Thursday, October 30, 2025

በምሥራቅ አርሲ ኦርቶዶክሳውያን ላይ በሚፈጸመው መንግሥት መር ኢስላማዊ ጅሃድ

ብፁዕ አቡነ ያሬድ የምሥራቅ አርሲ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ

በምሥራቅ አርሲ ኦርቶዶክሳውያን ላይ  በሚፈጸመው  መንግሥት መር ኢስላማዊ ጅሃድ የማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ ክፍል ሠራተኞች እልቂቱ ወደ ተፈጸመበት ወረዳ ደውለው ከአንድ ኦርቶዶክሳዊ መረጃ ይቀበላሉ።መረጃ ሰጪው ኦርቶዶክሳውያን ያሉበት አሳሳቢ መሆኑንና የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አባ ያሬድም ለ ጉዳዩ ትኩረት አለመስጠታቸውን ይናገራሉ።ማኅበሩም ድምፁን በሚዲያው ያወጠዋል።ይኽን የሰሙት አቡን ያሬድ ቪድዮው ከሚዲያው  እንዲወርድ በማስፈራሪያ ጭምር አዘዙ። በ ሞቱ ኦርቶዶክሳውያን ሥርዐተ ቀብር ላይ የሚገኙ የሀገረ ሰብከቱ ሠራተኞች ላይም ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደርግም ቀጭን ትእዛዝ ወጥቷል።ይኽ ብቻ አይደለም ከዚህን በፊት "በሀገረ ስብከትዎ ስለሚሞቱት ኦርቶዶክሳውያን ለምን ዝምታን መረጡ "ሲባሉ "ኦርቶዶክሳውያን መሞታቸውን እርግጠኛ አይደለሁም" እስከ ማለት የደፈሩ ሰው ናቸው።እንግዲህ ቤተ ክርስቲያን በእንደነዚህ ዓይነት ሰዎች እጅ ላይ ነው የወደቀችው።#EOTC  የገዳያችንን የብልጽግና ገጽታ የሚገነባ ስለ ኮሪደር ልማት ካልሆነ በቀር ሙሉ በሙሉ ስለ ኦርቶዶክሳውያን እልቂት አይዘግብም።ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል የአዳነች አቤቤ የቅርብ ሰው የሆኑት አባ ሄኖክsilent mood ላይ ቢያስገቡትም አልፎ አልፎም ቢሆን መከራችንን ይዘግባል።#Mktv  ገዳዮቻችንን  በስም እንዳይጠሩአቸው  "ያልታወቁ ኀይሎች" እያሉ እንዲዘግቡ  የሚያደርጉት የ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ  እሾኾች ናቸው።

መፍትሔው ቤተ ክርስቲያንን ከእነዚህ ሰዎች ነጻ ማውጣት ነው።የሚያስገድለን የሚያስጨርሰን እንጂ  የሚያድነን ቤተ ክርስቲያንን የሚያሻግር አባት የለንም።
ይሄ በዚህ ዘመን የተነሣው እጅግ ዘናኝ ግፍ ሲፈጸም ማንም ምንም አይልም ቢያንስ በሃገር ስብክከቱ ላይ በሃላፊነት ያሉት አባቶች እንኳን ይሄ ነገር እንዲቆም ወይም ሁኔታው እንዲሻሻል ምንም አይነት ጥረት አያደርጉም፤ አድርገውም ቢሆን ምንም አይነት ለውጥ አላመጣም ይህ በዚህ ከቀጠለ ምሥራቅ አርሲን ከኦርቶዶክሳውያን ነጻ እናወጣለን የሚሉትን ጂሃዳውያን ሕልማቸው እውን ሆነ ማለት ነው፤ ኦርቶዶክሳውያን በመላው ዓለም ያለን ይሄንን ዘግናኝ ግፍ በምንችለው አቅም ሁሉ ለማስቆም ግፈኞችንም ወደ ፍርድ አደባባይ እንዲቀርቡ የማድረግ ሃላፊነትም መብትም አለን፤ ስለዚህ በዚህ አካባቢ ያላችሁ ኦርቶዶክሳውያን የነገሮች ጠንሣሽ የሆኑት ሰዎች ፎቶ እና ማስረጃዎች ሁሉ እንድትልኩልን በአደራ ጭምር ለመግለጽ እንወዳለን፤ 
ለሃገረ ስብከቱ የሥራ ሃላፊዎች ፤ ለጠቅላይ ቤተክህነት የሥራ ሃላፊዎች ግን አዝነንባችኃል በዚህ መጠን ልጆቻችሁ እንደ በግ ሲታረዱ ሲገፉ ሲፈናቀሉ እና ግፍ ሲደርስባችሁ ከእናንተ ሌላ ማን ይምጣ ማን አቤት ይበል፤ የእነዚህ በግፍ ደማቸው የሚፈሰው ኦርቶዶክሳውያን ደም በእጃችሁ ላይ እንዳለ እወቁት፤ ቢያንስ እንኳን ጸሎት እንዲደረግላቸው አለማድረጋችሁ ሃላፊነታችሁ የዘነጋችሁ እረኞች ያስብላችኃል፤ ትዝብት ነው ትርፉ። 
ይቆየን 

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment