Friday, July 6, 2012

በዋልድባ ውጥረቱ ቀጥሏል. . . ESAT Radio Interview

በዋልድባ ገዳም ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው፥ እስራቱ፣ እንግልቱ፣ ማሳደዱ፣ ድብደባው በፌደራል ወታደሮች እንደቀጠለ ነው ገዳማውያኑ አባቶቻችንም ጩኽታቸውን አቤቱታቸውን በመላው ዓለም ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን እያስተላለፉ ነው፥ ዝምታውም ቀጥሏል መንግሥትም መፍረሱን እንደቀጠለ ነው። ዝምታችን ይብቃ ገዳማውያኑን እና ታሪካዊ ገዳማችንን እንታደግ እንተባበር። 

በተለይ በአሁን ሰዓት ቤተክርስቲያን ልጆቿን የምትፈልግበት ወቅት ላይ ደርሰናል በሃገር ውስጥም ሆነ በውጪ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ስለቅድስት ቤተክርስቲያን ስለሃገራችን ስለገዳማውያኑ በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ ገዳም ውስጥ የሚገኙት ገዳማውያን ለሃገር በጸለዩ፣ ለወገን በለመኑ፣ ለመሪዎች እና ለሃገር ወደ አምላካችን በለመኑ በየገዳሙ ዛሬ እስራት፣ ግርፋት፣ እንግልት እንዲሁም ግድያ እየደረሰባቸው ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ ከዚህ የከፋ በቤተክርስቲያናችን ላይ ሊመጣ አይችልም ስለዚህ እግዚአብሔር ያከበራችሁ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ቆሞሳት፣ ካሕናት አባቶች መከኩሳት፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ መምሕራን፣ ዘማሪያን፣ ዲያቆናት እንዲሁም የቤተክርስቲያን ፈርጦች የሆናችኊ ምዕመናን በሙሉ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ከዮዲት ጉዲት እና ከግራኝ መሀመድ በኃላ እንዲህ ዓይነት ፈተና ገጥሟት አያውቅም ስለዚህ ከሊቅ እስከ ደቂት ተባብረን ልዩነታችንን ወደ ጎን ትተን ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ልንታደግ ይገባናል እንላለን።


ዛሬ ቤተክርስቲያን ከእያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ የመክሊቱን እንዲያበረክት ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታቀርባለች፣ ገዳማውያኑ የወገን ያለህ እያሉ ነው ስለዚህ በዚህ ታሪካዊ ጥሪ ተቀብለን የበኩላችንን ጥረት ለማድረግ አምላከ ቅዱሳን የጻድቁ አባ ሳሙኤል ዘዋልድ
ባ አምላክ እንዲረዳን ሁላችን ከሕፃን እስከ አዋቂ ወደአምላካችን ልንጸልይ ይገባናል።
ገጸ ምሕረቱን ይመልስልን ለሕዝባችን፣ ለሃገራችን፣ ለቤተክርስቲያናችን አሜን
ለማንኛውም መረጃ በሚከተሉት ሊያገኙን ይችላሉ
savewaldba@gmail.com
Save Waldba Foundation
PO Box 56145
Washington DC 20040


ከsavewaldba የተገኘ
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment