያጠፉና ሥነ ምግባር የጎደለው የሐሰት ክስ የያዙ መጻሕፍት ታትመዋል::

እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል እንዲሉ አበው ባሁኑ ወቅት ግልጽ የሆነ ጉዳይ አለ-- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከባድ አደጋ ውስጥ ናት:: ቤተ ክርስቲ ያኗ ከውስጥና ከውጭ በሁለት ወገን እየተፈተነች ነው:: ባንድ ወገን ሲኖዶሱ ለሁለት ተከፍሎ አቅሟን አዳክሞታል:: ይሄንኑ ምክንያት በማድረግም በተለይ በውጭ ያለው ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ለሶስት ተከፍሏል:: የገዥውም ሆነ የተቃዋሚው ፖለቲካ አቀንቃኞች ቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ በመግባት አጀንዳዎቻቸውን ለማስፈጸም እየሮጡ ነው:: በዚህ ላይ የፓትርያርኩ ያባ ጳውሎስ አምባገነንነት ተጨምሮበት ቤተ ክርስቲ ያኗን እያዳከማት ነው:: ይሄን አጋጣሚና ክፈተት በመጠቀምም ራሱን “ተሐድሶ”  የሚለው ቡድን ቤተ ክርስቲያኗን ክፉኛ እየወጋት ነው::ቤተ ክርስትይኗ ከላይ በፖለቲከኞች ከስር ደግሞ በውስጥ ቀበኞች ሁለት እሳት እየነደደባት ነው::  የኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ቤተ ክርስቲያን የማፈራረስና ሰላም የመንሳት ሴራ ማብቂያው መቼ ይሆን?

ይቆየን




የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment