Wednesday, February 4, 2026

የሰማዕታቱን ደም አንረሳውም

እነርሱም ማስጠንቀቂያውን ተቀብለው ንሰሐ ገቡ “የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም አዋጅ ነገሩ፥ ከታላቁም ጀምሮ እስከ
ደመ ሰማዕታት ይጣራል 

ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ። ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እርሱም ከዙፋኑ ተነሥቶ መጐናጸፊያውን አወለቀ ማቅም ለበሰ፥ በአመድም ላይ ተቀመጠ። አዋጅም አስነገረ፥ በነነዌም ውስጥ የንጉሡንና የመኳንንቱን ትእዛዝ አሳወጀ፥ እንዲህም አለ፦ ሰዎችና እንስሶች ላሞችና በጎች አንዳችን አይቅመሱ፤ አይሰማሩም ውኃንም አይጠጡ” አለ።  ዮናስ ወደ ቤተ መንግሥቱ እንኳ መሒዱን አናነብም ነገር ግን ንጉሡ ሳይቀር ለስብከቱ ጆሮ ሰጠ። 

ጾማቸው ሁሉንም ያስተባበረ ነበር። ልጅ፣ አዋቂ፣ ንጉሥ፣ አማካሪዎቹ፣ ሴት፣ ወንዱ፣ እንስሳውን ሁሉ አንድ ሆነ። ራስንም ሀገርንም ማዳን የሚቻለው እንዲኽ በትብብር ሲሆን ነው። “ሰዎችና እንስሶችም በማቅ ይከደኑ፥ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩኹ፤ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ” ለንሰሐ ትክክለኛ አብነት ሆኑ። መቶ ሃያ ሺህ ሕዝብ አንድ ላይ መጮሕ ያስገርማል። የሚሰሩትን ክፋት በአንድ ቀን አቆሙ። ያቆሙት ከክፋት ብቻ ሳይሆን ከምቾታቸውም ጭምር ነበር። ከአልጋ ወረዱ፣ መሬት አነጠፉ፣ ንጉሡ ዙፋኑን ለቀቀ፣ መሬት ወረደ። ስውነታቸውን አልታጠቡም ፤ የሚለሰልስ ልብስ አወለቁ የሚወጋጋ የሚቆረቁር ማቅ ለበሱ የሚቀቡትን ሽቱና ቅባት አቁመው አመድ ነሰነሱ አመድ ሰውነት ያቃጥላል ቆዳ ያደርቃል ይሰነጥቃል።

ይኽንን አለባበስ ብዙ ጊዜ የሚለብሱት ባሮች፣ ድሆች፣ ሐዘንተኞች የሚለብሱት ልብስ ነው። በዚኽ መልክ ጥፋታቸውን አመኑ። ይኽ ነበር ታላቅ ከተማ ያሰኛት። ለእግዚአብሔር ባሪያ መሆናቸውን፣ በእግዚአብሔር ፊት ድሆች መሆናቸው፣ በበደላቸው ሐዘንተኞች መሆናቸውን በልብሳቸው ሳይቀር ገለጹ። ብሔራዊ ጾም እና ጸሎት።

ዮናስ ሲሰብክ ምንም ተስፋ አልሰጣቸውም ይምራችኋል እንኳ አላላቸውም እና ብናዝን ይምረናል ብለው ያሰቡት ራሳቸው ናቸው “እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደ ሆነ፥ ከጽኑ ቍጣውም ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?” ብለው አሰቡ። ይሆናል የሚሉትን መልካም ነገር ሁሉ አደረጉ። ጾሙ ጸለዩ ከክፉ ተመለሱ የራሳቸውን ድርሻ ተወጡ። 

አንዳንድ ሰዎች  ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ብቻ መስማት  ይወዳሉ። በዚኽ ምክንያት ወደ ራሳቸው ንሰሐ መግባት ትኩረት ያጣሉ። ሁሌም እግዚአብሔር መሐሪ ነው እያሉ ራሳቸውን ያታልላሉ። አዎ መሐሪ ነው። ነገር ግን እኩል ፈራጅና ቀጪ መኾኑንም ማሰብ ይገባል። ምንም ባደርግ ይምረኛ ማለትን ይወዳሉ። ይኽንን ሲሉ ምንም ባደርግ አልቀጣም እያሉ ነው። ይኽ ትክክል አይደለም። እግዚአብሔር ጥፋትን ክፋትን እንደሚጠየፍ ማወቅ ይቀጣልም ብሎ ማሰብ ተገቢ ነው። የነነዌ ሰዎች ሁሉንም በአግባብ ፈጸሙ ምሕረቱንም አሰቡ። ምሕረቱ እንዳለ ሁሉ የምጽአት ቀን እንደሚመጣም ማወቅ ነው። ማንም ለማንም የማይቆምበት ቀን። 

የነነዌ ሰዎች ስለ እግዚአብሔር ምንም እውቀት የላቸውም። እኛ ከእነርሱ የተሻለ ብዙ እናውቃለን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ሞተልን እናውቃለን ፤ የዓለምን ፈተና ድል ያደረጉ ለንሰሐ አብነት የሆኑም ብዙ የቅዱስንን ታሪክ አለን። ታሪካቸውን እንሰማለን። እና ከነነዌ ሰዎች የተሻልን ነን። እነርሱ ሀገራቸውን አተረፉ እና 365 ቀን እየጸለይን የክርስቲያን ሀገር ናት እያልን እንዴት ሀገራችንን ከዚህ ሁሉ ግፍ መታደግ አቃተን????

“እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም” ከክፉ መመለሳቸው ተመለከተ። ከቀድሙ ሥራቸው መመለሳቸው አይቶ እግዚአብሒር ራራላቸው። “ተጸጸተ” ይላል። አዳምን በመፍጠሩ ተጸጸተ እንደሚለው። ነገር ግን እግዚአብሒር አላዋቂ ሆኖ እንደ ሰው ተጸጸተ ማለት አይደለም። ያደርግባቸ ዘንድ ካሰበው ነገር በነሱ መመለስ ውሳኔውን ቀየረ ማለት ነው። እግዚአብሔር የሰዎችን ነጻ ፋቃድ አይገፋም። እሽ ብንል ይመለሳል እንቢ ብንል ይቀጣል። 

ይኽ ቃል ብዙ ያስተምራል። እግዚአብሔር ሕዝቦቹ ስለሆነ ይወዳቸዋል። እግዚአብሔር የሚጸየፈው የለም። ሁሉም ይመለሱ ዘንድ ይወዳል። እግዚአብሔር ተደሰተባቸው። “ሥራቸውንም አየ” ይላል ውሏችንን ያያል። ምን ስንሰራ እንድምንውል ያያል። ሀብታም ብቻ ለመሆን እድሜ ልካችንን ስንዋትት ያያል፤ እንጀራ እያልን ስንደክም ያያል፤ ማኅበራዊ ኖሮ እያልን ላይ ታች ስንል ያያል። ይኽ ሁሉ የእግዚአብሔር ፈቃድን የምንፈጽምበት የምናመልክበት መልካም የምንሰራበት እቅድ ከሌለን ሀብትም ጠላት ይገዛል እንቅልፍ ይነሳል። ማኅበራዊ ኑሯችንም ውለታ ቢስ ነው የሚተርፍህ ሰውን ለማስደሰት በመጠመድ ላይ ብቻ ነው ራስን ማየት ተገቢ ነው።

የነነዌ ሰዎችን ከክፉ መንገዳቸውም መመለሳቸው አየ። ሥራን የሚወስነው መንገዱ ስለሆነ ነው። መንገድህ ሳይስተካከል ሥራህ አይስተካከልም። መንገድህ ሁሌ ሀብታም መሆን ከሆነ ያ ትክክል አይደለም። ሁሌ ለገንዘብ መኖር ከሆነ ያ ትክክል አይደለም። የተፈጠርክበትን ዓላማ እግዚአብሔር አንተን የፈጠረበትን ግብ ማየትና ለእግዚአብሔር ፈቃድ መኖር። 


የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment