Wednesday, October 28, 2026

የመጀመሪያ ዙር ጥሪ ለመላው ሃገረ ወዳድ እና ሰላም ፈላጊ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በመላው ዓለም

 


◈ ለሀገር ወዳድ እና ለኦርቶዶክሳውያን አካላት።
◈ በብልጽግና ሥርዓት ሀገራችን እና ነባር እምነታችን መጥፋት ከጀመረ እነሆ ስምንት ዓመታት አልፈዋል፤
◈ የብልጽግና መንግሥት  የእውነተኛ መልኩ መገለጫው አርሲ ነው።
◈ እናንተ ሀገር ለመጠበቅ የወጣችሁለት ሥርዓት ሀገር የሠሩ ኦርቶዶክሳውያንን ሀገር አልባ አድርጎ ማሳደድ፣ ማፈናቀል፣ ቤተ መቅደሳችንን ማቃጠል፣ ምእመናንን ማረድ፣ በግድ ማስለም ከጀመረ ስምንት ዓመት አልፈዋል።
◈ እኛ ኦርቶዶክሳውያንም መሳደድ፣ መገደል፣ መፈናቀል፣ መቅደሳችን መንደድ፣ ቅርሳችን መውደም ከጀመረ ስምንት ዓመታት አልፈዋል፤ በደንብ እንዲገለጽላችሁ በተከታታይ ዓመታት በአሩሲ ኦርቶድክሳውያን የተፈጸመውን ግፍዕ ተሠልከቱ!

በመጀመሪያ በምዕራብ አርሲ የጀመረው ጭፍጨፋ እና ማሳደድ በመቶ እና በሺዎች የሚቆጠሩትን ንፁሐን ዜጎችን ገድሎ፣ አርዶ፣ እና አሳዶ ዛሬ ዛሬ በምሥራቅ አርሲ እጅግ በጣም ተባብሶ ቀጥሏል፤ የዞኑ ሃላፊዎች ይሄ ሁሉ ዜጎች ደማቸው እንደ ጎርፍ ሲፈስ ከመጠየቅ ይልቅ በሃገር አቀፍ ደረጃ ተሸልመዋል፤ ለሰሩት ዜጎችን ሃገር አልባ የማድረግ ሥራ እና ጭፍጭፎ ማሳደዱን ሥራ በሚገባ ስለተወጡ ያለምንም ህፍረት እና ሃዘን በሰፊው ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፤ ዛሬ ላይ ከ60 በላይ የሚሆኑ ዜጎች በግፍ ሕፃናት፣ ሴቶች እና አረጋውያንን ጨምሮ በግፍ እንደ በግ ሲታረዱ እና ደማቸው እንደጎርፍ ሲፈስ፤ የብልጽግና አለቅላቂዎች "ታዬ" ፅምዶ ነው የሚጮኸው በማለት ስላቅ፤ የኦሮሚያ የጸጥታ ሃላፊዎችም እንደተባለቱ "የፅምዶ ሰላም ማደፍረስ በአርሲ ከሸፈ" በማለት ሊያስተባብሉን ሞክረዋል፤ 

 

◈ ሀገር ወዳድ ወንድሞቻችን እናንተ የቆማችሀለት ሕዝብና ሀገር የትኛው ነው?
1) ሀገርና የሀገር አንድነት የሚፈርስበት?
2) ታሪካችን እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ የሚፋቅበት?
3) ኦርቶዶክስ መሆን ወንጀል ሁኖ ከምድረ ገጽ የምንጠፋበት?
4) አብያተ ክርስቲያናት የሚነዱበት?ምእመናን የሚታረዱበት?.. እናንተ የምትጠብቁት የትኛውን ነው?
ስለሆነም፦
ኦርቶዶክሳውያን የሆናችሁ እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን፦
1) የመከላከያ አካላት፤
2) የፖሊስ አካላት፤
3) የደኅንነት አካላት፤
4) የሚኒሻ አካላት፤
5) የአድማ ብተና አካላት፤
6) የልዩ ኃይል አካላት፤
7) የጥበቃ አካላት፤
8) የአየር ኃይል አካላት፤
9) የባሕር ኃይል አካላት፤
10) የደንብ አስከባሪ አካላት፤
11) አክቲቪስት ሁናችሁ ለምታገለግሉ አካላት፤
12) የፖለቲካ አካላት፤
የሀገር እና የሃይማኖት ፍቅር ያላችሁ ሁሉ ራሳችሁን ከዚህ ጸረ ኦርቶዶክስና ሀገር ሥርዓት ለይታችሁ ለሀገራችሁና ለሃይማኖታችሁ ትቆሙ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን ጩኸት ይድረሳችሁ።
◈ እናንተን ዱላ መከታ አድርጎ ሥርዓቱ እኛን ኦርቶዶክሳውያንን እየገደለን ስለሆነ ራሳችሁን አውጡ፤
ኦርቶዶክሳውያንን የሌሉባት ሀገር፣ የሚሳደዱባት ሀገር፣ የሚፈናቀሉባት ሀገር፣ የሚገደሉባት ሀገር፣ ቤተ መቅደሳችን የሚነድባት ሀገር፣ ታሪካችን ወንጀለኛ የሆነባት ሀገር፣ ሰይጣናዊነት የሚስፋፋባት ሀገር ለእናንተ ምናችሁ ናት?
◈ በተዘረዘሩት ተቅዋማት ዘመድ ወዳጅ ያላችሁ ሁሉ መልእክቱ እንዲደርሳቸው አድርጉ።

ከቤተሰቦች ባሻገር በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መጥፋት የሚገዳችሁ፣ የንፁሐን ክርስቲያኖች መጨፍጨፍ የሚያሳዝናችሁ ማንኛውም የሃገራችን ኢትዮጵያ ልጆች በሙሉ👇
◈ የሳተላይት ቴሌብዥ ጣቢያያች፤
◈ ዩቱበሮች፤
◈ ቲክቶከሮች፤
◈ ፌስቡከሮች፤
◈ ቲዊተሮች፤
◈ ቴሌግራም ገጾች፤
◈ ፌስቡከሮች፤
◈ ትዊተሮች፤
◈ የተለያየ ሚድያ አይነት የምትጠቀሙ።
◈ መልእክታችን ይዳረስ ዘንድ በቅዱሳን ሰማዕታት ደም ስም እንማጸናለን። 

 በአርሲ፣ በወለጋ፣ በሞያሌ፣ በሻሸመኔ፣ እና በሰላሌ አካባቢ ደማቸው እንደጎርፍ የሚፈሰው ንፁሐን ዜጎቻችን ደም ሁላችንንም ነቅተን አንድ ነገር ማድረግ እንዳለብን እናምናለን፣ ደማቸው ይጣራል፣ የነዚያ ሕፃናት ደም ይጣራል ሁላችንም በምንችለው እና ባለንበት ሁሉ የምንችለውን የንፁሐኑን ጥሪ እንጣራ ሰሚ እስከምናገኝ ድረስ፤ መቆም የለበትም የንፁሐን ደም ከምድረ ኢትዮጵያ ይጮኻል ለዚህም ተጠያቄ የሆኑትን አካላት ከዓብይ አሕመድ፣ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል የጸድጣ ክፍል ሃላፊዎች፣ የአርሲ ዞን የሁሉም ክልል ሃላፊዎች ከተጠያቂነት አያመልጡም፤ ፍትህ ለአርሲ ክርስቲያኖች እያልን ጩኸታችንን እንቀጥል እግዚአብሔር ይረዳናል፤ ፍርድ እስከምናገኝ ድረስ እንጮኻለን፤ የእኛ ሲኖዶስ ጆሮውን በብር ከዘጋ ቆይቷል ስለዚህ ብቸኛው መፍትሄያችን በምንችለው መንገድ በሙሉ መጮኸ እና ድምጽ ማሰማት ነው፤ በተለይ በውጪ ሃገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የዓለም አቀፍ ማሕበረስብ ተወካዮችን የአውሮፓውያን እና አሜሪካን ተወካዮች፣ የሰብዓዊ መብት ተወካዮችን፣ የዓለም አብያተ ክርስቲያናትን ተወካዮች በደብዳቤ አድርሱልን ይሄ ችግር በቀላሉ የሚቆም አይደለም ምክንያቱም ጠላቶቻችን አርሲ ከክርስቲያኖች ነጻ እስከሚሆን አናቆምም የሚል መረጃም ደርሷል እነ ጀዋርም በሚዲያ ወጥተው ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ይሉናል ነገር ግን በውስጥ ለወሃቢያዎቹ ቢላና መሣሪያ እያቀበሉ እንደሆነ ይሰማል። ስለዚህ እኛና እና እኛ ብቻ ነው ነን ያለነው ይሄንን ማስቆም ካልቻልን፣ ነግ በእኔ እንደሚሆን ማሰብ ይኖርብናል ወገኖቼ። 
ቸር ይግጠመን

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment