Tuesday, July 17, 2012

ሰዎች ምን ይላሉ?



፳ የአምባገነንነት፣ የሙስና፣ የዘረኝነት፣ የዝቅጠትና የአድርባይነት ዓመታት
የመጀመሪያ አስተያየት ሰጪ
''አይቴ ለነውር ብሔረ ሙላዱ 
በውስተ ኩሉ ብሔር እስመ ከመ ነግድ ይሄሉ 
ጠይቆተ ዝኒ ነገር ከመ ይትገሀድ ለኩሉ 
ኃጥእ ይሣለቅ ላዕለ ጻድቅ ከመ ዘንጹሕ ወሠናይ ባህሉ፥
እስመ እንዘ ሠርዌ በውስተ ዐይኑ  
እምነ ቢጹ ብሩህ አውጽኦተ ሐሠር ያስተዴሉ።
አይሁድኒ ሐዋርያተ በጽእሎቶሙ ጸዐሉ፥
ጊጉያነ ወአብዳነ ወሐሳውያነ እንዘ ይብሉ፥
ወብእሴ ጻድቀ ዘሀለዎሙ ይስቅሉ፥
እንዘ ውጹኣን እምነ ጽድቅ በጽድቀ ርእሶሙ ይትሌዐሉ። '' 
መወድስ ቅኔ ዘአለቃ ንጉሤ።
አባ ጳውሎስና ተከታይ የሥጋና የግብር ልጆቻቸው ያፈረሱትን እኮ ነው ገነባን የሚሉት። ቀኖና ቤተ ክርስቲያንንአፍርሰው በጦር መሳርያ ሃይል ቀምተው የተቀመጡበትን መንበር ማፍረሻ እንጅ መገምቢያ እንዳላደረጉትየሚታወቀውን ነገር ለራሳቸው ካልሆነ በስተቀር ለማንም ሊሸጡት የማችሉት የረከሰ ሸቀጥ መሆኑን መረዳትየሚያስችል አዕምሮ እንደሌላቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠንቅቆ ያውቃል። ተዋቸው የራሳቸውን ጽድቅ ለራሳቸውእያስተጋቡ ለጊዜው ይቀጥሉ።


ሁለተኛ አስተያየት ሰጪ
በአባ ጳውሎስ ዘመነ ሥልጣን ቤተክህነት የደረሰባትን አስተዳደራዊና መንፈሳዊ ውድቀት ለሚረዳ ሰውእውነትም ኮሜዲ ነው:: የሚገርመው ውጤትን በምን መስፈርት ቢለኩ ነው እንዲህ ለማለት የቻሉት:: መቼስየቤተክርስቲያንን አተዳደራዊ እድገትና የምእመናንን በሐይማኖት መጠንከር ሳይሆን ፓትርያርኩንና ግብረአበሮቻቸው በግል ያካበቷቸውን ንብረቶች ቆጥረው ከሆነ ከልብ ያሳዝናል:: ምክንያቱም ፓትርያርኩ ሱሾሙየተሰጣቸው ኃላፊነት ይህ አይደለምና:: በጣም እንዳላዝን የሚያደርገኝ ነገር ቢሮር እንዲህ ብለው የጻፉ ሰዎችትናንትና ሐውልት ያቆሙላቸው ግለሰቦች ስለሚሆኑና ሐውልት ከማቆም የበለጠ ቀልድ ስለሌለ ነው::ለማንኛውም 20 ዓመታት እናት ቤተክርስቲያን ተጎድታ ቆይታለችና ለቀጣይ 20ዓመታት ተመሳሳይ ፈተናእንዳያጋጥማት የሁል ጊዜ ምኞቴ ነው:: እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን::

ሶስተኛ አስተያየት ሰጪ (  ሐመረ ኖህ )
እኛ ዝም እስካልን ድረስ በተዋህዶ እምነታችንንና በኛም ላይ ገና ብዙ ግፍ ይሰራል  የኑፋቄ የውርደትየዘረኝነት የመከፋፈል የአምባገነንነት የሙስና የዝቅጠት የአድርባይነት የፈተና ሁሉ ፈተና የቅንጦተኞችዘመን አሳልፈናል አሁንም ዝም ካልን ይቀጥላል ሌላው ሁሉ ይቅርና ማለትም ዘርዝረን ስለማንጨርሰውየለበሱት ልብስ ለ፳ኛ ሲመታቸው ይሆን እጅግ በጣም ውድ ነው ስንት በገዳም የሚጋኙ በቀን አንዴመመገብ ላልቻሉ ለታረዙ መነኮሳትና የአብነት ተማሪዎች ለዓመት ቀለብ ይሆን ነበር እኔስ ከአሕዛብበእምነታቸው ሳይሆን በትግላቸው ቀናሁ ከሞተ አንበሳ ሕይወት ያላት ትሻላለች
ከአኖነመስ
20 አመታት የቤተክርስቲያን የፈተናና የወደኋላ ጉዞ ዘመናት!
ሰው ግን እስከመቼ ነው ለሆዱ የሚኖረው? እውነት ከልባቸው ነው ግን "20 ውጤታማ አመታት" ብለው የጻፋት?
ከደጀ ሰላም የተወሰደ

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment