Wednesday, February 4, 2026

የሰማዕታቱን ደም አንረሳውም

እነርሱም ማስጠንቀቂያውን ተቀብለው ንሰሐ ገቡ “የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም አዋጅ ነገሩ፥ ከታላቁም ጀምሮ እስከ
ደመ ሰማዕታት ይጣራል 

ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ። ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እርሱም ከዙፋኑ ተነሥቶ መጐናጸፊያውን አወለቀ ማቅም ለበሰ፥ በአመድም ላይ ተቀመጠ። አዋጅም አስነገረ፥ በነነዌም ውስጥ የንጉሡንና የመኳንንቱን ትእዛዝ አሳወጀ፥ እንዲህም አለ፦ ሰዎችና እንስሶች ላሞችና በጎች አንዳችን አይቅመሱ፤ አይሰማሩም ውኃንም አይጠጡ” አለ።  ዮናስ ወደ ቤተ መንግሥቱ እንኳ መሒዱን አናነብም ነገር ግን ንጉሡ ሳይቀር ለስብከቱ ጆሮ ሰጠ። 

ጾማቸው ሁሉንም ያስተባበረ ነበር። ልጅ፣ አዋቂ፣ ንጉሥ፣ አማካሪዎቹ፣ ሴት፣ ወንዱ፣ እንስሳውን ሁሉ አንድ ሆነ። ራስንም ሀገርንም ማዳን የሚቻለው እንዲኽ በትብብር ሲሆን ነው። “ሰዎችና እንስሶችም በማቅ ይከደኑ፥ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩኹ፤ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ” ለንሰሐ ትክክለኛ አብነት ሆኑ። መቶ ሃያ ሺህ ሕዝብ አንድ ላይ መጮሕ ያስገርማል። የሚሰሩትን ክፋት በአንድ ቀን አቆሙ። ያቆሙት ከክፋት ብቻ ሳይሆን ከምቾታቸውም ጭምር ነበር። ከአልጋ ወረዱ፣ መሬት አነጠፉ፣ ንጉሡ ዙፋኑን ለቀቀ፣ መሬት ወረደ። ስውነታቸውን አልታጠቡም ፤ የሚለሰልስ ልብስ አወለቁ የሚወጋጋ የሚቆረቁር ማቅ ለበሱ የሚቀቡትን ሽቱና ቅባት አቁመው አመድ ነሰነሱ አመድ ሰውነት ያቃጥላል ቆዳ ያደርቃል ይሰነጥቃል።