Tuesday, July 17, 2012

የዲሲው አባ መላኩ/ አባ ፋኑኤል - እዚያው በጸበልዎ ! ከሲያትል ዋሽንግተን


ሰሞኑን ወደ ሲያትል ዋሽንግተን ለመሄድ በዝግጅት ላይ የሚገኙት አባ ፋኑኤል ገና የመምጣታቸው ዜና ከመሰማቱ ጀምሮ በርካታ
የአካባቢው ምዕመናን ተቃውሞ እያሰሙ ነው። በሲያትል ዋሽንግተን ከተማ የሚገኙ ቤተክርስቲያናት በተለይ የቅዱስ አማኑኤል
ቀንደኛው የተሃድሶ ጋሻ ጃግሬ ከነባራኪው
የቅዱስ ሚካኤል፣ የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያናት ምዕመናን ድምጻቸው የሁሉም አይምጡብን፣ አይድረሱብን እርሶ ይዘው የሚመጡት ከፋፋይ እና በታኝ ሃሳብዎን "እዛው በጸበልዎ" እያሉ ይገኛሉ፤ ነገር ግን በተቃራኒው የሕዝበ ክርስቲያኑን እሮሮ እና ቁጣ ችላ በማለት ስልጣን እና ሹመት ወይም ጥቅም ፈላጊ እና ለነፍሳቸው ሳይሆን ለሥጋቸው ባደሩ የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች ጋባዥነት እና ጋሻ ጃግሬነት ወደ ሲያትል ሕዝብ ለማስገባት የሚሞክሩ ካህናት ሥራቸውን ቀጥለውበት በተለይ የቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን አስተዳደር የሕዝበ ክርስቲያኑን ጥያቄ እና አቤቱታ ወደ ጎን በመተው በማናለብኝነት ከፋፋዩን ከነ ጋሻ ጃግሬያቸው ኃይለጊዮርጊስ ጋር ለመስተናገድ ሽር ጉድ እያሉ ይገኛሉ። በዚህም ምክንያት ነው ከዚሁ ከሲያትል አካባቢ የሚገኙ የቤተክርስቲያኒቱ ቁርጠኛ ልጆች ከነዚህ የተሃድሶ አቀናባሪዎች ሕዝቡን ለመታደግ መልዕክቶችን በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ፣ "የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመቱባችሁ ተኩላዎች ተጠበቁ" በማለት ድምጻቸውን እያሰሙ ያሉት። የዝግጅት ክፍላችን መልክቱ ደርሶናል እና ለአንባቢያን አቅርበነዋል። መልካም ንባብ . . .


"ጅብ የማያውቁት ሀገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ ይላል"
                                                                                                               ሰኔ 5 ቀን 2004 ዓ/ም
ከላይ የተጠቀሰው ሀገራዊ አባባል በእንስሳት በላነቱና አጥፊነቱ የታወቀው ጅብ የማይታወቅበት ሀገር ሂዶ የማይገባውን ክብር ወይም የክብር ቦታ ለማግኘት መሞከሩን ያሳያል :: የጅብ ማስመሰል ለመብላት ነው:: ለማጥፋት ለማረድ ነው:: ከሰሞኑም ይህ ነገር በአባ መላኩ /አቡነ ፋኑኤል / ሲያትል ሊደገም ይመስላል :: ጨዋ መስለው አባት መስለው : ሀገር አቅኚ መስለው : ህዝብ ሰብሳቢ መስለው : ሕገ ቤ/ክን አክባሪና አስከባሪ መስለው ሲያትል ቅዱስ አማኑኤልና ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ሊመጡ እየተዘጋጁ እንደሆነ ነው የሚሰማው ::



አይ ዘመን ! አይ ስምንተኛው ሺህ ! መንፈሳዊ መስለው አለማዊ ሥራ የሚሠሩ : መንኩሰናል : ለአለምና ለኃጢአት ሞተናል እያሉ: ለፖለቲካ : ለገንዘብ : ለጥቅምና ለሥልጣን የሚሠሩ “መነኮሳት”/ ካህናት የበዙበት ዘመን ! እግዚኦ : አድነን አውጣን ነው !
የወያኔ የቀድሞ መሪ የነበሩት ዶ/ር አረጋዊ በርሔ ስለ ወያኔ ታሪክ በጻፉት መጽሐፍ እንደተገለጠው በሥልጣን ላይ ያለው መንግስት : የፖለቲካ አላማውን የሚያስፈጽሙለት ካህናት መሳይ : መነኮሳት መሳይ ካድሬዎችን መልምሎ የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ውስጥ ተሰግስገው የዘረኝነት : የመከፋፈል ሥራዎች እየሠሩ እንደሆነ ይታወቃል ::

ቤተ ክርስቲያን የሁሉም ኢትዮጵያውያን አማኞች ሁሉ ብትሆንም እውነተኞቹን ሊቃውንቱን እየገፉ : ምሁራኑን እያስወጡ (እነ አለቃ አያሌውንና ብዙዎቹን መጥቀስ ይቻላል) : በየቦታው በደብር አለቅነት/ ሀላፊነት የሚሾሙት በዘር ግንድ እየተመለመሉ የአንድ አካባቢ /ቋንቋ ተናጋሪዎች/ ወይም ዘራፊና ቀማኛ ተባባሪዎቻቸው ናቸው :: እነዚህ ካድሬ ካህናት/መነኮሳት/ ዋና ሥራቸው ምዕመኑን መሠለል ነው :: ቢቻል የአላማቸው ደጋፊ ለማድረግ ምልመላ ማካሄድ ነው:: ካልሆነ ማበጣበጥ: ህዝብን ማለያየት መከፋፈል የተሰጣቸው “መንፈሳዊ ሀብት” ነው:: ለነዚህ የሃይማኖት ሥራው ማጥመቅ ማቁረቡ: ማስተማሩ ሽፋን አልያ የትርፍ ጊዜ ሥራ ነው :: ዝቋላ ብትቃጠል : ዋልድባ ቢታረስ : ቤተ ክርስቲያን ቢዘጋ: ምእመናን ቢበተኑ: አክራሪዎች ጥፋት ቢፈጽሙ ግድ የላቸውም :: አላማቸው አይደለምና !

አባ መላኩ/ አባ ፋኑኤል/ ማን ናቸው ?

በዋሽንግተን ዲሲ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክን ከ10 ዓመት በላይ የአቡነ ጳውሎስን አስተዳደር በማውገዝ ገለልተኛ አስተዳደር ነው የምከተለው በማለት ህዝቡን ሲያታልሉ/ ገንዘቡን/ ሲዘርፉ የነበሩ አፈ ጮሌ ብልጣብልጥ መነኩሴ ናቸው :: ከኢህአዴግ መንግስት ተቃዋሚዎች ጋር ግንባር ቀደም ተሰላፊ እየሆኑ : መግለጫ እየሰጡ አይዟችሁ በርቱ ሲሉ ነበር :: የአሜሪካንን መንግስት የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቀው እስከ ዜግነት ድረስ አግኝተዋል::
እንደ ግል ንብረታቸው/ድርጅታቸው/ ከሚያዙበት ቤተ ክርስቲያን የሚፈልጉትን ያህል ገንዘብ ከሰበሰቡ በኋላ : ሥልጣን ሲያምራቸው ቤተ ክርስቲያኑን ለታማኞቻቸው ሰጥተው ትላንት ሲያወግዟቸው ከነበሩት አቡነ ጳውሎስ ጋር በመሻረክ በእጅ መንሻ ትልቁን የቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት ሥልጣን “ጵጵስናን” ተቀብለዋል:: በመጽሐፍ ቅዱስ መንፈሳዊ ስልጣንን በገንዘብ የሚገዛና የሚሰጥ ሰው መወገዙን እንረዳለን :: ወይ የዘመናችን ጉዶች ! ይህ ነው ስምንተኛው ሺህ !
የቀድሞው አባ መላኩ የአሁኑ አባ ፋኑኤል ለሌላ መንፈሳዊ ኦርቶዶክሳዊ ላልሆነ ተልዕኮ ሚሽነሪ ሆነው ወደ አሚሪካ ተመልሰው መጥተዋል :: በአዋሳ ያደረጉት ብጥበጣ : ያፈሰሱት እንባ : በመንፈሳዊ ኮሌጅ የደረሰባቸው ተቃውሞና ውግዘት ብዙ ነው:: ዛሬም በዋሽንግተን ዲሲ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ብዙ ችግር እያስከተሉ ነው::

የዲሲው አባ መላኩ/ አባ ፋኑኤል - እዚያው በጸበልዎ !

በሀገር ቤት ያለውን ሲኖዶስ እወክላለሁ ይላሉ : አካሄዳቸውና አሠራራቸው ግን ከሲኖዶስ ውጭ ነው :: አሁንም መቀመጫቸው ገለልተኛ ቤ/ክን ውስጥ ነው :: የግል ንብረታቸው በሆነውና መንበር ባደረጉት ደብር በቅዳሴ ጊዜ የፓትሪያርኩ ስም አይጠራም :: ሁለት ቃል ተናጋሪ : ሁለት ምላስ ያላቸው አፈ ቅቤ ሆደ ጩቤ አይነት ናቸው :: በውጭ ያለውንና የሀገር ቤቱን ሲኖዶስ አስታርቃለሁ ይላሉ ሥራቸው ግን ማለያየት ነው :: ራሳቸው ሕገ ቤተ ክርስቲያን ሳያከብሩ ሌላውን እንዴት አክብሩ ሊሉ ይችላሉ? እውር እውርን ቢመራው ተያይዞ ገደል እንደሚል ቅዱስ መጽሐፍ::

እዚያው በጸበልዎ ! አባ ፋኑኤል !

የጥፋት ሥራዎን እናውቃለን : የመጡበትንም ሚሽን እንረዳለን: መናፍቁና መሰሪውን “ዲ/ን” ኃይለ ጊዮርጊስን ፊት አውራሪ ሌሎች ጀሌዎችና ካድሬዎችን ተባባሪ አድርገው ብዙ የመለያያ : የጥፋት እቅዶች እንደያዙ አውቀናል :: ሌባ ሊያርድ ሊያጠፋ ይመጣል እንደተባለ የእርሶም አመጣጥ እንዲሁ ነው::

ስለዚህ እዚያው በጸበልዎ ! አይድረሱብን ! አይምጡብን ! በቤተ ክርስቲያን አምላክ ስም እንጠይቆታለን !
ሲያትል ለሰላም ሰው ለእውነተኛ የሃይማኖት ሰው እንጂ ለምንደኛ እረኛ ቦታ የላትም ! በበግ ለምድ ለሚመጡ ቀበሮዎች ስፍራ አትሰጥም : ቁርበት አታነጥፍም :: በዓይናማ መሪ እንጂ ተደናብሮ በሚያደናብር መሪ አትመራም ::

አባ ፋኑኤል : አልታደሉም እንጂ የያዙት/ በገንዘብ የገዙት/ ሥልጣን ታላቅ ነበር :: ምድራዊውን ብቻ ሳይሆን ሰማያዊውን በር የሚያስከፍት ቁልፍ :: ምን ያደርጋል ለሚገባው ሥራ አልተጠቀሙበትም ! ሥልጣኑን የተቀበሉት ለክብር : ሊበሉበት እንጂ መች ሊሠሩበት ሆነና ! መንኮስ ሞተ የሚለው የግእዝ ቃል ትርጉም በርሶና መሰሎችዎ ምክንያት መነኮሰ በላ ተብሏል:: ሆዳቸው አምላካቸው የተባለበት ያልተባረከ ዘመን:: ደጋጉ ቅዱሳኑ : እውነተኞቹ ፈሪሃ እግዚአብሔር : አክብሮተ ሰብ ያላቸው አበው : መነኮሳት የተሰወሩበት ዘመን !

ለማንኛውም ሲያትል እግዚአብሔር ፈቅዶ ሌላ እውነተኛ እረኛ እስክታገኝ ድረስ አድነነ እግዚአ /አቤቱ አድነን ደግ ሰው አልቋልና እያለች የቅዱስ ዳዊትን መዝሙር መዘመር ትፈልጋለች:: ሌላ ዙር ሁከት ረብሻ ውስጥ መግባት አትፈልግምና አደራ አይምጡብን ::
የአባ ፋኑኤል ጋሻ ጃግሬዎች!

ሁሉን እያወቅን ዝም ብንል : ሰላም ፍቅር እናድርግ ብንል : እግዚአብሔር መፍትሔ ይስጥ ብለን ብንል የምታደርጉትን ሥራ የማናውቅ አይምሰላችሁ :: ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም ስንል ነው:: ተዉ ! ለቅድስት ቤ/ክን ሰላም : ለምዕመናን አንድነትና ፍቅር ብትሠሩ ይበጃችኋል ! የእግዚአብሔር ከሆናችሁ የእግዚአብሔርን ሥራ ሥሩ :: ዓላማችን ሃይማኖት ይጠበቅ : ሥርዓት ይከበር :: እግዚአብሔርን አምኖ: ሃይማኖቴ ብሎ ሁለመናውን ለቤተ ክርስቲያን የሠጠውን ምእመን መቀለጃ ወይም ሞኝ አታድርጉት :: ሰበካ ጉባኤም: ሰንበት ት/ቤቶችም: ምእመናንም ደብራችሁን ጠብቁ : ለጥቂቶች መጠቀሚያ ርስት አትተዉት::
ባለ ሁለት ምላሱ : ሚሽነሪው አባ ፋኑኤል መጥተው ለሚከሰተው ችግር ራሳችሁ ኃላፊነት ትወስዳላችሁ ! ኋላ ባለጌ የተመከረለት:
ዋንጫ የተረገጠበትለት ይብሳል የሚለው ተረት እንዳይደርስባችሁ !


ሙሉውን ደብዳቤ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ


ማተባችንን እንጠብቅ የምንል ምእመናን ነን ከሲያትል ዋሽንግተን



የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

1 comment:

  1. teru sera yseru abatochnem BTEZEKERU teru new alebleza hulum abat metfo sera yeseral ymilewen amlekaket mesbek endayhonbachu mdehanitem side effect alw be be careful!

    ReplyDelete