በቅድሚያ ሰላምታችን ይድረሳችሁ ውድ አንባቢያን፤ ይሄንን ደብዳቤ እና ይሄንን ጽሁፍ ከሰሜን አሜሪካ ከአንድ አንባቢያችን ተልኮልን በተለያየ ጊዜ የዋሺንግተን ሃገረ ስበክት አባ ፋኑኤል ላይ የተለያዩ ጽሁፎችን ማቅረባችን ይታወሳል፤ ሰውየው ከዚህ በፊት ባልተሰጣቸው ሥልጣን በአንድ አጥቢያ ላይ ላለ አንድ መነኮስ የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብዳቤ መስጠታቸው ይታወሳል፤ አሁን ደግሞ በሌላ የሽምግልና ደብዳቤ ማውጣታቸውን ስንሰማ በጣም ግርምት ፈጥሮብናል፤ <<በአንድ ራስ፤ ሁለት ምላስ>> የሚሉት አይነት መሆኑ ነው፤ ጽሁፉን ሳንቀንስ ሳንጨምር እንደተላከልን አቅርበነዋል፤ ሃሳብ አስተያየታችሁን እንጠብቃለን እስከዚያው መልካም ጊዜ።
ሀገረ ስብከቱ ማሸማገል ነው ወይስ ማደራደር ነው የፈለገው? ሽምግልና የእርቅና የሰላም መሣሪያ እንጂ የግል ፍላጎት ማስፈጸሚያ አይደለም። ሽምግልና በኢትዮጵያ ታሪክ በሃይማኖትም በባህልም እጅግ የላቀ ስፍራ ያለው የተከበረ የማህበረሰብ ታላቅ እሴት እንጅ ለሽፍጥ የሚጠቀሙበት የጊዜ መግዣ ወይም ማደንዘዣ ስልት አይደለም ። የሽምግልናው ጉዳይ ከዚህ በፊት ተሞክሮ እንዳልተሳካ እየታወቀ አሁንም እዚያው አዙሪት ውስጥ ተመልሰን እንድንገባ ለምን ተፈለገ?













