በአርሲ ሀገረ ስብከት በኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚኖሩ 14 ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ።
ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም [ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ]
በአርሲ ሀገረ ስብከት ጉና ወረዳ በሚገኘ ኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን መገዳላቸውን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያሳያል።
በደረሰን መረጃ መሠረት በቀበሌው የሚኖሩ 14 ኦርቶዶክሳውያን ከለሊቱ 6:00 ሰዓት አካባቢ በዕለተ ረቡዕ ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ለ14 አጥቢያ ከተኙበት ከቤታቸው አስወጥተው የታጠቁ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሲሆን ስድስቱ ከመገደላቸው ከአንድ ቀን በፈት ቀድመው ታፍነው ተወስደው ነበር ተብሏል።
የተገደሉት ምእመናን የዕድሜ ክልላቸው ከ2 ዓመት ጀምሮ እስከ 76 ዓመት አዛውንት እንደሚገኙበት መረጃው ይገልጻል።
በተጨማሪም ሁለት ሰዎች በጥቃቱ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ለተሻለ ሕክምና ወደ አቦምሳ ከተማ ሪፈር መሄዳቸውን በመረጃው ተያይዞ ተነግሯል፡፡
ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ በቀበሌው ውስጥ የሚኖሩ 8 ኦርቶዶክሳውያን ሌሊት ላይ ከቤታቸው አስወጥተው የታጠቁ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸውን በደረሰን መረጃ ለማወቅ ችለናል።
ከተገደሉት ምእመናን ውስጥ 6ቱ በገገሌ በዓለወልድ ቤተ ክርስቲያን፣አንድ ደግሞ በሞዬ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን እና ቀሪ ሟቾች ባሉበት አካባቢያቸው ሥርዓተ ቀብራቸው መፈጸሙ ተገልጿል።
በመረጃው እንደተመላከተው በቀበሌው ባለ ከፍተኛ ስጋት በቀጣይ የባሰ ችግር እንዳይፈጠር በሀገረ ስብከት ደረጃ ከመንግሥት ጋር በጋራ መሥራት ይገባል ተብሏል።
በአሁኑ ሰዓት በአካባቢው ሁኔታዎችን ለማረረጋት የሀገር መከላከያ በስፍራው እንደሚገኝ በመረጃው ተጠቅሷል።
©ማኅበረ ቅዱሳን
በምሥራቅ አርሲ ዞን የኦርቶዶክሳውያን መታረጃ ቄራ በሆነችው በሽርካ ወረዳ በሄላ ዘምባባ ቀበሌ በዘምባባ አርሴማ በትናንትናው ዕለት በቀን17/02/2018ዓ.ም በዘምባባ አርሴማ ምሸት 4:00 በኦነግ/ብልጽግና መንግሥት የሚደገፈው ራሱን የኦሮሚያ ኢስላማዊ መንግሥት IslamicStateOfOromia ብሎ የሚጠራው ጅሃድስት ቡድን ኦርቶዶክሳውያንን ከ ቤት አውጥቶ በእ ሰቃቂ ሁኔታ የረሸነ ሲሆን አራቱን ደግሞ አግቶ ወስዳቸዋል።በግፍ የተረሸኑት ፦
፩ ማሙሽ ደርቤ እድሜ 30
፪ ትግስት ጅማ እድሜ 50
፫ ግዛው ከተማ እድሜ 40
ታግተው የተወሰዱት ኦርቶዶክሳውያን፦
፩አስታጥቄ ደርቤ
፪ ከተማ ተክሉ
፫በኃይሉ አበባየሁ
፬ ሲሳይ ከተማ
በግፍ የተረሸኑት በዛሬው ዕለት 18/02/2018 ዓ.ም በዘምባባ አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ሥርዐተ ቀብራቸው ተፈጽሟል።አግተው የወሰዷቸውንም ሊገድሏቸው እንደሚችሉ መረጃዎች እየወጡ ነው።
ኦርቶዶክሳውያን ሆይ ምን ይሻላል?እንዲህ እንዲህ ተራችንን እየጠበቅን እንለቅ ወይስ በኅብረት ቆመን ዋጋ ያለው ሞት እንሙት?
@ኢዮሳፍጥ ጌታቸው
No comments:
Post a Comment