Tuesday, October 28, 2025

የተነሳው አወዛጋቢው ነገር ምንድነው? መፍትሔውስ ምን ሊሆን ይችላል ከኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ

የምንሰውማ ጉድ ምንድነው? 

አዲስ የተገዛው የ8 ሚሊዮን የቅድስ ተ/ኃይማኖት ቤ/ክ አሜሪካ
በቨርጂኒያ ቅዱስ ተክለኃይማኖት ቤተክርስቲያን አጥቢያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከበድ ያለ ጭቅጭቅ እና ንትርክ የሚመስል ነገር ተነስቷል ፤ ከብዙ የብሎጎች እና የቴሌግራም ግሩፖች እንደተረዳነው፤ ይሄ ቤተ ክርስቲያን ከተመሠረት ከአሥራ ሁለት ወይም ሦስት አመት በላይ በአገልግሎት እንደቆየ ይነገራል ፤ ነገር ግን ቦታው ከተገዛ ቅርብ ጊዜ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለያዩ ጣልቃ ገብነት በተለይ ከባሕርዳር ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አቡነ አብርሃም በቀጥታ ጣልቃ በመግባት በቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ እና በቤተክርስቲያኑ ምዕመናን ጋር የተነሳውን አለመግባባት ለማስማማት ሳይሆን ያልተፈጠረውን ታሪኩን በማጣመም ሌላ እንደሆነ አድርገው በማቅረብ በምዕመናኑ እና በቤተክስቲያኑ ምዕመናን መካከል ከፍተኛ አምባጓሮ አይነት መነሳቱን እና ፖሊስ ተጠርቶ እንደነበር የታሰሩ ምዕመናን እንዳሉ ግን የድረሰን መረጃ ባይኖርም፤ ፖሊሶች ግን በቦታው ላይ መጥተው ወደ ቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ገብተው እንደነበር መረጃዎች ደርሰውናል፤ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ለመረዳት እንደቻልነው፤ የሚከተለውን መረጃ ለዚህ ሚዲያ ቤተሰቦች ለማድረስ ፤ ነው፤ 
በቀጣይነት ያሉትን እየተከታተልን እንዘግባለን፤ በዚህ አጥቢያ ያሉትንም ምዕመናን መረጃውን ብታደርሱን በሚዲያችን ለማስተናገድ እንደምንችል ከወዲሁ ለማስታወስ እንድወዳለን፤ 

📝የሚሰማው ምንድን ነው ? 

👉በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው  በቅርቡ ስምንት ሚሊዮን ዶላር (8Million $) ወጥቶበት  የተገዛው የምሥራቀ ጸሐይ ቅዱስ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን  ቨርጅኒያ በመሀከላቸው ምንድን ነው የተፈጠረው ?

👉 የሚሰማው ደስ አይልም  ፦ ከእናንተው ይምጣ ብለን እንጂ ፣ በቪዲዮም ሆነ  በጽሑህፍ እና በድምፅ  የቀረቡትን መረጃዎች  አይተናል ፣ ቀደም ሲልም ቤተክርስቲያኑ ሳይገዛ በፊት በአውደ ምሕረቱ  ጭምር የነበረውን ምልልሶች አይተናል፣  የአሁንም ለሚዲያችንም ደርሶናል ።

👉ተፈጠረ የተባለውንም ችግር  ዋጋ ለከፈለው ለሕዝበ ክርስቲያኑ ( ለምዕመኑ ) ብሎም ለወጣቱ ትውልድ ስብራት እንዳይገጥመው  በማሰብ ይህ ፈተና መሆኑንን በማመን  በርን ዘግቶ መክሮ ለመፍትሔ አንድ ልብ መሆኑ ግን ሚዛን የደፋ ምርጫ እንደሆነ  ለመጦቆም እንወዳለን ።

👉መረጃው እውነት ቢሆንም  ከባለጉዳዮቹ ስላልመጣ ዝርዝሩን ለማውጣት አልፈለግንም ፣ በየትኛውም በኩል  ላሉ ባለ ድርሻ አካላት  እውነት አለን  ሕዝብ ማወቅ አለበት ካሉ ግን ሚዲያችን በሩ ክፍት ነው ። 

                  📌ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment