Friday, June 22, 2012

የላስ ቬጋስ ኪዳነ ምሕረት ወቅዱስ ሚካኤል ቤተ ከርስቲያን ከአቡነ ፋኑኤል ጋር አልሠራም አለ

ከላስ ቤጋስ ሐመረ ኖህ ኪዳነ ምሕረት ወቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የተጻፈው ደብዳቤ
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 14/2004 ዓ.ም፤ ጁን 21/ 2012/ READ THISARTICLE IN PDF)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በምዕራብ አሜሪካ የካሊፎርኒያ ሀ/ስብከት ሥር የሚገኘው የላስ ቬጋስ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ወቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን “ከብፁዕ አቡነ ፋኔኡል ጋር እንደማንሠራ እና የሸሙትንም ሹመት የማንቀበል መሆኑን” እንገልጻለን ባለበት መግለጫው አቡነ ፋኑኤል “ከዚህ በፊት ለአህጉረ ስብከቱ ተመድበው አባታዊ መመሪያ እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ይሰጡ ከነበሩት አባቶች በተለየ ምልኩ በመጓዝ ካህናት እና ምዕመናንን በማሳዘን ለመናፍቃን በር የሚከፍት የቤተ ክርስቲያን መዋቅር እና ሥርዓት ባልጠበቀ እና ባልተከተለ መንገድ መመሪያ በመስጠት እና በተግባርም በመፈፀም የግል ጥቅምን ብቻ በሚያስጠብቅ አካሄደ በመጓዛቸው በሚሠጡት የተሣሣተ እና ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የወጣ አመራር ጋር አብሮ መጓዝ ተገቢ ባለመሆኑ ከዚህ በፊት ያለንን አቋም/ አቋማችንን እንገልጻለን” ብሏል።


ሊቀ ጳጳሱ መግለጫዎቻቸውን እና መመሪያዎቻቸውን ጸረ ተዋሕዶ በሆኑ ብሎጎች/ የጡመራ መድረኮች ላይ ማውጣታቸውን በጽኑዕ የነቀፈው መግለጫው “የብፁዕነታቸው ማንኛውም መልዕክት ያለ እሳቸው ፈቃድ ነው የወጣው እንዳይባል ምንም ዓይነት የጽሑፍ ማስተባበያ ያልሰጡ በመሆናቸው እና ይህንና ይህንን በመሳሰሉት የቤተ ክርስቲያን ችግሮች ምክንያት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ማምጣት ሳይሆን መለያየት ምክንያት ከመሆናቸው በተጨማሪ ለቤተ ክርስቲያን ክብር እና መቆርቆር እንደሌላቸው ከዚህ ተግባራቸው ተረድተናል። ስለዚህ … ቤተ ክርስቲያናችን አብራ የማትሠራ መሆኑን እና የፈፀሙትንም ተግባር የምንቃወመው መሆኑን ለሚመለከተው አካላት ሁሉ መግለፅ አስፈልጎናል። በአጠቃላይ የብፁዕነታቸው አካሄድ፦
 1. ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ቤት መሆኑን የዘነጋ፣ 
2. የቀደሙ ቅዱሳን አባቶቻችን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ያስቀመጡትን የቤተ ክርስቲያን ቀኖና ቀስ በቀስ የሚሸረሽር በመሆኑ … ከብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ጋር አብሮ ለመሥራት የማንችል መሆኑን እና ለቤተ ክርስቲያናችን አስተዳዳሪ ለመላከ ኪዳን ቀሲስ ሳሙኤል ደጀኔ እና ለዲ. ስዩም ወ/አረጋዊ የተሠጠውን ሹመትም የማንቀበል መሆኑን እናስታውቃለን” ይላል።

የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ ይህንን ይጫኑ።


የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

1 comment:

  1. Duros ke tehadiso,siriat aliba tiwulid,genzeb asadaj group gar endet mesirat,menor yichalal !! Hulunim le Egzihabiher seten new enji zim yalnew yemigeba hono new endee?? Bicha hulum le bego new !!

    ReplyDelete