Saturday, June 23, 2012

በሙስና የሚታሙት የላፍቶ ደ/ትጉሃን ቅ/ሚካኤል አስተዳዳሪ አባ አእምሮ ሥላሴ ታከለ የአ/አ ሀ/ስብከት ም/ሥራ አስኪያጅ ኾነው ተሾሙ



·         የደብሩ ሰበካ ጉባኤ በአስተዳዳሪው ላይ ያቀረበው የሙስናክስ በመጣራት ላይ ነበር::
·         ወርቅ፣ የውጭ ምንዛሬና የሌሎች ነዋያት ግምት ሳይጨምር በጥሬ ብር ከ200,000 በላይ መዝብረዋል::
·         የአስተዳዳሪውን ሹመት በማስፈጸም የእጅጋየሁ በየነ ሚናአለበት::
·         የሀ/ስብከቱን ገዳማትና አድባራት ሓላፊዎች ለዐመፅ ለማዘጋጀት አባ ጳውሎስ ያሰቡት ዕቅድ አካል ይኾን?
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 15/2004 ዓ.ም፤ ጁን 22/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF):- ሰባኬ ወንጌል ከነበሩበት የመርካቶ ደብረ ኀይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን ወደ ላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንተዘዋውረው በአስተዳዳሪነት ከተሾሙ ሁለት ዓመታትን  ብቻ ነው ያስቆጠሩት - አባ አእምሮ ሥላሴ ታከለ፡፡በሁለት ዓመት የደብሩ ቆይታቸው ግን ካራታቸው በመዝገብ ላይ ያልሰፈረ የወርቅ እና የውጭ ምንዛሬ ስርቆትንጨምሮ ለተፈጸሙ ሕገ ወጥ የነዋየ ቅድሳት ሽያጭ እና የሙዳይ ምጽዋት ቆጠራ እንዲሁም ያለ ደረሰኝ ገቢየመሰብሰብ ድርጊቶች ዋነኛ ተጠያቂ መኾናቸው በሰፊው ይነገራል። በደብሩ የአንድ ወገን የጎጠኝነትአስተሳሰብ እንዲስፋፋና ሌሎች በርካታ አስተዳደራዊ ችግሮችም እንዲከሠቱ ምክንያት የመኾናቸው ጉዳይአደባባይ የወጣ ምስጢር መኾኑን ብዙዎች ይመሰክራሉ።


በድንገት ተነሥተው ከሄዱበት ገዳም በጣም በአጭር ጊዜ ውስጥ ምንኩስና ከተቀበሉ በኋላ ብዙም ሳይቆዩ የላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የኾኑት አባ አእምሮ ሥላሴ÷ ይህን ሹመት ለማግኘት ለቀድሞዎቹ የሀ/ስብከቱ አስተዳደር ሓላፊዎች እስከ 2ዐ ሺሕ ብር ገደማ መማለጃ መስጠታቸውተጠቁሟል፡፡ አባ አእምሮን በቅርበት የሚያውቋቸው ሰዎች ሰውዬው ገንዘብ አምላኩ፣ ቤት ለመሥራትና መኪናለመግዛት የሚቋምጡ፣ የመጠጥ ሱስ እና ከምንኩስና ሕይወት ይኹን ከጥሩ ምእመን ጋራ የማይጣጣሙ እኵይጠባዕያትን የተላበሱ ስለመኾናቸው ይመሰክሩባቸዋል፡፡ ከዕድሜያቸው አለመብሰልና ምግባር ጉድለት አኳያምየአስተዳዳሪነት ይኹን አሁን በአባ ጳውሎስ የተቸራቸው ሥልጣን በጭራሽ እንደማይገባቸው በመግለጽ ይተቿቸዋል፡፡

ምንጮቹ አያይዘው እንደገለጹት÷ አስተዳዳሪው ወደ ደብሩ ከመጡ ከአንድ ዓመት በኋላ አዲስ የተመረጠውሰበካ ጉባኤ ከእርሳቸው ጋራ በነበረው የአንድ ዓመት ቆይታ ተግባብቶ መሥራት አልቻለም፡፡ እንደሌሎቹ ጥቅመኛ አለቆች በቃለ ዐዋዲው መሠረት መሥራትም ኾነ መመራት ማይፈልጉት አባ አእምሮ÷ የጋራ ውሳኔበሚያስፈልጋቸው የተለያዩ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ የግል ፍላጎታቸው ጎልቶ የሚወጣባቸው አጋጣሚዎችበርካታ እንደነበሩ የዜናው ምንጮች ያደረሱን መረጃ ይጠቁማል፡፡ በተመሳሳይ ኹኔታ ከሰንበት ትምህርት ቤቱ፣ከስብከተ ወንጌል እና ልማት ኮሚቴዎች ጋራ ተግባብተው መሥራት ብቃት ይኹን ፍላጎት እንዳልነበራቸው ነው ዘገባው የሚጠቁመው፡፡

አባ አእምሮ በተለይም ከቀድሞው የደብሩ ጸሐፊ ጋራ በመተባበር የፈጸሟቸውን ሕገ ወጥ ድርጊቶች በተመለከተ ሰበካ ጉባኤው ከሁለት ወራት በፊት ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት በዝርዝር ማመልከቱን ተከትሎ ጉዳዩን የሚያጣራ ቡድን በግንቦት ወር ተልኮ እንደነበር ተዘግቧል፡፡ ይኹንና አጣሪ ቡድኑ ችግሩ ለማጣራት ወደደብሩ ለመጀመሪያ ጊዜ በመጣበት ወቅት÷ የአስተዳደር /ቤቱ ማኅበረ ካህናቱ ተሟልተው እንዳይገኙ ለማድረግ የሞከረ ቢኾንም ሰበካ ጉባኤው ስብሰባው ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ በመጠየቁ፣ የአጣሪ ቡድኑ ሰብሳቢ ንቡረ እድ አባ ዮሐንስ ገብረ ዮሐንስ በሰጡትም ማሳሰቢያ ስብሰባው ከሳምንት በኋላ የአስተዳደር /ቤት ሠራተኞች፣ካህናት፣ ዲያቆናት፣ የሰንበት /ቤት ሥራ አስፈጻሚ አባላት እና የጥበቃ አባላት ተሟልተው በተገኙበት ተካሂዷል፤ ሀገረ ስብከቱም በቅርቡ ውሳኔ እንደሚሰጥበት በተገለጸው የአጣሪ ቡድኑ ሰብሳቢ ማሳሰቢያ መሠረት አቤቱታው ፍትሐዊ ውሳኔ እንደሚያገኝም ተስፋ ተደርጎ ነበር፡፡

በዚህ መካከል ከሰኔ ሦስት ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ከእጅጋየሁ በየነ ጋራ ያላቸውን የቀደመ ወዳጅነት ማጠናከራቸው የተገለጸው አባ አእምሮ÷ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ አባላት እና የሰንበት /ቤት ሥራ አስፈጻሚዎችየማኅበረ ቅዱሳን አባላት እንደ ኾኑ፣ እርሳቸውን በሐሰት እንደ ከሰሷቸውና ሥራም አላሠራ እንዳሏቸውአድርገው ስሞታ እንዳቀረቡላቸው ነው የተጠቆመው። እንደ ቅርብ ምንጮች ከኾነ ታዲያ÷ ወይዘሮዋ አስተዳዳሪው ምንም ዐይነት ችግር እንደማይገጥማቸው በማደፋፈር ጉዳዩን ለፓትርያርኩ እንደሚያሳውቁነግረዋቸው ተለያይተዋል፡፡

ይህ በኾነ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ነበር ለአባ አእምሮ ሥላሴ ታከለ አቤቱታው ሹመት ኾኖላቸው የአዲስአበባ ሀገረ ስብከት /ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ኾነው ስለ መመደባቸው የተሰማው፡፡ የሊቀ መላእክት ቅዱስሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በደብሩ በተከበረበት ሰኔ 12 ቀን 2004 ዓ.ም ከሀገረ ስብከቱ የተላኩትና የዕለቱንትምህርት የሰጡት የአጣሪ ቡድኑ ሰብሳቢ ንቡረ እድ አባ ዮሐንስ፣ ከእርሳቸው በማይጠበቅ አኳኋን አስተዳዳሪውን ሲያሞካሹ እና የሹመታቸውን ‹የምሥራች› ሲናገሩ ከነፋስ ጋራ እንጂ አባ አእምሮን አሣምሮ ለሚያውቀው የላፍቶ ቅዱስ ሚካኤል አጥቢያ ምእመን የሚናገሩ አይመስሉም ነበር - እየሠሩ ያሉት መልካምሥራ በአንድ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ብቻ ተወስኖ እንዳይቀርና መልካም ሥራቸው በአዲስ አበባ ሀገረስብከት ሁሉ እንዲስፋፋ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት /ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ኾነውእንዲያገለግሉ በቅዱስ አባታችን በአቡነ ጳውሎስ ተሹመዋል፡፡” መቼም ‹ማፈር ድሮ ቀርቷል›ና ተሿሚው አባ አእምሮም በታቦተ ሕጉ ፊት ሰዎች  ወደ ላይ ሄደ ይሉኛል፤ እኔ ግን አልሄድኩም፤ ይህን ቦታ ገናእናለማለን” በማለት ሲዘርፉት በነበረው አገልጋይና ምእመን ላይ አላግጠዋል፡፡

ይህን ድራማ መሳይ አሳፋሪና አሳዛኝ ኹኔታ በቁጭት የተከታተሉት የደብሩ ማኅበረ ካህናት÷ ንቡረ እድ አባ ዮሐንስ ለአጣሪነት መጥተው በነበሩበት ወቅት በስብሰባ ላይ የተናገሩትን አጽናኝ እና መልካም ቃላት እያስታወሱና በዕለቱ የተናገሩትን በማነጻጸር÷ አይ አንቺ ቤተ ክርስቲያንከቶ ማን ይኾን በዚህ ዘመንየሚታመንልሽ?” በማለት እጅጉ ማዘናቸው ተዘግቧል፡፡ አንዳንዶቹም ንቡረ እዱ በፊት የተናገሩትንአስተባብሉ በሚል ተገደው እንደ ኾነ እንጂ በጤናቸው እንዴት በአንድ ራስ ሁለት ምላስ ይናገራሉ?” በማለትሲጠይቁም ተደምጠዋል፡፡

ጉዳዩን በቅርበት በመከታተል ፍትሕ ሲጠባበቁ ነገሩ ግራ ያጋባቸው ምእመናን የሀገረ ስብከቱ ፍትሕ ሲጠባበቁየነበሩ ታላላቅ አባቶችና እናቶች ምእመናንም “ውርደታቸው ክብራቸው (ክብራቸው በነውራቸው) ይኾናልየተባለው ዛሬ ተፈጸመ” ሲሉ ሌሎች ሰዎች ደግሞ “ጭራሽ አያፍሩም ወይለማፈርም እኮ ኅሊና ያስፈልጋል” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የክሱን ጉዳይ የያዘው አጣሪ ቡድን የደረሰበት ውሳኔ ሳይታወቅ ለአስተዳዳሪው የተሰጠው ሹመት፣ የአጣሪውቡድን ሰብሳቢ እርስ በራሳቸው የሚጋጩ አስተያየቶች እና ያልተጠበቀ ሙገሳ እንዲሁም ሰሞኑን አስተዳዳሪውበተደጋጋሚ በየሰፈሩ በእኔ ላይ የሚወራውን አትስሙ፤ አትመኑ፤ እንደሚባለው ከዚህ ቦታ የተነሣኹትበቀረበብኝ ክስ አይደለም፤ ይልቁንም በሠራኹት መልካም  በቅዱስ አባታችን ተሹሜያለኹ፤ እውነታውምይህ ብቻ ነው፤” በማለት በዐውደ ምሕረት እየተናገሩ የሚገኙት [ማስታዋወቂያ] ብዙዎችን አሳዝኗል፡፡

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን አሠራር በሚገባ የሚያውቁቱ “ድሮውንስ ምን ተጠብቆ ኖሯል?” ቢሉም ለአጥቢያው ምእመናን ÷ የአባ አእምሮ የምክትል ሥራ አስኪያጅነት ሹመት የአባ ጳውሎስን አስተዳደራዊ ፍትሕ በተጨባጭ የፈተነበትንና በሩቅ ሲሰ የቆየውን በቅርበት ያረጋገጠበትን አጋጣሚ ፈጥሮለታል፤ የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓልም ውደ ምሕረቱን በተቆጣጠሩት ግለሰቦች ሐሰት የተሰበከበት እና እውነት ለጊዜውም ቢኾን አንገቷን የደፋችበት የማይረሳ ቀን ኾኖ አልፏል።

ቀደም ሲል ባሰፈርነው ዘገባችን እንደተጠቆመው÷ በእጅጋየሁ በየነ ባለሟልነት ከአባ ጳውሎስ የተገኘው የአባ አእምሮ ታከለ ሹመት የፓትርያሪኩን ዐምባገነንት፣ የተጠያቂነት መጥፋት እና በወይዛዝርቱ አቅራቢነት እየገነገነ የመጣውን የሥልጣን መቆናጠጥ አባዜ ከማስረገጡም ባሻገር የሀ/ስብከቱን አድባራትና ገዳማት አስተዳደር ሓላፊዎች በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ላይ ለዐመፅ የማዘጋጀት ደባ አካል ሊኾን እንደሚችል አስተያየት እየተሰጠበት ይገኛል፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment