Wednesday, August 14, 2013

“በ22 ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያን ያስተዳደረ ሙስሊም የለም” የሙስሊሞች የተቃውሞ ድምጽ


(አንድ አድርገን ነሀሴ 5 2005 ዓ.ም)፡- ባሳለፍነው ዕለተ ሀሙስ በሙስሊሞች የበዓል እለት አዲስ አበባ በብዙ ቦታዎች በተቃውሞ ስትናጥ መዋሏን የተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ኢቲቪን ሳይቀር ተቀባብለው መዘገባቸው ይታወሳል፡፡ በተነሳው ግጭት ፖሊስ ብዙዎችን ማረፊያ ቤት ማጎሩም ይታወቃል፡፡ ባሳለፍናቸው 3 ቀናት ፖሊስ ጣቢያዎች የምሳ እና የእራት ሰሀን በያዙ ሰዎች ተከበው ውለዋል፡፡ በወቅቱ የታሰበበትና የተጠና ሰላማዊ ሰልፍ መሆኑን ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ ፤ የባነሮቹ ተመሳሳይነት ፤ የመፈክሮቹ ይዘት ፤ ተቃውሞ የተነሳበት ሰአትና ቦታ ሰልፉ ታሰበበት መሆኑን ያመለክል ፡፡



እንደ ስታስቲክ ኤጀንሲ መሰረት በአዲስ አበባ ውስጥ 72 በመቶ ክርስቲያኖችና 16 በመቶ ሙስሊም ማህበረሰብ ይኖራል የሚል መረጃ ቢኖረውም የወጣው ሕዝበ ሙስሊም ግን እውን ይህ ሁሉ ሰው አዲስ አበባ ውስጥ ይኖራልን ? የሚያስብል ጥያቄ አስነስቷል ፡፡ በመሰረቱ በበዓላቸው ወቅት ከዚህ በፊት በኢድ ፤ በአረፋ እና በተለያዩ ወቅቶች የዕምነቱ ተከታዮች ወደ ገጠር የመግባት ሂደት የሚስተዋል ሲሆን በዚህ በዓል ግን የተገላቢጦሽ ሆኖ አልፏል ፡፡ሰዎች ከአዲስ አበባ ወደ ገጠር የሚገቡበት በዓል ሳይሆን ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ወደ አዲስ አበባ የመጡበት ሆኖ ተስተውሏል ፤ ይህ ሁኔታ በቁጥር ብዛታቸውን ለማሳየት እና ድምጻቸውን እጅጉን አጉልተው ለማሰማት እንደተጠቀሙበት ለመመልከት ተችሏል፡፡ ባሳለፍነው ዓመት በ2004 ዓ.ም ሀምሌ ላይ በአወሊያ ትምህርት ቤት የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬ እዚህ ደረጃ ሊደርስ ችሏል ፡፡ በወቅቱ ጥያቄው ከአወሊያ መስኪድ ከለሊቱ ስድስት ሰዓት በግላጭ በማይክራፎን ‹‹ጅሀድ›› በማወጅ ነበር ነገሩን የቆሰቆሱት ፤ ይህ የጅሀድ ጥሪን የተቀላቀሉ በርካቶች በወቅቱ ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመጋጨት ብዙዎች መታሰራቸውን ብዙዎች ላይ ቀላልና ከባድ አደጋ መድረሱን የአንድ ዓመት ትውስታችን ነው፡፡ ይህ በሆነ ከአንድ ቀን በኋላ በአዲስ አበባ በአምስቱም አቅጣጫዎች በህዝብ ማመላለሻ መኪናዎች ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ የነበሩ በርካታ የእስልምና ተከታዮችን መታወቂያቸውን ፖሊስ እየተመለከተ  ወደ መጡበት እንዲመለሱ ሲያደርግ እንደነበርም በወቅቱ ለመመልከት ችለናል፡፡ ለምሳሌ በናዝሪት መስመር ለ3 ቀናት ያህል ከአዳማ ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ የህዝብ ማመላለሻ መኪኖች ፖሊስ መታወቂያቸው እያየ ሲፈቅድና ሲከለክል ነበር ፤ በመሰረቱ የሰዎችን ከቦታ ቦታ የመዘዋወር መብት ሕገ-መንግስቱ ቢፈቅድም ችግር ሲፈጠር በደቦ ከሀገር ወደ ሀገር መንቀሳቀስ ምንን ያመለክታል ? እውን እነሱ እንደሚሉት አዲስ መስኪድ ለመመረቅ ወይስ በክብሪት የተነኮሰችው እሳት ወደ ሰደድ እሳትነት ለመቀየር ?

የሩቁን ያላስተዋለ አለቃ፣ ኃላፊ ወይም መሪ፣ አስተውሎም ያላመዛዘነ፤ አመዛዝኖም በጊዜ እርምጃ  ያልወሰደ ከሆነ፤ በአደጋው ውስብስብ መረብ ውስጥ ገብቶ መተብተቡ አይቀሬ ነው፡፡ አሁንም እየተስተዋለ ያለው ይህ ነው ፤ ሲጀመር በእኩለ ለሊት በአዲስ አበባ  ‹‹ጅሀድ›› ያወጁትን ሰዎች በፍትህ መድረክ ላይ ፍርድ ስላልተሰጠ ነገሮች እዚህ ሊደርሱ ችለዋል ፡፡ እንደተጣደ ወተት መቼ ሊገነፍሉ እንደሚችሉ የማናውቃቸውን ነገሮች በዐይነ-ቁራኛ ማየት፤ ተገቢውን ማርከሻ ማወቅና በጊዜው መጠቀም ተገቢ ሆኖ ሳለ መንግሥት ሁሉን በአግባቡ እና በጊዜው ተገቢ መልስ መስጠት ባለመቻሉ እዚህም እዛም የሚሰሙ ሃይማኖታዊ መሰል ፖለቲካዊ ጥያቄዎች እየተበራከቱ ይገኛሉ፡፡

በሰልፉ ወቅት ከተነሱ በርካታ መፈክሮች ውስጥ አንዱ “በ22 ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያን ያስተዳደረ ሙስሊም የለም” የሚል ነበር፡፡ ይህ ጥያቄ በሀገሪቱ ላይ እስላማዊ መንግሥት እንዲቋቋም የሚፈልጉ ሰዎች ጥያቄ ነው፡፡ አሁን ሰዎቹ ሃይማኖታዊ ጭንብላቸውን እንደለበሱ የወደፊት ራዕያቸውን ለማሳካት አንዱን ጥያቄ እንዲህ ብለው አቅርበውታል፡፡ የዛሬ ዓመት ገደማ ሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ ለመመስረት ጥያቄ ማቅረባቸውም መዘንጋት የለበትም፡፡

የሃይማኖት ጉዳዮችን እንዲከታተል እና ከስር ከስር መፍትሄ እንዲሰጥ በሚኒስትር ደረጃ የተቋቋመው የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ስራዎቹ ከሪፖርትነት ይልቅ መፍትሄ ሰጪ ሲሆኑ አይስተዋልም ፡፡ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ጥቂት አክራሪዎች ቤተክርስቲያን ሲያቃጥሉ ፤ ህዝበ ክርስቲያኑን በሰይፍ ሲያሳድዱ ፤  ሲብስብ የህይወትን መስዋዕትነት የሚያስከፍል ድርጊቲ ሲከውኑ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱም ሆነ መንግሥት ይህ ነው የሚባል መልስ በጊዜው መስጠት ባለመቻላቸው ሰዎቹ የልብ ልብ እንዲሰማቸው አድርጓቸዋል ፡፡ ትላንት በቤተክርስቲያኖች ላይ ለተነሳው ሰይፍ መልስ የሚሰጥ አካል ባለመኖሩ ዛሬ ዱላዎችና ሰይፎችም ወደ መንግሥት አካላት ተነጣጥረው ይገኛሉ፡፡

ከአመት በፊት በፓርላማ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሁኔታውን በግልጽ ለተወካዮች ምክር ቤት ማቅረባቸው ይታወቃል፡፡ ሱኒ ፤ ሰለፊ ፤ ወሀቢያ ምን ማለት እንደሆነ ላልገባው የኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ የህዝብ ተወካይ በግልጽ አስቀምጠዋል፡፡ ከሞላ ጎደል የማይመለከታቸውን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተቋማት ከመወረፋቸው በስተቀር ምስሉ ላልገባቸው ወገኖች ግንጽ እንዲሆን ጥረዋል፡፡ ነገር ግን በተግባር የተነገረውን ነገር ለማስቆመ መንግሥት እርምጃ ሲራመድ ማስተዋል አልተቻለም፡፡ የአሜሪካ መንግሥት ከአዲስ አበባ ለስቴት ዲፓርትመንት የላከው በዊኪሊክስ ተጠልፎ የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው በኢትዮጵያ ውስጥ ወሀቢያን ሰፍረውበታል አስተምህሮታቸውን ያካሂዱበታል ካለባቸው ቦታዎች ውስጥ ደሴ ፤ ሀረር ፤ ጅማ እና አርሲ ይገኛሉ ፡፡ አሁንም ከአመታት በፊት የተተከለችው የአክራሪነት ፍሬ ከሳምንታት በፊት በደሴ ፍሬ እያፈራች መሆኗን መመልከት ችለናል፡፡

ግብጽ አሁን ላለችበት ውጥንቅጡ ለወጣ ሁኔታ ትልቅቁንና የአንበሳውን ድርሻ የያዘው የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ ሕገ-መግስቱን ከሼሪያ ህግ በታች በማድረጉ እና መንግስቱም እንደ ኢራን እና መሰል ሀገራት እስላማዊ መንግሥት እንዲሆን መጣሩ ነበር ፡፡ አሁንም ኢትዮጵያ ወደዚህ መስመር እንድትሄድ የሚፈልጉ የቀን ቅዠተኞች ቀላል አይደሉም፡፡ ጥያቄያቸውም ‹‹ኢትዮጵያ ያስተዳደረ ሙስሊም የለም››ወደሚል ተሸጋግሯል፡፡ የትላልቅ ሰላማዊ ሰልፎች ጥያቄዎች በአንድ ጊዜ የሚመጡ አይደሉም ፤ ሲጀመር ‹‹የመጅሊስ ምርጫ ይካሄድ ፤ መጅሊሱ እኛን አይወክለንም›› አሉ፡፡ ሲቀጥል‹‹ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ እናቋቁም›› ተባለ፡፡ ሲቀጥል መጅሊሱ እንደማይወክላቸው የሚያሳምን የህዝብ ድምጽ እናሰባስብ አሉ፤ በህዝቡም ድምጽ መጅሊሱ ፈቅዶ ‹‹ምርጫው አካሂዱ ትችላላችሁ›› አላቸው ፡፡ ሲቀጥል ‹‹ ምርጫ መካሄድ ያለበት በመስኪድ እንጂ በቀበሌ መሆን የለበትም›› የሚል ጥያቄ አነሱ ፤ እያለ እያለ  “የታሰሩት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ይፈቱ”፣ “የደሴው ሼህ ግድያ ድራማ ነው”፣ “መጅሊሱ (ምክር ቤቱ) እኛን አይወክልም”፣ “ምርጫው ፍትሀዊ አይደለም”፣ ፣ “አህበሽ የተባለው አስተሳሰብ ይቅር”፣ “መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ አይግባ”፣ “አወሊያ የሙስሊሙ ተቋም ነው” ፤ እያለ እያለ አሁን “በ22 ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያን ያስተዳደረ ሙስሊም የለም” የሚል ጥያቄ ላይ ደረሰ………… ነገስ ጥያቄው ምን ይሆን?

አሁን የሀገሪቱ አስተዳዳሪ በስም አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ የOnly Jesus እምነት ተከታይ ናቸው ፤ ምክትሎቻቸው ሦስቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ውስጥ ሁለቱ የእስልምና እምነት ተከታዮች ናቸው ፡፡  የምክር ቤቱ ቁንጮ አቶ አባዱላ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ናቸው ፤ የኢህአዴግ ጽ/ቤት አላፊም ሙስሊም ነው፡፡ ከኦሮሚያ ክልል ከተመረጡ 169 የህዝብ ተወካዮች ከ70 በላዮቹ የእስልምና እምነት ተከታዮች ናቸው ፤ (ምንጭ ፡-የምክር ቤቱ ድረ-ገጽhttp://www.hopr.gov.et/HPR/faces/c/mps.jsp) ፤ በጠቅላላው ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ከ547 መቀመጫ ውስጥ ከ220 በላይ የእስልምና ተከታዮች ናቸው ፤ ካሉት 16 ቋሚ ኮሚቴዎች  አቶ ሳዲቅ አደም  የሕግ፤ የፍትህና አለስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ፤ ወ/ሮ ፈቲያ ዩሱፍ  የባህል፤ ቱሪዝምና መገናኛ ብዙኃን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበርና ፤ ወ/ሮ አይሻ እስማኤል የባህል፤ ቱሪዝምና መገናኛ ብዙኃን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሊቀመንበር ፤ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ  የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ም/ሊቀመንበር ፤ አቶ መሐመድ አብዶሽ  የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ፤ አቶ መሐመድ ዩሱፍ  አርብቶ አደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ፤  ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል  የትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር በመሆን ካሉት 16 ቋሚ ኮሚቴዎች ሰባቱን እነሱ እንደተቆናጠጡት አጥተውን ይሆን ? እነዚህ ቋሚ  ኮሚቴዎች ናቸው በሀገሪቱ ውስጥ ያሉት ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች የሚቆጣጠሩት ፤ በም/ቤቱ የአማካሪ ኮሚቴ አባላት የ21 ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ዘጠኙ ሙስሊሞች መሆናቸውን ሳያውቁ ቀርተው ይሆን ?  ከዚህ በላይስ እንዴት አድርገው መውረር ነው የፈለጉት?  ‹‹አንድ አድርገን›› ይችን ለመረጃ ያህል ያወጣች የሀገሪቱ የበላይ ህግ የሚወጣበት ቦታ ምን አይነት ስብጥር እንዳለው ለማመላከት ሲሆን ጥያቄውን መጠየቅ እንኳን ቢኖርበት በማን መጠይቅ እንዳለበት ከማመላከት ውጪ ነገ መሪዎቻችንና ተመራጮቻችን እነማን እንደሚሆኑም ለማሳየት ጭምር ነው፡፡ ታዲያ እነዚህ ሰዎች አላማቸው ምን ይሆን ? እነዚህ ሰዎች እንደፈጣን ቢፍቋቸው ጥያቄያቸው ሌላ ሆኖ እንደሚገኝ ልናውቅ ይገባል፡፡

የምክር ቤቱ የባህል፤ ቱሪዝምና መገናኛ ብዙኃን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች እና ምክትል ሰብሳቢዎች ሁለት ጊዜም ሲቀያየሩ ሁለቱም የእስልምና እምነት ተከታይ ነበሩ፡፡ በተጨማሪ የባህልና ቱሪዝም ሚንስትር አቶ መሀመድ ድሪል በአሁኑ ወቅት የግብጽ የኢትዮጵያ ሙሉ  አምባሳደር ለአስር ዓመታት መስሪያ ቤታቸውን አስተዳድረው ሲያበቁ በ2002 ዓ.ም በፊት ለፊት ወንበር አስቀምጠውት የሄዱት ሌላውን ሙስሊም ነበር ፤ የፓርላማው ቋሚ ኪሚቴ እና ባህልና ቱሪዝም ያስተሳሰራቸው መስመር የጠያቂ እና ተጠያቂነት ብቻ ሳይሆን እምነትም ያስተሳሰራቸው ይመስላል፡፡ (አስፈላጊ ከሆነ ከላይ እስከ መካከለኛው አስተዳደር ድረስ ምን ያህል ቦታ እንዳላቸው ከመረጃ ጋር ማቅረብ ይቻላል)፡፡ አንዱ ገበሬ ‹‹አንቺ ክምር ያለሽ መስሎሻል ተበልተሸ አልቀሻል›› ነበር ያለው

ሌላ ጊዜ እንመለስበታለን… ለዛሬ ቸር ሰንብቱ….
እግዚአብሔር አገራችንን ሰላም ያድርግልን
Source: http://andadirgen.blogspot.com/
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment