በቅድሚያ እንኳን ለጌታችን እና ለመድኅኒታች ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት ሁላችንንም በሰላም አድረሰን እንዲሁም ቅዱስ
| አባ ፍቅረማርያም አጣናው |
ሚካኤል ቃና ዘገሊላ ሁላችንንም በያለንበት በስላም አድረሰን እንላለን፤ ባለፈው በአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አስተዳደር ላይ ሰፋ ያለ ዳሰሳ አዘጋጅተን እንዳስተላለፍን ይታወሳል፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአቡነ ተክለሃይማኖት አስተዳዳሪ የሆኑት አባ ፍቅረማርያም አጣናው አንተነህ በአቡነ አብረሃም አማካኝነት ከኢትዮጵያ መጥተው አንገታቸውን ደፍተው የተጠጉት እና የሕዝቡን ፍቅር እና አክብሮት ካገኙ እና ሁኔታዎች በሙሉ በእኔ ቁጥጥር ስር ነው ብለው በአመኑበት ሰዓት ይልቁንም አሁን ባለው አዲስ በተገዛው ሕንጻ ላይ የበላይነታቸውን ይዘው ከዚህ በኃላ ከእኔ በስተቀር ማንም ሰው በዚህ አጥቢያ ላይ ሊያዝም ሆነ ሊናዝዝ አይችልም ብለው አምነው ወይንም ተመኝተው ሕዝቡንምም ሆነ ማኅበረ ካሕናቱን እየተጠበጡት የሚጉኙት የቀበሮው መነኩሴ ዛሬ ላይ በርካታ ካህናትን በማገድ፤ እንዲሁም ብዙ መከራ አይተው በገንዘብ፣ በእውቀት እንዲሁም በሙያ ሲያግዙ የነበሩትን ምዕመናን ከዚህ በኃል የዚህ አጥቢያ አባል አይደላችሁም በማለት በማገድ ማሕበረ ምዕመናኑን በተለይ ይቃወኛል ወይም እኔ በምለው መንገድ አይሄድም ብለው ያሰቡትን በሙሉ በማገድ፤ ማኅበረ ምዕመናኑን በማወቅ በተለይ በዚህ አጥቢያ ላይ ከባድ የሆነ ይልቁንም በመላው አሜሪካ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የማናለብኝነት እና የጎጠኝነት ሥራቸውን እይሰሩ እያ እያስፋፉ ይገኛሉ።
በተለይ በዚህ ሰዓት ይህ የቀበሮ መነኩሴ በመቅበዝበዝ ላይ አንዴ ዋሺንግተን ዲስ አንዴ አዲስ አበባ እያሉ እየተመላለሱ
በተለያየ ምክንያት ከዋሺንግተን ዲሲ ወደ አዲስ አበባ በተለያዩ ሁኔታ መረጃዎችን ይልቁንም የእርሳቸው ተቃዋሚ የሆኑ ምዕመናንን
ለብልጽግናው መንግሥት ለማስጥቆር ወደ ኢይትዮጵያ በሚመጡበት ወቅት በሰዎቹ ላይ ብዙ ፈተና እንዲደርስባቸው በማሰብ ይልቁንም ለብልጽግናው
መንግሥት ታማኝነታቸው ለማሳየት በሚመስል መልኩ የተቻላቸውን ያክል እላይ እታች እያሉ ይገኛሉ፤ ብዙ ሰው እንዴት ለብልጽግና ይሰራሉ
የሚል ጥያቄ ሊያስነሳ እንደሚችል ብዙዎች ሊጠይቁ ስለሚችሉ በአጭሩ ፤ መነኩሴው በአንድ አጥቢያ ተቀጣሪ የሆኑ መነኩሴ ሆነው ሳለ፤
አንድ መነኩስ ለዚያውም መነነ መነኮሰ፣ እራሱን ለእግዚአብሔር ሰጠ የሚባል መነኩሴ እንዴት በዓመት ሦስት እና አራት ጊዜ ወደ አዲስ
አበባ ይልቁንም ወደ ጎተራ አካባቢ በሚገኘው ቅንጡ ኮንዶሚኒየም በመሄድ ሦስት አራት ጊዜ ለአንድ ለሁለት እስከ ሦስት ወራት ሊያሳልፍ
ይችልላል? ለዚያውም ተመልከቱ፤ በትንሹ ለሦስት ጊዜ ቢሄዱ እና በእያንዳንዱ ጊዜ ለሁለት ወራት ቢቆዩ፤ በዓመት ወስጥ ስድስት ወራትን በአዲስ አበባ ፤ ስድስት ወራትን ደግሞ በዋሺንግተን የሚቀመጥ መነኩሴ በየትኛውም መመዘኛ ሌላ ድብቅ የሆነ ሚስጢር ከሌለው በስተቀር
በዚህ ሁኔታ ሊያሳልፍ እንደማይችል ይገመታል፤ በብዙዎች ግምት የተለያዩ መላምቶች ናቸው መረጃውን በቅርብ ጊዜ የመረጃ ክፍላችን
አነፍንፎ ለአንባቢያን ለማድረስ ቃል እንገባለን፤ መላምቶቹ
1ኛ/ እንደተባለው ለብልጽግና በመሥራት በሁለት ቢላ የሚበላ የቀበሮ መነኩሴ ሆነዋል
2ኛ/ ቅምጥ ኑሯቸው ልጆችን ለማሳደግ ከዋሺንግተን ወደ አዲስ አበባ የሚመላለሱባቸው ሁኔታዎች አሉ ፤ ልጆችም አባታችን
የት አለ በማለት የሚያስቸግሩ ከሆነ ግማሽ ኑሮ ከዚህ ግማሽ ኑሮ ከዚያ ማድረግ ግድ ስለሚሆን፤
3ኛ/ ሌላ ድብቅ የሆነ ምስጢራዊ ሥራ በመስራት ላይ ናቸው፤ ከግብራበሮቻቸው ጋር በዛው በዋሺንግተን እና በዚህ በአዲስ
አበባ የሚኖሩ ግብረ አበሮች (ግብረ በላዎች) እንዳሉ ይታመናል
4ኛ/ ከዚህ በፊት በተለያየ ማባበያ እየሰጡ ወደ ጵጵስና ሹመት ለመድረስ የሚያደርጓቸው ሥራቸውን ዛሬ በቅርብ ሆነ ለብልጽግና
ተላላኪ በመሆን በመሥራት ወደሚመኙት ጵጵስና ለመድረስ ሙከራዎችን በቅርብ ከዚህ ከአዲስ አበባ በመሆን በቅርብ በመከታተል ላይ ናቸው
ማለት ነው፤
ከላይ የጠቀስናቸው የሚባሉ እና ብዙዎችም የሚስማሙበት እውነት ነው፤ ነገር ግን የዝግጅት ክፍላችን ማረጋገጫ እና መረጃ
ባለመኖሩ በእርግጠኛነት ይሄኛው ነው ምክንያቱ ብለን ለማለት ጊዜው ገና በመሆኑ በቅርብ ጊዜ ውስጥ መረጃዎችን በማቀናጀት እውነታውን
ለአንባቢያን ለማድረስ በድጋሚ ቃል እንገባለን፤
በሌላ በኩል ደግሞ በዚህ አጥቢያ ማለትም በአቡነ ተክለሃማኖት አጥቢያ ለብዙ ዓመታት ሳይመረጥ እና በዚሁ በቀበሮ መነኩሴ
በግል ጥቆማ ብቻ እየተሸሙ የቆዩ “የሰበካ ጉባኤ” ወይንም በሃገሩ አጠራር ቦርድ የሚባል ሰውየው በግል የሚያውቋቸውን እና ታማኝ
አገልጋዮቻቸውን ብቻ እየመረጡ ሲያስቀምጡ ቆይተው አሁን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዚህ አጥቢያ ማለትም በአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን
ውስጥ የሰበካ ጉባኤ ምርጫ ለማድረግ አስመራጭ ኮሚቴ በጠቅላላ ጉባኤው ተመርጠው እያለ መነኩሴው አዲስ አበባ በለመዱት መልኩ አስመራጭ
ኮሚቴውን በማገድ ለራሳቸው በሚመች መልኩ ሊሰሩ እና የራሳቸውን ሰው እንዲመረጥ በማሰብ አስመራጭ ኮሚቴውን ሕጋዊ ባልሆነ መልኩ
የእግድ ደብዳቤ አውጥተው፤ የአስመራጭ ኮሚቴውን እግድ አውጥተውበታል፤ (የእግዱን ደብዳቤ ለጊዜው እጃችን ባይገባም፤ የመረጃ ምንጫችን
በቅርቡ እንደላኩልን፤ ለአንባቢያን እንደምናደርስ ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን) በመሆኑም ማኅበረ ምዕመናን እና ማኅበረ ካህናቱ ፤ እንደ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት
ወደ ላይ ወደሚቀጥለው እርከን ወደ ሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፋኑኤል ጋር በመሄድ አቤቱታቸውን አሰምተው ነበር፤ ይህ የቀበሮ
መነኩሴ የሚሰሩት ትክክል እንዳልሆነ እና ሃገረ ስብከቱ አስቸኳይ ብይን እንዲሰጥ ብለው ቢጠይቁም ፤ የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስም
(ድሮ እዚህ አዋሳ እንደለመዱት) ሙሰኛ ጳጳስ በመሆናቸው ገንዘብ ስለበሉበት እና የበሉበትን ወጨት ሰባሪ እንዳይባሉ ይመስላል፤
አርፋችሁ ተቀመጡ ፤ ምንም አይነት አቤቱታ አልቀበልም ብለው አቤቱታውን ሳይቀብሉ፤ ይልቁንም ጊዜያቸውን፤ ሥራቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን
ትተው ለአቤቱታ የሄዱትን ትላልቅ ሰዎች ከቢሮ እንኳን ሳያስገቧቸው ከውጪ “አቤቱታ አልቀበልም” በማለት ለማነጋገር እንኳን ፍቃደኛ
ሳይሆኑ ሁሌም እንደሚያደርጉት በደንብ ላጎረሳቸው ታማኝነታቸው አሳይትው የሀገር ሽማግሌዎችን እና ካህናቱን አሰናብተዋቸዋል መባልን በሰማን ወቅት “እውን ይህች ቤተ ክርስቲያን ያለ አስታዋሽ ቀረች እንዴ”
በማለት ለመስራቿ ለመድኅኔ ዓለም የዝግጅት ክፍላችን በሙሉ ፍርዱን ይስጥ በማለት ለማሕበረ ምዕመኑ እና ለማሕበረ ካህናቱ በእውነት
በከባድ ሃዘን ላይ እንደሚሆኑ እንገምታለን።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በርካታ ምዕመናን ለዝግጅት ክፍላችን የተለያዩ መልዕክቶችን ልከውልን ነበር፤ አንዳንዱ ይበልጥ ነገሮችን
ለማብራራት በሚመስል መልኩ ነገሮችን ገላልጠው ስሞችንም ጠቅሰው አሁን ነገሮችን በማወሳሰብ ላይ ካሉ የቦርድ አባላት መካክል ሙሉ
ስማቸውን እና መረጃቸውን ልከውልናል፤ እንዲሁም ከካህናት ወገንም ወደ አምስት የሚሆኑ የቀበሮ መነኩሴው ጋሻ ጃግሬዎች በመሆን ግብረ
በላዎችን ስማቸውን ከነ ሙሉ መረጃዎቻቸው የተላከልን አለ ጊዜ ሲደርስ ከነ ሙሉ መረጃው እናወጣዋለን፤ ለጊዜው ግን በተአቅቦ ይቀመጡ
ብለን እነዚህ መረጃዎች ለሕዝብ ይፋ ከማድረግ ተቆጥበናል፤ በሌላ ብኩል ደግሞ የቀበሮው መነኩሴ ደጋፊ የሆኑ ሰዎችም እንዲሁ መልእክቶችን
ልከውልናል አንዳንዶቹ ጸያፍ ስድቦችንም ጨምረው ልከውልናል፤ እውን ሃይማኖተኛ ከሆኑ እነዚህ ሰዎች ፈጣሪን ከመደገፍ ይልቅ አንድን
ለዚያውም ማንነቱ የማይታወቅን መነኩሴን ተደግፈው እውነተኛ ማንነታው ሲታወቅ የሚገቡበት እንዳይጠፋቸው ከወዲሁ እንዲያስቡት ለማስታወስ
እንወዳለን፤
በአጠቃላይ ከዚህ አጥቢያ ጋር በተያያዘ እስከ ዛሬ ድረስ 117 የተለያዩ መልእክቶችን ተቀብለናል፤ አንዳንዶቹ መጻፍ ተስኗቸው
በድምጽ የላኩልንም አሉ አንዳንዴ ስድብ ሌላ ጊዜ ደግሞ ምክር ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ብዙ ማስፈራራት የተቀላቀለበት መልዕክቶች ናቸው
የደረሱን፤ ከመልእክቶች በሙሉ ግን እጅግ በጣም ያስፈነደቀን እና ያዝናናን መልእክት ከአንዲት ተለቅ ያለች ሴት ወይም ሴትዮ ባል
ያላቸው አይመስሉም አነጋገራቸው ወይም ከመነኩሴው ጋር ሌላ ግብር እንዳላቸው አናውቅም ግን አነጋገራቸው የሆነ ጥቅማቸው የተነካባቸው
የሆነ ልክ አንዲት ሚስት ባሏ የተነካባት ያክል የተሰማቸው አይነት ሴት ናቸው መልእክቱን የላኩልን፤ ጊዜው ሲደርስ ይሄንንም ድምጽ
እናወጣዋለን አንባቢ ሰምቶ እንዲታዘብ ያክል እንጂ ሰዎችን ለማሳጣት እንዳልሆን ለማስታወስ እንወዳለን፤
ሴትዮይቱ በመልእክታቸው ላይ በከባድ ማስፈራራት ነው ንግግራቸውን የጀመሩት “በቅርብ ጊዜ ለፍርድ እንደምትቀርብ እና ከፍርድ
እንደማታመልጥ እወቀው” ለካ በዛ በሰለጠነው ዓለም የሚኖሩ ከእኛ የባሱ ደናቁርት ለካ አሉ በማለት የዝግጅት ክፍላችን ውስጥ የሚሰሩ
አባላት የሰማን ጊዜ በእጅጉ ተዝናናን፤ በመቀጠል ማስፈራራታቸውን ገታ
በማድረግ ደግሞ ፤ “እናንተ እኒህን የመሰሉ አባት በዚህ መልክ መግለጻችሁ እንዳያቀስፋችሁ፤ ደግሞ ትቀሰፋላችሁ፣ ፍርድ ያገኛችኋል፤
ንሰሀ ብትገቡ ይሻላችኋል . . . “በማለት የሚጠቅመውንም የማይጠቅመውንም
ድሪቶ ሲደርቱ ቆይተው ፤ ልክ ፍርድ የሚሰቱ የሚመስሉ ይልቁንም በፍትህ አደባባይ የዝግጅት ክፍላችን በቀበሮ መነኩሴው ላይ ያቀረብነውን
ትችት ልክ ሕገ እግዚአብሔርን የተላለፍን ያክል በመቁጠር በነገው እለት የሞት ፍርድ የሚፈረድብን ያክል ነው የማስፈራሪው ብዛት፣
የስድቡ መዓት፣ የማስጠንቀቂያው ጋጋታ፣ በአጠቃላይ ሴትይቱ በትክክል የመከኩሴው ጋር የአባት እና የምእመን አይነት ግንኙነት አይነት
ግንኙነት አይመስልም ፤ ፍፁም የተለየ የሚመስል ንግግር ደርተውብን የሄዱት የመነኩሴው . . . ምንነት ለጊዜው ግልጽ ባይሆንም
እጅግ ተቆርቋሪ እና ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ይልቅ ለቀበሮ መነኩሴው እጅግ ተቆርቋሪ እና ምናልባትም በሌላ ግብር የሚተዋወቁ የሚመስሉ
ሰው በላኩልን መልዕክት በእጅጉ ተዝናንተንበታል፤
በሌላ በኩል አንዳንድ ሰዎች ፍፁም ሚዛናዊ በመሆን የተወሰኑ ነገሮች እውነት እንደሆነ እና የተወሰኑት ትንሽ ማጋነን የሚመስሉ
ነገሮች እንዳሉ ጠቁመውናል፤ በእኛ በኩል ለአንባቢያችን ተገቢውን ምላሽ ሰጥተናል፤ ምናልባት ለአንባቢያችን እንደተናገርነው፤ እኛ
ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነትም ሆነ ችግርም የሌላብን መሆናችንን ገልጸን ይልቁንም የሚባለውን አጥቢያ በስም ከማውቅ ባሻገር አካባቢውንም
እንደማናውቀው ለመጠቆም ሞክረናል፤ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን በየትም ምትሆን አሃቲ ነችና ችግር ካለ እና በሰዎች ጥቆማ እንደደረሰን
እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነታችንን የደረሰንን መረጃ በመመርኮዝ መጣጥፎችን እናቀርባለን በደረሰን መረጃ እና ማስረጃ በመመርኮዝ
እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነታችንን አስተያየት እና ጥቆም እንሰጣለን፤ ይበልጥ ደግሞ የአጥቢያው ምእመናን አንድ በመሆን ለአጥቢያቸው
የሚበጀውን እና የሚጠቅመውን ማወቅ እና መገንዘብ ያለባቸው እነሱ እንደመሆናቸው መጠን፤ አንድ መነኩስ ተቀጣሪ ነው፤ የሕዝብ አገልጋይ
ነው ይልቁንም ደግሞ ሞተ ለክርስቶስ እራሱን አሳልፎ ሰጠ የሚባል ሰው እንደዚህ እጅግ በርካታ ሺህ ዶላሮችን የሕዝብ ገንዘብ እየመነዘረ
ቅንጡ መኪናዎችን፤ ቅንጡ ቪላዎችን ፤ ቅንጡ ቅምጦችን ካስከመጠ ይሄ የቀበሮ መኩሴ እንጂ የሕዝብም የእግዚአብሔርም አገልጋይ ሊሆን
አይገባውም የዝግጅት ክፍላችንም እስከ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ድረስ አቤቱታችንን እናደርሳለን የምናገኛቸውንም መረጃዎች ለጠቅላይ ቤተክህነቱ
እናደርሳለን፤ በፍጹም ምንም አይነት ጥላቻም ሆነ ትውውቅ የለንም፤ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጪ ግን ያልሆነ ነገር ሲሰራ እና
ሲያደርግ ከተገኘ ፤ በአግባቢ ስም ሳንጠቅስ ምክረ ሃሳብ ለመስጠት እንሞክራለን፤ ካልሆነ ግን ጥቁር እና ነጭ በሆነ መልኩ መረጃዎችን
በማስቀመጥ ያሉትን እውነታዎች ሁሉ ምዕመን አውቆ ፍርዱን እንዲሰጥ ይልቁንም ከቀበሮ መነኩስ እንዲጠነቀቅ መረጃዎችን እናደርሳለን፤
እናቀርባለን፤ ከዚህ በተረፈ ግን ምንም አይነት ግንኙነትም ሆነ ጥላቻ በዝግጅት ክፍላችን እና በአጥቢያው አገልጋዮች ላይ የሌለን
እና እንደሌለን ለማሳወቅ እንወዳለን።
በቅርቡ የምናገኛቸውን መረጃዎች በተለይም የቀበሮ መነኩሴው በዓመት ለ6 ወራት አዲስ አበባ የሚያመላልሳቸውን ጉዳዮች በይበልጥ
እና በቅርበት ተከታትለን ለአንባቢያን ለማድረስ ማንኛውንም ጥረት እናደርጋለን፤ ከአንባቢያንም መረጃዎች ይጠቅማል ለሕዝብ ቢደርስ
የሚያመጣው ችግር የለም ብለን የምናምነውን ብታደርሱን በዝግጅት ክፍላችን በኩል ማጣራቶች ተደርጎ ለሕዝብ ለማድረስ ቃል እየገባን፤
የቀበሮው መነኩሴ ወዳጆች፣ ግብር አበሮች እና ግብረ በላዎችም ማስተላለፍ የምትፈልጉት ካለ በዝግጅት ክፍላችን በኩል እንደወረደ
ያለ አድልዎ ለማቅረብ ሙሉ ፍቃደኞች መሆናችንን ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን፤ ከዚህ በፊት እንደጠቆምናችሁ በቀጥታ ለማግኘት ቢፈልጉ
በኢሜል አድራሻችን ማለትም kurtegnalejoch@gmail.com በመላክ መልእክታችሁን እንድታደርሱን
ለማስታወስ እና ለማሳሰብ እንወዳለን፤
ኢትዮጵያ ሃገራችንን እና ቅድስት ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን እግዚአብሔር ይባርክ ይጠብቅ አሜን
ይቆየን
ከግዝጅት ክፍላችን
በጣም ይገርማል እኚህ ሰውዬ በሩቅ አውቃቸዋለሁ: አንገታቸውን ደፋ ያደረጉ ሰው ናቸው: ሰውን ግን ማወቅ ከባድ ነው: ለነገሩ ዛሬ ዛሬ ለሆዱ የማይሞት መነኩስ እና አባት ተብዬዎች የሞሉበት ነው: እርግጠኛ ነኝ ልጅ እንዳላቸው ሲወራ ሰምቻለሁ ከዚህ በፊት: “ጭስ የሌለበት እሳት አይነድም ይባላል” አይደል ስለዚህ ሰውየው አንገት ደፊ አገር አጥፊ የሚባሉ ሳይሆኑ አይቀርም ለማንኛውም ስለመረጃው እናመሰግናለን።
ReplyDeleteWhat the hell, I have known Abba for very long time, I don’t even think of him in a such a position doing this and that, please share all this concerns for us so we also accept your claims, otherwise it won’t be a valid accusation.
ReplyDelete