የሚያሳዝነኝ ዛሬ መሞታችን ብቻ ሳይሆን ሞታችን እንዳይቀጥል አንድ አይነት ድምፅ ማውጣት አለመቻላችን ነው ሌሎች እንኳን ሲሞቱ ይቅርና ሲታመሙ እንኳን የሚያወጡት ድምፅ አንድ አይነት ነው እኛ በሞታችን ሳይቀር ዥንጉርጉር ነን ድምፃችንን አንድ አድርገን መኖር ይፈቀድልን ለምን እንገደላለን ከሚል ጩኸት ይልቅ ሞታችንን እንከፋፈልበታለን እነ እገሌ አብረውን አልቅሰዋል እነ እገሌ በደንብ አልጮሁም የእነ እገሌ አለመጮህ ወዘተ እያልን ድምፅ መቀነሳችን ልዩነት መፍጠራችን ወደ ፊት እንኳን ለገዳዮቻችን አንድ ሆነን እንደማንቆም እየነገርናቸው ነው😭😭 ኦርቶዶክስ ናቸው ተብለን እየተገደልን ሞታችን ውስጥ ብዙ ነገር መሥራታችን ሞታችንን በልዩ ልዩ ምንዛሬ ማየታችን እጅግ ያሳዝናል መግደል ባይደክማችሁ እንኳን መሞት ደክሞናል ይበቃል እንበል የተከፋፈለ ሐሳብና የግል አመለካከት ከመሰንዘር ወጥተን ሞታችንን እናስቁም ገዳዮቻችንን እናውግዝ ዝምተኞችን እንቀስቅስ ተናጋሪዎች ንግግራቸው ትክክለኛ ሐሳብ ላይ ያነጣጠረ እንዲሆን እንምከር ሞታችንን ለልዩ ልዩ ፍጆታ የሚጎትቱትን በወንድምና እህት በልጅ በእናትና አባት ሞት ገብያ አትክፈቱ እንበል ያ ካልሆነ በስተቀር ለጊዜው ተነቃቅፈን ተወጋግዘንና ተነቋቁረን ተመልሰን ደግሞ ዝም እንላለን ሞቱም መቀጠሉ አይቀርምና አንድ ሆነን እንቁም ሞታችን ውስጥ በመከራችን የምድጃ እሳት ላይ የግል ነገራችንን ለማብሰል የግል ድስት አንጣድ!😭
የተገደልነው ኦርቶዶክስና ሰው ናቸው ብቻ ተብለን ነውና ሰዎች ተብለን ስለተገደልን ኅሊና ያለው ሰው ሁሉ አብሮን እንዲጮህ እናድርግ
ኦርቶዶክስ ናቸው ተብለን ብቻ ተመርጠን እየተገደልን ስለሆነ ኦርቶዶክሱ ሁሉ አንድ ሆኖ ድምፁን እንዲያሰማ እናድርግ ያ ሲሆን ድምፃችን የእንቁራሪት ሳይሆን አሶፈሪና ጉልበት ያለው የማዕበልና የነጎድጓድ ድምፅ ሆኖ ተሰሚነት ያገኛል

No comments:
Post a Comment