
የአርሲ ሀገረ ስብከት በ45ኛው ሰበካ መንፈሳዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባቀረበውን ሪፖርት አንደኛ ወጥቶ ተሸልሟል¡¡¡። በሪፖርቱም እንኳን በሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን የተጨፈጨፉበት ፣ አብያተ ክርስቲያናት የተቃጠሉበት ሊመስል ቀርቶ፣ 1 ሰው እንኳን የሞተበት አይመስልም። ሪፖርቱ ሁሉ ለጨረቃው ጳጳስ መወድስ ሆኖ አለቀ። ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ በርካታ የቤተክርስቲያኒቱ ምዕመናን እንደበግ የታረዱበት፣ ካህናት አንገታቸው የተቀላበት፣ አብያተ ክርስቲያናት እንደ ጧፍ የነደዱበት በተለይ እጅግ በሚገርም ሁኔታ ምዕመናን ጽላት ተሸክመው ሃገር ለቀው እስከ መሰደድ የደረሱበት የምሥራቅ አርሲ ሃገረ ስብከት በደረጃ 84% አምጥቷል ብለው ስላቅ የሚመስል ሽልማት ለሀገረ ስብከቱ ተሸልሞ ማየት ፤ እውነት ቤተክህነቱ የሚያደርገውን ያውቀዋል? ከ2ሺህ በላይ ኦርቶዶክሳውያን ማለቃቸውን አያውቁም እንዴ? በርካቶችስ ሃገራቸውን ቀያቸውን እትብታቸው የተቀበረበትን መንደር ትተው መሰደዳቸውን አልሰሙም ይሆን እንዴ? ይሄ በእውነት እነዚህ ደማቸውን ያፈሰሱትን አጥንታቸውን የከሰከሱትን ምዕመናን ደግሞ የመግደል ያክል ነው፤ አምላከ እሥራኤል ፍርዱን ይስጥ ነው የሚባለው ፤ የሚገርመው ደግሞ ሪፖርቱን የሚሰሙት በሙሉ የምዕመናንን መገደል እንደማያውቁ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ዝም በማለት ሪፖርቱን ማጽደቃቸው ነው።
እናም ቤተክህነታችን ሞታችንን አያውቀውም ስላችሁ
በአይ_አዎ ዘይቤ ነው።
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም
No comments:
Post a Comment