Thursday, October 30, 2025

አትነሳም ወይ፤ ኦርቶዶክሳዊ አይደልህም ወይ?

የመጣብንን የአላውያን ጦር በመስቀሉ እንሰብራለን፤
"አትነሳም ወይ? " 

አንተ የተዋሕዶ ልጅ ሆይ
ማንቀላፋቱ አይበቃም ሆይ!
መዘናጋቱስ አይበቃም  ወይ
አይገድህም ወይ!
አትነሳም ወይ
እያለቀ ያለው ወገንህ አይደለም ወይ!

ወገን ሲታረድ እንደ በግ ጠቦት
ደሙ ሲፈስ እንደ ውኃ ጅረት
አየነው አየነው እረፉ ባይ ጠፋ
ሞት ታውጆብን ከምድር እንድንጠፋ

       አየገባህም ወይ
        አትነሳም ወይ
       በግፍ የሚገደለው ሕዝብህ አይደለም ወይ

       መንግሥት አለ ብለህ እንዳትጃጃል
አባት አለ ብለህ እንዳትጃጃል
እግዚአብሔርን ይዘህ ተነስ ለ ትግል
ወደ ፊት ሩጥ እንጂ ወደ ኋላ አትበል

           አይበቃም ወይ
            አያሳዝንም ወይ
            አትነሳም ወይ
      በግፍ የሚታረደው
       ሕዝብህ አይደለም ወይ
ወገን በሃይማኖቱ በግፍ ሲገደል
ሬሳው እንኳ  ሳይቀር በእሳት ሲቃጠል
አያሳዝንም ወይ እየሆነ ያለው
ተነሳ ወጣት ሆይ  መፍትሔው 
መነሳት ነው

         አይገባህም ወይ
        አይበቃህም ወይ
         አይገድህም ወይ
         አትነሳም ወይ
   በመከራ ውስጥ ያለው 
  ሕዝብህ አይደለም ወይ

ሥጋህን በልቶ ደምህን የሚጠጣ
የእናት ሆድ ቀዶ ጽንስ የሚያዉጣ
አውሬው እጅግ ከፍቷል አስወግደው
ለጭቁን ሕዝብህ ሙሴ  ሁነው
    
           አትነሳም ወይ
            አይገድህም ወይ
          አያሳዝንህም ወይ
            አይበቃህም ወይ
         በእሳት የሚነደው ሕዝብ አይደለም ወይ

ሃይማኖትህን የሚያረክስ ጠላት
ጥቁር ጣሊያን የክፋት አባት
ገዳማትህን በእሳት አውድሞ
መነኮሳትን ሲያርድ አጋድሞ

       አትነሳም  ወይ
       አይበቃህም ወይ
      አይገድህም ወይ
      አይጨንቅህም ወይ
      እየተሰቃየ ያለው ወገንህ አይደለም

በፖለቲካ ረሃብ ሕዝብ እየጨረሰ
የኦርቶዶክሳዊያን ዘር ቁጥር እየቀነሰ
ሰው አልተራበም ይላል በሚድያ ወጥቶ
በአባቱ መንፈስ በሰይጣን ተመርቶ

        አይገባህም ወይ
        አይበቃህም ወይ
          አትነሳም ወይ
           በረሃብ የሚረግፈው
           አካልህ አይደለም ወይ

     እናም ወገኔ ሆይ...!!!
      እናም ወገኔ ሆይ!!!

ጠላትህ ሊያጠፋህ ቆርጦ ከተነሳ

ከደጃፍህ መጥቶ ሊውጡህ ካገሳ

በብርቱ ታገለው እንዳት ሰጥእጅ

መብትህን አስከብረህ በ ነጻነት ኑር እንጂ

ሁሉም ሰው ለትግል አእምሮውን ያድስ

ከእንግዲህስ ይበቃናል ተቀምጦ ማለቃቀስ

እንደ  አርበኞቹ  እንደነ አጼ ካሌብ

ሕዝብን ለመታደግ እንነሳ ከልብ

ሃይማኖት ሲደፈር ሃገር ስትፈራርስ

ወገንህ ሲታረድ ደም እንደ ጅረት ሲፈስ

በአርምሞ መመልከት መረገም ነውና
ገዳይህን ታገለው በነቂስ ዉጣና።

በመቻቻል ሴራ የሚያደነዝዙንን
በቁማርተኞች
"ሰላም"የሚያጃጅሉንን

ለሆዳቸው ሲሉ እኛን የከዱንን

ከጠላት አብረው የሚሳለቁብንን

እነርሱን አንስማ አንከተላቸው

ተኩላዎች ናቸውና እንወቅባቸው።

የተገፋው ሕዝባችን ነጻነት የሚያገኘው
በገዛ ሃገሩ ተከብሮ የሚኖረው

በአንድነት ታግለን ለውጥ ስናመጣ ነው።

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment